Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር_ዜና የመከላከያ ሠራዊት፣ ኮማንዶ፣ ልዩ ኃይልና ፋኖ በጥምረት የቆቦን ከተማ መልሶ ተቆጣጠ | Ertalepost ኤርታሌ ፖስት

ሰበር_ዜና

የመከላከያ ሠራዊት፣ ኮማንዶ፣ ልዩ ኃይልና ፋኖ በጥምረት የቆቦን ከተማ መልሶ ተቆጣጠረ!

የአራቱንም ጥምር ምት መቋቋም የተሳነው የህወሓት ጀሌ ቆቦን ለቆ
ወደ አላማጣ ጉዞ ጀምሯል። እንደገና ዛሬ 4 ሰዓት አካባቢ በግዳን በኩል ለመግባት ሞክሮ አከርካሪውን ተመትቶ ተመልሷል።

-ዛሬ የተሰራው ኦፕሬሽን የሚደንው ነው። ኮማንዶዎች የወልዲያን ዩኒቨርስቲ መግቢያ በር፣ ወደ ባህርዳር የሚወስደውን መንገድ ማንም እንዳይገባና እንዳይወጣ ከዘጉ በኋላ ነው የቆቦ ኦፕሬሽን የተከናወነው። የምሥራቁ ኮከብ ፋኖ ምሬ ወዳጆ ከመከላከያና ከልዩ ኃይል ጎን ሆኖ የሰራው ጀብዱ ታሪክ የሚዘክረው ይሆናል።

-ሌላው የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ከዛሬ ጀምሮ የሚተገበር የሰዓት እላፊ ገደብ አስቀምጧል።
ከተመደበው የጸጥታ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ማንኛውም ሰው መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። ለጸጥታ ስራ ስምሪት ከተሰጠው ተሽከርካሪ ውጭ ማንኛውም ተሽከርካሪ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ የማይችል መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።

-በተመሳሳይ የደባርቅ ከተማ አስተዳደር
በከተማዋ የሚገኙ የተፈናቃይ መጠለያ ነዋሪ ከ12:00 በሗላ ወደ ውስጥም ሆነ ወደ ከተማ መግባት ከልክሏል። የከተማ ባጃጆች ከምሽቱ 1:00 በሗላ መንቀሳቀስ አይችሉም።

-አሁን ግምባር ላይ ያለው ወኔ፣ እልህና ቁጭት የሚገርም ነው። መከላከያ ነፍሱን እየሰጠ ነው፤ ልዩ ኃይሉ አጥንቱን እየከሰከሰ ነው፤ የምሥራቅ ዐማራ ፋኖ ደሙን እያፈሰሰ ይገኛል። ከኛ የሚጠበቀው ሞራል፣ ስንቅ፣ ደጀንነት ብቻ ነው።

-ነገርግን እዚህ የሚኖረው በስነልቦናው ስልብ የሆነው የፌስቡክ ጀሌ መከላከያን ያህል የሀገር ተቋም ሲሳደብ፣ ሲያንቋሽሽ፣ ሲሳለቅ ይውላል፥ ኧረ ሞራል ወዴት አለሽ? በምን ሞራል ነው ደሙን እያንጠባጠበ፣ ላቡን እያፈሰሰ፣ ሸለቆ ውስጥ አጥንቱን እየከሰከሰ ያለ ወታደር የሚሰደበው?
ቤተሰብ፣ ሃይማኖትና ትምህርት ቤት የሚባሉ ተቋማት ይህን ትውልድ እንዴት አድርገው አስተምረው ቢያሳድጉት ነው እንዲህ ያለ የተሳሳተ ትውልድ (wrong generation) የተፈጠረው?

በፊት መከላከያ የቅጥር ማስታወቂያ ሲያወጣ ተመዝገቡ፣ ዐማራ በልኩ ውክልና ያግኝ፣ ዘመናዊው መሳሪያዎችና ሥልጠናዎች የሚገኙት ከዚህ ተቋም ነው ስንል "አይሆንም" ብለው ሰፊ ዘመቻ ከፍተው የሚመዘገቡ ጠፍቶ ክልሉ የሚያስመዘግበው ሰው አጥቶ እንደነበር አስታውሳለሁ። የትናንቱ ረስተው ዛሬ ደግሞ በመከላከያ ተከዳን የሚል ትናንትና ውስጥ ይገኛሉ። አሁንም የምመክረው ወቀሳውን ከፖለቲካ አመራሩ ላይ አድርጉ እጃችሁን ከመከላከያ ላይ አንሱ!

-በጣም ያስገረመኝ ወያኔ ከጦርነቱ በፊት በድጅታል ሚዲያ ሊያግዛት የሚችል ይህን ያህል አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ግብረ ኃይል ታዘምትብናለች ብዬ በፍጹም አልጠበቅሁም ነበር።

የሆነው ሆኖ ባንዳ አንገቱን ደፍቶ ይቀራል የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ሠራዊት ድል ማድረጉን ይቀጥላል።

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng