Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስአበባ የተገነባው ኃይሌ ግራንድ ሆቴል ሊመረቅ ነው ኃይሌ ሪዞርት እና ሆቴሎች በአዲስ አበ | Ertalepost ኤርታሌ ፖስት

በአዲስአበባ የተገነባው ኃይሌ ግራንድ ሆቴል ሊመረቅ ነው

ኃይሌ ሪዞርት እና ሆቴሎች በአዲስ አበባ ላምበረት አካባቢ ያስገነባውን ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል በቅርቡ እንደሚያስመርቅ ተገለጸ፡፡

ባለ ዘጠኝ ወለል ዘመናዊ ሕንጻ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል እንደሆነ የተነገረለት የኃይሌ ሪዞርት እና ሆቴል 8ኛ ሆቴል "ኃይሌ ግራንድ ሆቴል" ተብሎ እንደተሰየመ ተሰምቷል፡፡

ሆቴሉ 160 ምቹ የመኝታ ክፍሎች ፤ ስታንዳርድ እና ፕሬዝደንሺያል ተብለው የተለዩ ልዩ የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች ፤ የመዋኛ ገንዳ ፤ ጂምናዝየም ፤ ቅርጫት ኳስ ፤ የቤት ውስጥ እግር ኳስ ፤የጠረጴዛ ቴኒስ መጫወቻዎች እና የምሽት ክበብ አካቶ የያዘ ነው ፡፡

በተጨማሪም 300 መኪኖች የሚይዝ ፓርኪንግ በሕንጻው ምድር ክፍል ተገንብቶለታል፡፡

በአሁኑ ወቅት የሰራተኞች ቅጥር እና ስልጠና በመካሔድ ላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 በሃዋሳ አንድ ብሎ የመጀመሪያውን ሆቴል የከፈተው ሃይሌ ሪዞርት እና ሆቴሎች በቅርቡ በወላይታ ሶዶ ፤ ደ/ብርሃን እና ኮንሶ ተጨማሪ ሶስት ሆቴሎች እንደሚከፍት ታውቋል፡፡

በቀጣይ በጎርጎራ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ልዩ የመዝናኛ ሆቴል እንደሚገነባ እና ሃይሌ ሪዞርት ዓለም አቀፍ ብራንድ በማድረግ በምስራቅ አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ አገሮች ሆቴሎች እና ሪዞርቶች የመገንባት እቅድ እንዳለው ታውቋል፡፡

(ምንጭ፦ ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ)

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng