Get Mystery Box with random crypto!

ጉባኤው በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲቆምና የሰላም ሂደቱ እንዲቀጥል ጥሪ የ | Ertalepost ኤርታሌ ፖስት

ጉባኤው በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲቆምና የሰላም ሂደቱ እንዲቀጥል ጥሪ

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲቆምና የሰላም ሂደቱ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበ።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፤ በመግለጫው የሰላም ቅድመ ሁኔታው ሰላም ብቻ በመሆኑ ጦርነቱን በማቆም ሰላማዊ ንግግሮች መቀጠል አለባቸው ብለዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ አሁንም የሰላም ጥሪ ማቅረባቸውን ገልጸዋል። በመሆኑም በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲቆምና የሰላም ጥረቱ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። የፌደራሉ መንግሥት ለሰላማዊ ንግግሮች ዝግጁ መሆኑን በተደጋጋሚ እንደገለጸው ሁሉ ሌሎችም ወገኖች ለዚሁ መልካም ተግባር ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።

የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማትና ንጹኃን ዜጎች ጥበቃ እንዲደረግላቸውም አሳስበዋል። ለወታደራዊ ዘመቻ ህፃናትን ማሰለፍ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል የሚያስጠይቅና በሁሉም መመዘኛ ተገቢ ባለመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል ያለው ኢዜአ ነው። በአገራዊ ጉዳይ በተለይ ወጣቶች ሁኔታውን በጥልቀት በማጤን ከስሜት በወጣ፣ ነፃና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ እንዲመረምሩ ጠይቀዋል።
  

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP