Get Mystery Box with random crypto!

Ertalepost ኤርታሌ ፖስት

የቴሌግራም ቻናል አርማ ertalepost — Ertalepost ኤርታሌ ፖስት E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ertalepost — Ertalepost ኤርታሌ ፖስት
የሰርጥ አድራሻ: @ertalepost
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.46K
የሰርጥ መግለጫ

ለአስተያየት
@MarcusR17
https://youtube.com/channel/UCvQGJghpEs4UQUivG_J4QLg
Subscribe our youtube channel

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 09:44:00
የምያንማር ፍርድ ቤት ከስልጣን የተባረሩትን የቀድሞ የሀገሪቷን መሪ ኦንግ ሳን ሱ ኪን 'በምርጫ ማጭበርበር' ክስ የሶስት አመት እስር ፈርዶባቸዋል።

ኤፒ

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
28 viewsedited  06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 09:44:00
ከንቲባው ተገደሉ

የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው የተሰጣቸውን የህዝብ አደራ ለመወጣት ውሎአቸውን በስራ ተጠምደው ለእረፍት ትላንት ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ምሽት ከመኪና ላይ ወርደው ወደቤታቸው ሊገቡ ሲሉ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው አልፋል ።

አቶ ውብሸት አያሌው ባለትዳር እና የአንድ ሴትና አንድ ወንድ አባት ነበሩ ።

አቶ ውብሸት ወደ ሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር በስራ ኃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት በቀወት ወረዳ አስተዳደር በተለያዩ ተቋማት በባለሙያነትና በስራ ኃላፊነት ህዝብን በለጋ የወጣትነት ጊዜያቸው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

እንደ አንድ የህዝብ አደራ እንደተቀበለ አመራር እና እንደ ተወላጅ ከተማዋ የሚገባትን እድገትና ማዕረግ እንድታገኝ እንዲሁም ነዋሪዎቿ ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ በከፍተኛ ቁጭት እየሰሩ የሚገኙ ወጣት አመራር ነበሩ ።

የደረሰብን ሀዘን እጅግ መራርና አስደንጋጭ ነው ፤ ይህም መስዋእትነት ለህዝብ ዘላቂ ሰላም ፣ ልማትና አንድነት የተከፈለ ዋጋ ነው ።

አቶ ውብሸት ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት እንዲያኖርልን ፤ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለቤተሰቦቹ ደግሞ መጽናናትን አስተዳደሩ ከልብ እንመኛለሁ።

ቀብሩም በሸዋሮቢት ከተማ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከቀኑ 6 ስዓት ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት የስርአተ ቀብራቸው ይፈጸማል።

(የሸዋሮቢት ከንቲባ ፅ/ቤት የሐዘን መገለጫ)

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
27 viewsedited  06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 09:44:00
ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ የመንግሥት የሰላም በሮች ክፍት መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ መንግሥት የዜጎቹን ደኅንነት የመጠበቅ ግዴታውን መወጣት ይቀጥላል ሲሉ ዛሬ ለውጭ ዲፕሎማቶች በሰጡት ማብራሪያ ተናግረዋል። ሕወሃት ተኩስ አቁሙን በመጣስ "በግጭት ቀስቃሽ ፕሮፓጋንዳ፣ ሕዝብን ለጦርነት በማንቀሳቀስ እና ሕጻናትን ለውጊያ በመመልመል" ተሰማርቶ ቆይቷል ያሉት ደመቀ፣ አሁንም "መንግሥትን በሐሰት በመወንጀልና በማጥላላት እና የሐሰት የውጊያ ድል በመንዛት ስልቶች" ላይ ተጠምዷል በማለት ከሰዋል። ደመቀ በዚሁ ማብራሪያቸው፣ "አንዳንድ ወገኖች መንግሥትን እና ሕወሃትን በእኩል ዓይን ከማየት እና ግጭቱን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ" አሳስበዋል።

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
23 viewsedited  06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 07:33:30 በሆሮ ጉዱሩው ጥቃት ከ55 ሰዎች በላይ ተገደሉ

የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በቦምብ ጥቃት ጋይቷል


በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ አገምሳ ከተማ የታጠቁ አካላት በከፈቱት ተኩስ ቢያንስ ሲሉ የአይን እማኞች ተናገሩ፡፡የአከባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ለአንድ ዓመት ያህል አስከፊ የተባለ የፀጥታ ችግር ውስጥ በነበረበት በዚህ አከባቢ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በመደበኛነት ተመድበው የአከባቢውን ፀጥታ ሲያስከብሩ ነበር፡፡ ይሁንና ባለፈው እሁድ ነሃሴ 22 ቀን 2014 ዓ.ም. የአከባቢውን ፀጥታ ሲያስከብር የነበሩ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት ከከተማዋ መነሳታቸውን ተከትሎ የተለያዩ ስያሜ ያላቸው ታጣቂዎች በከተማዋ ባለፉት ቀናት መታየታቸውን ነው የአይን እማኞች የገለጹት፡፡

አቶ ንጉሴ ባንጃ የተባሉ የአይን እማኝ “እሁድ ማታ የኦሮምያ ልዩ ኃይል ለሌላ ግዳጅ ትፈለጋላችሁ ተብለው ከተማዋን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ መንግስት ‘ሸነ’ ያላቸው “የኦሮሞ ነጻነት ጦር” ሰኞ ጠዋቱን ገብተው ከተማዋን ተቆጣጠሩዋት፡፡”ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። የአይን እማኙ «ታጣቂዎቹ በከተማዋ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መንቀሳቀስ ከጀመሩ በኋላ ወደ 59 የጦር መሣሪያ ከማህበረሰቡ አስፈትተው በዚያው ሰኞ ቀን ከተማዋን ለቀው ወጥተዋል፡፡»ብለዋል

አቶ ንጉሴ አክለው በሰጡን አስተያየታቸው፤ “ትናንት ማክሰኞ ጠዋት ደግሞ ፋኖ ነን ያሉ የታጠቁ አካላት ወደ ከተማዋ ገብተው ከኦነግ ጋር አብራችኋል በሚል በመደዳው ከተማዋ ላይ ተኩስ በመክፈታቸው ከ15 ሺህ የማያንሱ የከተማዋ ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል” ነው ያሉት፡፡ ጥቃቱን ተከትሎ ከትናንት ማታ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ብቻ የ55 ሲቪል ዜጎች አስከሬን መቅበራቸውን የሚናገሩት እኚው አስተያየት ሰጪ “ ከማህበረሰቡ በአጠቃላይ የ87 ሰዎች ሕይወት የጠፉ በመሆኑ የ32 ሰዎች አስከሬን በየጫካውና በየገደሉ እየፈለግን ነው” ሲሉም የችግሩን ስፋት አስረድተዋል፡፡

አስተያየት ሰጪው እንደሚሉት ታጣቂዎቹ ከኪረሙ ወረዳ ሃሮ ቀበሌ የመጡ ናቸው፡፡ በትናንትናው የአገምሳ ከተማ ጥቃት ከጠፋው የሰው ህይወት በተጨማሪ በከተማዋ የሚገኝ የአዋሽ ባንክ በቦምብ ሲጋይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክን ጨምሮ በበርካታ የከተማዋ ተቋማት ላይ ዘረፋ ተፈጽሟል ብለዋል,።

አስተያየት ሰጪው ለፀጥታ ችግሩ መከሰት የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች አከባቢውን ለቀው የመውጣት ውሳኔን ተጠያቂ ያደርጋሉ። አስቀድሞም ከአንድ ዓመት በላይ በአከባቢው በቆየው የፀጥታ ችግር በርካታ ሰው በከተማዋ ተጠልለው እንዲቆዩ እንዳስገደዳቸው በመግለጽም፤ አሁን ላይ ግን በከተማዋ ላይ ባነጣጠረው ጥቃት ነዋሪዎች ወደየጫካው ነፍሳቸውን ለማዳን መሸሻቸው ነው የተብራራው፡፡

ሌላው አስተያየታቸውን ያጋሩን የከተማዋ ነዋሪና በመምህርነት ሙያ የተሰማሩት ቢቂላ ዓለሙ፤ በጸጥታ ችግር ምክኒያት ከየገጠር ቀበሌያት የተፈናቀሉ የተለያዩ የማህበረሰብ አካላት በዚሁ “የፋኖ ታጣቂዎች” ባሏቸው በተፈጸመው ጥቃት ከተማዋን ለቀው ተሰደዋል፡፡

ኒሞና ዴሬሳ የተባሉ አስተያየታቸውን የቀጠሉ ሌላው በመምህርነት ሙያ የሚተዳደሩ ነዋሪ እንዳሉት 20 አስከሬኖችን በአይናቸው አይተው ስማቸውንም መመዝገባቸውን አስረድተዋል፡፡ የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ መሆኑንም በመግለጽ፡፡

እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ ከ40 በላይ ቁስለኞች መታከሚያ ቦታ እንኳ አጥተው ‘አስከፊ’ ያሉት ችግር ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የነዋሪዎች ንብረት የሆኑ ከብቶችን ጨምሮ በርካታ ሃብት መዘረፋቸውንም አንስተዋል።

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የአሙሩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፋንታሁን ታዬ ስለሁኔታው ማብራሪያቸውን እንዲሰጡ ከዶይቼ ቬለ ለቀረበላቸው ጥያቄ ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ ሳይሰጡ፤ ከህበረተሰቡ ጋር በውይይት ላይ መሆናቸውንና ነገ መልስ እንደሚሰጡ አስረዱ፡፡


Via ዶይቼ ቬለ

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
97 viewsedited  04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 07:33:30 በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ የሚያደርጉባቸው የባንክ ሒሳብ ቁጥሮችን የገንዘብ ሚኒስቴር ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።

ኢትዮጵያውያኑ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር በግንባር እየተዋደቀ ለሚገኘው ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ የሚያደርጉባቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥሮችንም ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ መሰረት:-

~ ለዩሮ - 1000439142832 ፣

~ ለዶላር - 1000439142786 ፣

~ ለፓውንድ - 1000443606304 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሒሳብ ቁጥሮች ተዘጋጅተዋል።

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
86 viewsedited  04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 07:33:29
ጉባኤው በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲቆምና የሰላም ሂደቱ እንዲቀጥል ጥሪ

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲቆምና የሰላም ሂደቱ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበ።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፤ በመግለጫው የሰላም ቅድመ ሁኔታው ሰላም ብቻ በመሆኑ ጦርነቱን በማቆም ሰላማዊ ንግግሮች መቀጠል አለባቸው ብለዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ አሁንም የሰላም ጥሪ ማቅረባቸውን ገልጸዋል። በመሆኑም በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲቆምና የሰላም ጥረቱ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። የፌደራሉ መንግሥት ለሰላማዊ ንግግሮች ዝግጁ መሆኑን በተደጋጋሚ እንደገለጸው ሁሉ ሌሎችም ወገኖች ለዚሁ መልካም ተግባር ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።

የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማትና ንጹኃን ዜጎች ጥበቃ እንዲደረግላቸውም አሳስበዋል። ለወታደራዊ ዘመቻ ህፃናትን ማሰለፍ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል የሚያስጠይቅና በሁሉም መመዘኛ ተገቢ ባለመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል ያለው ኢዜአ ነው። በአገራዊ ጉዳይ በተለይ ወጣቶች ሁኔታውን በጥልቀት በማጤን ከስሜት በወጣ፣ ነፃና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ እንዲመረምሩ ጠይቀዋል።
  

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
92 viewsedited  04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 08:13:54
አቶ ጌታቸው ረዳ መሳሪያ ጭኖላቸው ሲገባ ስለተመታው አውሮፕላን በቁጭት ተናገሩ።

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
178 views05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:51:05
#Update

ቅዱስ ፓትርያርኩ ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን የሕክምና ክትትል በማጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ጤናቸውንም በተመለከተ የተወሰነ መሻሻል ማሳየቱ ታውቋል።

በመሆኑም ቀደም ሲል በተያዘው  የጉዞ መርሐ ግብር መሠረት ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
179 viewsedited  04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:51:04
የመጨረሻው የሶቪየት ህብረት መሪ ሚካሂል ጎርባቾቭ በ91 አመታቸው አረፉ

ኢንተርፋክስ ፣ TASS እና RIA Novosti የዜና ወኪሎች እንደዘገቡት በሞስኮ የሚገኘው ማዕከላዊ ክሊኒካል ሆስፒታል የነበሩት ጎርባቼቭ በከባድ እና ረዥም የኮቪድ 19 ህመም ከታመሙ በኋላ ትናንት ምሽት ማረፋቸውን ዘግበዋል ።

ጎርባቾቭ እ.ኤ.አ. ከ1985 ጀምሮ የሶቭየት ህብረትን እስከ ውድቀቷ 1991 ድረስ መርተዋል።
የቀዝቃዛው ጦርነት እንዲያቆም ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
165 viewsedited  04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:51:04
ሊትዌኒያ ከቤላሩስ ጋር የሚያዋስናት አደገኛ የሽቦ አጥር ስራን ጨረሰች

አጥሩ አራት ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን በላዩ ላይ የተገጠመ ሽቦ ያለው ነው። በዓመቱ መጨረሻ የቪዲዮ ካሜራዎች ይገጠሙበታል ። የአጥሩ ርዝመት 502 ኪሎ ሜትር ነው

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng
160 viewsedited  04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ