Get Mystery Box with random crypto!

Ertalepost ኤርታሌ ፖስት

የቴሌግራም ቻናል አርማ ertalepost — Ertalepost ኤርታሌ ፖስት E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ertalepost — Ertalepost ኤርታሌ ፖስት
የሰርጥ አድራሻ: @ertalepost
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.46K
የሰርጥ መግለጫ

ለአስተያየት
@MarcusR17
https://youtube.com/channel/UCvQGJghpEs4UQUivG_J4QLg
Subscribe our youtube channel

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-30 16:07:15
በአዲስአበባ የተገነባው ኃይሌ ግራንድ ሆቴል ሊመረቅ ነው

ኃይሌ ሪዞርት እና ሆቴሎች በአዲስ አበባ ላምበረት አካባቢ ያስገነባውን ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል በቅርቡ እንደሚያስመርቅ ተገለጸ፡፡

ባለ ዘጠኝ ወለል ዘመናዊ ሕንጻ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል እንደሆነ የተነገረለት የኃይሌ ሪዞርት እና ሆቴል 8ኛ ሆቴል "ኃይሌ ግራንድ ሆቴል" ተብሎ እንደተሰየመ ተሰምቷል፡፡

ሆቴሉ 160 ምቹ የመኝታ ክፍሎች ፤ ስታንዳርድ እና ፕሬዝደንሺያል ተብለው የተለዩ ልዩ የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች ፤ የመዋኛ ገንዳ ፤ ጂምናዝየም ፤ ቅርጫት ኳስ ፤ የቤት ውስጥ እግር ኳስ ፤የጠረጴዛ ቴኒስ መጫወቻዎች እና የምሽት ክበብ አካቶ የያዘ ነው ፡፡

በተጨማሪም 300 መኪኖች የሚይዝ ፓርኪንግ በሕንጻው ምድር ክፍል ተገንብቶለታል፡፡

በአሁኑ ወቅት የሰራተኞች ቅጥር እና ስልጠና በመካሔድ ላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 በሃዋሳ አንድ ብሎ የመጀመሪያውን ሆቴል የከፈተው ሃይሌ ሪዞርት እና ሆቴሎች በቅርቡ በወላይታ ሶዶ ፤ ደ/ብርሃን እና ኮንሶ ተጨማሪ ሶስት ሆቴሎች እንደሚከፍት ታውቋል፡፡

በቀጣይ በጎርጎራ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ልዩ የመዝናኛ ሆቴል እንደሚገነባ እና ሃይሌ ሪዞርት ዓለም አቀፍ ብራንድ በማድረግ በምስራቅ አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ አገሮች ሆቴሎች እና ሪዞርቶች የመገንባት እቅድ እንዳለው ታውቋል፡፡

(ምንጭ፦ ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ)

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
234 viewsedited  13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 16:07:15
የናይጄሪያ ፖሊስ በቲኪቶክ ላይ በለቀቁት ስነ ምግባር የጎደለው ቪዲዮ ሁለት ሴት መኮንኖችን ከስራ አገደ።

የናይጄሪያ ፖሊስ ሃይል ኦባዜ ብሌሲንግ እና ኦባዜ ኢማኑኤልላ ኡጁ የተባሉ የከፍተኛ ቁጥር ፖሊሶችን በስነ ምግባር ጉድለት እና በማህበራዊ ሚዲያ ፖሊሲ ጥሰት ከስራ አግዷቸዋል።

አፍሪካን ሪፖርት ፋየል

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
216 viewsedited  13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:43:43
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አልጀርስ ፕሬዝዳንታዊ ቤተ መንግሥት ሲደርሱ በአልጄሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት አብደልመጂድ ታቡን አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያ እና አልጄሪያ ግንኙነት ላይ መክረዋል።

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
301 views11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 06:29:17
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አልጄሪያ ገቡ

ነሐሴ 22 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አልጄሪያ ገቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአልጄሪያ ርዕሰ መዲና አልጀርስ ሲደርሱ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አይመን ቤናብደርሃማኔ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአልጄሪያ በሚኖራቸው ቆይታ የአገሪቱን ፕሬዚዳንት አብድልማጂድ ተቡኔን ጨምሮ ከተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
315 viewsedited  03:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 18:25:13 ሰበር_ዜና

የመከላከያ ሠራዊት፣ ኮማንዶ፣ ልዩ ኃይልና ፋኖ በጥምረት የቆቦን ከተማ መልሶ ተቆጣጠረ!

የአራቱንም ጥምር ምት መቋቋም የተሳነው የህወሓት ጀሌ ቆቦን ለቆ
ወደ አላማጣ ጉዞ ጀምሯል። እንደገና ዛሬ 4 ሰዓት አካባቢ በግዳን በኩል ለመግባት ሞክሮ አከርካሪውን ተመትቶ ተመልሷል።

-ዛሬ የተሰራው ኦፕሬሽን የሚደንው ነው። ኮማንዶዎች የወልዲያን ዩኒቨርስቲ መግቢያ በር፣ ወደ ባህርዳር የሚወስደውን መንገድ ማንም እንዳይገባና እንዳይወጣ ከዘጉ በኋላ ነው የቆቦ ኦፕሬሽን የተከናወነው። የምሥራቁ ኮከብ ፋኖ ምሬ ወዳጆ ከመከላከያና ከልዩ ኃይል ጎን ሆኖ የሰራው ጀብዱ ታሪክ የሚዘክረው ይሆናል።

-ሌላው የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ከዛሬ ጀምሮ የሚተገበር የሰዓት እላፊ ገደብ አስቀምጧል።
ከተመደበው የጸጥታ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ማንኛውም ሰው መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። ለጸጥታ ስራ ስምሪት ከተሰጠው ተሽከርካሪ ውጭ ማንኛውም ተሽከርካሪ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ የማይችል መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።

-በተመሳሳይ የደባርቅ ከተማ አስተዳደር
በከተማዋ የሚገኙ የተፈናቃይ መጠለያ ነዋሪ ከ12:00 በሗላ ወደ ውስጥም ሆነ ወደ ከተማ መግባት ከልክሏል። የከተማ ባጃጆች ከምሽቱ 1:00 በሗላ መንቀሳቀስ አይችሉም።

-አሁን ግምባር ላይ ያለው ወኔ፣ እልህና ቁጭት የሚገርም ነው። መከላከያ ነፍሱን እየሰጠ ነው፤ ልዩ ኃይሉ አጥንቱን እየከሰከሰ ነው፤ የምሥራቅ ዐማራ ፋኖ ደሙን እያፈሰሰ ይገኛል። ከኛ የሚጠበቀው ሞራል፣ ስንቅ፣ ደጀንነት ብቻ ነው።

-ነገርግን እዚህ የሚኖረው በስነልቦናው ስልብ የሆነው የፌስቡክ ጀሌ መከላከያን ያህል የሀገር ተቋም ሲሳደብ፣ ሲያንቋሽሽ፣ ሲሳለቅ ይውላል፥ ኧረ ሞራል ወዴት አለሽ? በምን ሞራል ነው ደሙን እያንጠባጠበ፣ ላቡን እያፈሰሰ፣ ሸለቆ ውስጥ አጥንቱን እየከሰከሰ ያለ ወታደር የሚሰደበው?
ቤተሰብ፣ ሃይማኖትና ትምህርት ቤት የሚባሉ ተቋማት ይህን ትውልድ እንዴት አድርገው አስተምረው ቢያሳድጉት ነው እንዲህ ያለ የተሳሳተ ትውልድ (wrong generation) የተፈጠረው?

በፊት መከላከያ የቅጥር ማስታወቂያ ሲያወጣ ተመዝገቡ፣ ዐማራ በልኩ ውክልና ያግኝ፣ ዘመናዊው መሳሪያዎችና ሥልጠናዎች የሚገኙት ከዚህ ተቋም ነው ስንል "አይሆንም" ብለው ሰፊ ዘመቻ ከፍተው የሚመዘገቡ ጠፍቶ ክልሉ የሚያስመዘግበው ሰው አጥቶ እንደነበር አስታውሳለሁ። የትናንቱ ረስተው ዛሬ ደግሞ በመከላከያ ተከዳን የሚል ትናንትና ውስጥ ይገኛሉ። አሁንም የምመክረው ወቀሳውን ከፖለቲካ አመራሩ ላይ አድርጉ እጃችሁን ከመከላከያ ላይ አንሱ!

-በጣም ያስገረመኝ ወያኔ ከጦርነቱ በፊት በድጅታል ሚዲያ ሊያግዛት የሚችል ይህን ያህል አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ግብረ ኃይል ታዘምትብናለች ብዬ በፍጹም አልጠበቅሁም ነበር።

የሆነው ሆኖ ባንዳ አንገቱን ደፍቶ ይቀራል የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ሠራዊት ድል ማድረጉን ይቀጥላል።

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
367 views15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 14:18:55
የወልድያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በዚህ መልኩ ከተማውን በእግራቸው ለቀው እየወጡ ይገኛሉ። ባልተጨበጠ መረጃ መንገላታት አነበረባቸውም።

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
384 views11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 12:27:19
አቶ ኢሳያስ ጅራ በድጋሚ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንን  ለቀጣዩ 4 ዓመታት እንዲመሩ በ 94   ድምፅ  ተመርጠዋል።

Via Hatrick Sport

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
364 viewsedited  09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 21:34:31 የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አሸባሪው ሕወሐት በአንድ በኩል የተለመደውን የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማ ከውጭ በብዙ አቅጣጫ እያጠቃ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ውስጥ ሠርጎ ገቦችን በማሥረግ የሕዝቡን ደኅንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል።

የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ ሲባል የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን በመልቀቅ እና ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ተገዷል።

አሸባሪው ኃይል የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱን ካላቆመ መከላከያ ሕጋዊ ፣ ሞራላዊና ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣት የሚገደድ ይሆናል።

ነሃሴ 21 ቀን 2014 ዓም
አዲስ አበባ

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
102 viewsedited  18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 11:00:26
ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬቷን ከባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተቀብላለች፡፡

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በስፖርቱ ዘርፍ ለሀገሯ ባበረከተችው ታላቅ አስተዋጽዖ ነው ከባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት የተሰጣት፡፡

አሚኮ

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
200 viewsedited  08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 18:41:52
ፎቶ : ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ በባህርዳር ገቡ።

ባህር ዳር ዩንቨርስቲ በነገው እለት በሚያካሂደው የተማሪዎች ምረቃ ወቅት ለብፁዕ አቡነ ኤርምያስ እንዲሁም ለኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት እንደሚሰጥ ማሳወቁ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ አትሌት ደራርቱ ቱሉ ዛሬ በባህርዳር ገብተዋል።

ባህር ዳር አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የባህርዳር ዩንቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ በተገኙበት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
251 views15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ