Get Mystery Box with random crypto!

Ermi HD

የቴሌግራም ቻናል አርማ ermih — Ermi HD E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ermih — Ermi HD
የሰርጥ አድራሻ: @ermih
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.25K
የሰርጥ መግለጫ

This is the orginal chanal
Addmin✔✔(https://t.me/Ermi_HD)

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-16 10:34:25 ጌታችን የሞተው ስለ ስጋችን ወይስ ስለ ነብሳችን???
2.5K viewsËrmï HD, 07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 23:08:10 T
2.9K viewsËrmï HD, 20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 16:50:38 ሀጥያት ለቤተክርስትያን አባቶች ለምን እንናዘዛለን??
መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይላል ለቤተክርስትያን የሰጣት ስልጣንስ በትንሹ ምን ይመስላል????
ቤተ ክርስትያን የእውነት ሁሉ መገኛ ነች
1ኛ ጢሞቴዎስ 3
15፤ ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።
ቤተ ክርስትያን የክርስቶስ አካል ክርስቶስም የቤተ ክርስትያን ራስ ነው

ወደ ኤፌሶን 1
22፤ ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው።

23፤ እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት።

በቤተ ክርስትያን ያሉ ቅዱሳን ሁሉ ደግሞ የክርስቶስ ቤልቶች ናቸው

1ኛ ቆሮንቶስ 12
27፤ እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ እያንዳንዳችሁም ብልቶች ናችሁ።

ስለዚህም ክርስቶስ አካሉ በሆነች ቤተ ክርስትያን ውስጥ አካል በመሆን የሚገለግሉ ቅዱሳንን ስራውን ይሰራባቸዋል
ዛሬ ስለ ሀጥያት ስርየት ስልጣን እንዴት አካሉን እንደሚጠቀም እንይ
1ኛ ዮሐንስ 1
8፤ ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።

9፤ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።

ስለዚህ ሀጥያታችንን ስንናዘዝ ከሀጥያት በደሙ እንደሚያጦበን ይነግረናል ሀጥያትን ደግሞ ሰው ለሰው መናዘዝ እንዳለበት መፅሀፍ እንዲህ ይላል
የያዕቆብ መልእክት 5
14፤ ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።

15፤ የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል።

16፤ እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።

በተጨማሪም ክርስቶስ አካሉ ለሆኑ ቅዱሳን የመንግስተ ሰማያትን ቁልፍ ሰጥቶ የማሰርና የመፍታት ስልጣን ሰጥተአል
የማቴዎስ ወንጌል 16
19፤ የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።

ይህንንም በማያወላዳ መልኩ ስለ ሀጥያት ስርየት ለሀዋርያት የተሰጠ ስልጣን መሆኑን ይናገራል
የዮሐንስ ወንጌል 20
23፤ ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል፡ አላቸው።

ለዚ ነው በሀዋርያዊ ቅብብሎሽ በመልእክት ብቻ ሳይሆን በቃልም ሀዋርያትን እና የነሱን አምላክ ክርስቶስን አስተምሮ ተቀብላ 2ኛ ተሰሎንቄ 2
15፤ እንግዲያስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፥ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ።
የእውነት ሁሉ አምድና መገኛ የሆነችው ቤተ ክርስትያናችን ሀጥያትን ስለ መናዘዝ የምታስተምረው ለዚህ ነው

ብዙ ጥቅሞችም አሉት በመጀመርያ

1ኛ ዮሐንስ 4
20፤ ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ፥ እያለ ወንድሙን ቢጠላ፥ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?

ይህን ቃል ወስደን እኛ በሰው ፊት የማናደርገውን በእግዚአብሄር ፊት ደግሞ ለመስራት ደፍረናልና ለሰዎች ስንናገር ሀጥያቱን ድጋሚ ላለመስራት እንሞክራለን ከሰራን ግን እግዚአብሄርን ፈርተን የግድ ለሰዎች መናዘዝ ስላለብን ሀጥያትን የመለማመድ እድላችን ይቀንሳል።

ሌላው ደግሞ ከሀጥያት እንዴት መመለስ እንዳለብን ምክር እናገኛለን

ፀሎትን ስለኛ ያደርጉልናል በፀሎት ያግዙናል
የያዕቆብ መልእክት 5
14፤ ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።

ወደ ሀጥያት እንዳንመለስ ሰይጣንን የምናሸንፍበትን መሳርያ (ፆም እና ፀሎት) ያስታጥቁናል

የማቴዎስ ወንጌል 17
21፤ ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም፡ አላቸው።

የፃፍኩት ጌታዬና መዳኒቴ ክርስቶስ ኢየሱስ በረዳኝ ልክ ነው ምናልባትም የኔ ደካማነት ጌታ ከዚ በላይ እኔን እንዳይጠቀም አድርጎም ይሆናል

ግልፅ ያልሆነ ነገር ኬለ ጠይቁ @ermi_hd

2ኛ ቆሮንቶስ 9
15፤ ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን። በ @ermi_hd የተሰጠ መልስ
3.6K viewsËrmï HD, 13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-07 21:51:40 Ermi HD pinned « ስእለ አድኖ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ነውን? ኪሩብ ማለት እኮ ኪሩቤል ማለት ነው ዘፀአት25፣18 ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፥ በስርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ። 20 ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘረጋሉ፥ የስርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፥ ፊታቸውም እርስ በርሱ ይተያያል፤ የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ ስርየት መክደኛው ይመለከታሉ። ያው ኪሩብ ኪሩቤል ማለት ነው የመላእክት…»
18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-07 09:55:48 ስእለ አድኖ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ነውን? ኪሩብ ማለት እኮ ኪሩቤል ማለት ነው ዘፀአት25፣18 ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፥ በስርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ። 20 ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘረጋሉ፥ የስርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፥ ፊታቸውም እርስ በርሱ ይተያያል፤ የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ ስርየት መክደኛው ይመለከታሉ። ያው ኪሩብ ኪሩቤል ማለት ነው የመላእክት ስም ነው ጌታ እራሱ ለሙሴ እያዘዘው ነው ከታቦቱ ጋር የ መላእክት ምስል እንዲሰራ በተጨማሪም
1ኛ ነገስት6፣23 በቅድስተ ቅዱሳኑም ውስጥ ቁመታቸው አሥር ክንድ የሆነ ከወይራ እንጨት ሁለት ኪሩቤል ሠራ።
29 በቤቱም ግንብ ሁሉ ዙሪያ በውስጥና በውጭ የኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸ።
ህዝቅኤል4፣1 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ጡብን ወስደህ በፊትህ አኑራት የኢየሩሳሌምንም ከተማ ስዕል ሳልባት ክበባት፥
ያው ከመፅሀፍ ቅዱስ እናሳይ ተብሎ እንጂ መፅሀፍ ቅዱስ ብቻ የሚል አስተምሮ እራሱ መፅሀፍ ቅዱሳዊ አይደለም ማስረጃውም ራሱ መፅሀፍ ቅዱስ ነው 2ጢሞ 3፣16-17 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።
2ኛ ተሰሎንቄ 2፣15 እንግዲያስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፥ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ። 2 ወንድሞች ሆይ፥ በሁሉ ስለምታስቡኝና አሳልፌ እንደ ሰጠኋችሁ ወግን ፈጽማችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ። ወግ ወይም ቱፊት ደግሞ የሚተላለፈው ከአባት ወደ ልጅ ከትውልድም ወደ ትውልድ ነው ስለዚህም ነው ነባር የሚባሉት ክርስትናዎች (ካቶሊክ እና ኦርቶዶክስ) ስእል የሚጠቀሙት ለምሳሌ በታሪክ (በወግ) የእናትና ልጁን ስእለ አድኖ ሀዋርያው ቅዱስ ሉቃስ እንደሳለው ይታወቃል
ጣኦቶች እና ስእሎች ከጥንት በአህዛብ የሚመለኩ እስራኤላውያንም እግዚአብሄርን የሚያስቆጣ ጣኦት ይሰራሉ እግዚአብሄርም ይቆጣ ነበር
ዘፀአት 32፣4 ከእጃቸውም ተቀብሎ በመቅረጫ ቀረጸው፥ ቀልጦ የተሠራ ጥጃም አደረገው፤ እርሱም፡— እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው፡ አላቸው።
ስለነዚህም ስለሚያመልኩአቸው ጣኦቶች እግዚአብሄር እንዲህ ይላል
ዘፀአት 20፣በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።

5 አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤
በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
የሐዋርያት ሥራ 17
29፤ እንግዲህ የእግዚአብሔር ዘመዶች ከሆንን፥ አምላክ በሰው ብልሃትና አሳብ የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ እንዲመስል እናስብ ዘንድ አይገባንም።
ይቺን ጥቅስም ለክርስትያኖች የተሰጠ ማስጠንቀቂያ አድርገው ይጠቀሙባታል ይህ ግን የተፃፈው ለማን እንደሆነ ለማወቅ ከፍ ብሎ ማየት ነው
የሐዋርያት ሥራ 17
16፤ ጳውሎስም በአቴና ሲጠብቃቸው ሳለ፥ በከተማው ጣዖት መሙላቱን እየተመለከተ መንፈሱ ተበሳጨበት።

ይሄ የተፃፈው አምላካቸውን ለማያውቁ ጣኦት አምላኪዎች ነው እሱንም አምላክ ብለው ለያዙት ነው

ምስኪን እና አለማወቃቸውን የማያውቁ ወገኖቻችን ግይ ይህን እግዚአብሄርን ለሚያስቆጡ እና ለሚመለኩ ጣኦቶች እንዳያመልኩ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ እግዚአብሄር እራሱ ላዘዘውና ነብያት እንዲሁም ሀዋርያት ለሰሩት በመፅሀፍ ቅዱስና በቱፊት ማስረጃ ላላቸው ስእለ አድኖ ማስጠንቀቂያ ይጠቀሙበታል


ይህም ችግር መፅሀፍ ቅዱስን ካለማወቅና 1ጥቅስ ብቻ ከመያዝ የሚመጣ ነው ያለዚያማ እግዚአብሄርን ራሱ የሚጋጅ ነገር ይናገራል ብሎም ውሸታም እንደማድረግ ነው
ለምሳሌ ዘፀአት20፣4-5 እግዚአብሄር ምንም አይነት ምስል እንዳይስል እንዳይቀርፅ ለራሱም እንዳያደርግ ይናገራል እዛው ዘፀአት 25፣18-20 ደግሞ የመላእክቱን ኪሩቤል ምስል እንዳቀርፅ ያዝዛል
ይህን ቃል በደፈናው የመፅሀፍ ቅዱስ ግጭት የማመስል ነገር ግን መፅሀፍን ካለማወቅና ልክ ከላይ እንደፃፍኩት የቱ እንደተከለከለና የቱ እንደታዘዘ ካለማወቅ የሚመጣ የአእምሮ ግጭት ነው
ያው ጥቂቱን ነው የነገርኩሽ ከማውቀው በጎደለው ጌታ ኢየሱስ ይሙላበት ከነገርኩሽ ግን ግር ያለሽ ነገር ካለ ጠይቂኝ
ስለ ስእለ አድኖ ግልፅ ከሆነ ወደ ቀጣዩ ጥያቄሽ እንግባ በ ኤርሚያስ የተሰጠ ምላሽ ለ ጥያቂ እና አስተያየት @ermi_hd
2.9K viewsËrmï HD, 06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 21:38:40 ለቅዱሳን መዘመር ተገቢ ነውን? መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይላል??
ፈጣሪ እንደ ልቤ ያለው ዳዊት የልቤን ማን እንደነገረው እንጃ የእኔን ጥያቄ ለመመለስ ቸኩሎ ጠበቀኝ፡፡ ገና የመጀመሪያው መዝሙሩን ‹‹ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሔደ ፣ በኃጢአተኞች መንገድ ያልቆመ ፣ በዋዘኞች ወንበር ያልተቀመጠ›› ብሎ ጀምሮት አገኘሁት፡፡ (መዝ. 1፡1) ዳዊት በዚህ ዝማሬው ‹ምስጉን ነው› ያለው ፈጣሪን ነው ወይንስ ፍጡርን? እግዚአብሔርን ነው እንዳልል ‹በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል› ይላል፡፡ ስለዚህ ዳዊት ዝማሬውን የጀመረው ‹በክፉዎች ምክር ያልሔደ ፣ በኃጢአተኞች መንገድ ያልቆመ ፣ በዋዘኞች ወንበር ያልተቀመጠ›ን ሰው በማመስገን ነው፡፡

ወደ መዝሙሩ ስገባ ዳዊት ምስጋናውን ሰፋ አድርጎ ‹ለቅኖች ምስጋና ይገባቸዋል› ‹ለችግረኛ የሚያስብ ምስጉን ነው› ‹አንተ የመረጥከው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልከው ምስጉን ነው› ‹እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ ምስጉን ነው› ‹እልልታን የሚያውቅ ሕዝብ ምስጉን ነው› ብሎ ከግለሰቦች አልፎ ሕዝብን ሲያመሰግን አገኘሁት፡፡ ከሁሉ ያስደነቀኝ ግን ‹‹መተላለፉ የቀረችለት ፣ ኃጢአቱ የተከደነችለት ሰው ምስጉን ነው›› የሚለው ዝማሬው ነው፡፡ ኃጢአቱን እግዚአብሔር ይቅር ያለውና በደሉን ፈጣሪ የሸፈነለት ሰው በታላቁ ዘማሪ በዳዊት አንደበት መዝሙር ከተዘመረለት በሃሳብዋ እንኳን ኃጢአትን ስላልሠራችው ድንግል ምን ዓይነት መዝሙር ይዘመርላት ይሆን?

ንጉሥ ዳዊት ሕይወት ላላቸው ሰዎች ብቻ ዘምሮ አላቆመም ፤ ለማትናገረውና ከእንጨት ከድንጋይ በሰው እጅ ለተሠራችው ከተማው ለጽዮን የእግዚአብሔር ማደሪያ በመሆንዋ ዝማሬን አዝንሞላታል፡፡
‹‹እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታል ፤ ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወድዷታል፡፡ እንዲህ ሲል ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት ፣ መርጫታለሁና በእርስዋ አድራለሁ››
‹‹እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል ፤ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የከበረ ነገር ይባላል››
‹‹በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን ፤ ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን ፤ የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን ፤ የእግዚአብሔርን ዝማሬ እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምራለን? ኢየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ፤ ባላስብሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ጋር ይጣበቅ ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ›› ብሎ ስለ ቅድስቲቱ ከተማ ሲዘምር አገኘሁት፡፡ ከራሱ አልፎም በዙሪያው ላሉት በመዝሙሩ እንዲህ ሲል ጥሪ አቀረበ ‹‹መዝሙረ ዳዊት 48
12፤ ጽዮንን ክበቡአት፥
በዙሪያዋም ተመላለሱ፥
ግንቦችዋንም ቍጠሩ፤ ›› የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮንን ለማይወድዱ ደግሞ በመዝሙሩ ‹‹መዝሙረ ዳዊት 129
5፤ ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥
ወደ ኋላቸውም ይመለሱ። ›› ብሎ ዘምሮአል፡፡

ዳዊት ስንት ኃጢአተኛ ሲራኮት ለሚውልና ለሚያድርባት ከተማ የእግዚአብሔር ማደሪያው እንድትሆን እንደ መረጣት አውቆ እንዲህ ሲዘምር ማየቴ ‹መንፈስ ቅዱስ ይጸልልሻል የልዑል ኃይልም ያድርብሻል› ለተባለችዋ ቅድስት ድንግል ማርያም ‹የጌታዬ እናት ፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ፣ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ› ብዬ ለመዘመር እንድችል ኃይል የሚሠጥ ሆነልኝ፡፡ ባቢሎን በተባለ በኃጢአት ሥፍራ ሆኜ ድንግልን ባሰብኳት ጊዜ እንዳለቅስና ‹‹ድንግል ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ባላስብሽም ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ›› ብዬ እንድዘምርላት ድፍረት ሠጠኝ
2.5K viewsËrmï HD, 18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 21:32:48 የአጋንንት አሰራር እና ወጥመድ እንዲሁም የመንፈስ ቅዱስ መፍትሄ
በ @ermi_hd የተሰጠ መልስ
1.8K viewsËrmï HD, 18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-20 19:13:56
ሮሜ 8፣34 ኢየሱስ አማላጅ ነው አይልም ከመፅሀፍ ቅዱስ የማያወላዳ መልስ ከ @ermi_hd
1.8K viewsËrmï HD, 16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ