Get Mystery Box with random crypto!

ስእለ አድኖ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ነውን? ኪሩብ ማለት እኮ ኪሩቤል ማለት ነው ዘፀአት25፣18 ሁለት | Ermi HD

ስእለ አድኖ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ነውን? ኪሩብ ማለት እኮ ኪሩቤል ማለት ነው ዘፀአት25፣18 ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፥ በስርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ። 20 ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘረጋሉ፥ የስርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፥ ፊታቸውም እርስ በርሱ ይተያያል፤ የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ ስርየት መክደኛው ይመለከታሉ። ያው ኪሩብ ኪሩቤል ማለት ነው የመላእክት ስም ነው ጌታ እራሱ ለሙሴ እያዘዘው ነው ከታቦቱ ጋር የ መላእክት ምስል እንዲሰራ በተጨማሪም
1ኛ ነገስት6፣23 በቅድስተ ቅዱሳኑም ውስጥ ቁመታቸው አሥር ክንድ የሆነ ከወይራ እንጨት ሁለት ኪሩቤል ሠራ።
29 በቤቱም ግንብ ሁሉ ዙሪያ በውስጥና በውጭ የኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸ።
ህዝቅኤል4፣1 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ጡብን ወስደህ በፊትህ አኑራት የኢየሩሳሌምንም ከተማ ስዕል ሳልባት ክበባት፥
ያው ከመፅሀፍ ቅዱስ እናሳይ ተብሎ እንጂ መፅሀፍ ቅዱስ ብቻ የሚል አስተምሮ እራሱ መፅሀፍ ቅዱሳዊ አይደለም ማስረጃውም ራሱ መፅሀፍ ቅዱስ ነው 2ጢሞ 3፣16-17 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።
2ኛ ተሰሎንቄ 2፣15 እንግዲያስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፥ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ። 2 ወንድሞች ሆይ፥ በሁሉ ስለምታስቡኝና አሳልፌ እንደ ሰጠኋችሁ ወግን ፈጽማችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ። ወግ ወይም ቱፊት ደግሞ የሚተላለፈው ከአባት ወደ ልጅ ከትውልድም ወደ ትውልድ ነው ስለዚህም ነው ነባር የሚባሉት ክርስትናዎች (ካቶሊክ እና ኦርቶዶክስ) ስእል የሚጠቀሙት ለምሳሌ በታሪክ (በወግ) የእናትና ልጁን ስእለ አድኖ ሀዋርያው ቅዱስ ሉቃስ እንደሳለው ይታወቃል
ጣኦቶች እና ስእሎች ከጥንት በአህዛብ የሚመለኩ እስራኤላውያንም እግዚአብሄርን የሚያስቆጣ ጣኦት ይሰራሉ እግዚአብሄርም ይቆጣ ነበር
ዘፀአት 32፣4 ከእጃቸውም ተቀብሎ በመቅረጫ ቀረጸው፥ ቀልጦ የተሠራ ጥጃም አደረገው፤ እርሱም፡— እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው፡ አላቸው።
ስለነዚህም ስለሚያመልኩአቸው ጣኦቶች እግዚአብሄር እንዲህ ይላል
ዘፀአት 20፣በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።

5 አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤
በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
የሐዋርያት ሥራ 17
29፤ እንግዲህ የእግዚአብሔር ዘመዶች ከሆንን፥ አምላክ በሰው ብልሃትና አሳብ የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ እንዲመስል እናስብ ዘንድ አይገባንም።
ይቺን ጥቅስም ለክርስትያኖች የተሰጠ ማስጠንቀቂያ አድርገው ይጠቀሙባታል ይህ ግን የተፃፈው ለማን እንደሆነ ለማወቅ ከፍ ብሎ ማየት ነው
የሐዋርያት ሥራ 17
16፤ ጳውሎስም በአቴና ሲጠብቃቸው ሳለ፥ በከተማው ጣዖት መሙላቱን እየተመለከተ መንፈሱ ተበሳጨበት።

ይሄ የተፃፈው አምላካቸውን ለማያውቁ ጣኦት አምላኪዎች ነው እሱንም አምላክ ብለው ለያዙት ነው

ምስኪን እና አለማወቃቸውን የማያውቁ ወገኖቻችን ግይ ይህን እግዚአብሄርን ለሚያስቆጡ እና ለሚመለኩ ጣኦቶች እንዳያመልኩ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ እግዚአብሄር እራሱ ላዘዘውና ነብያት እንዲሁም ሀዋርያት ለሰሩት በመፅሀፍ ቅዱስና በቱፊት ማስረጃ ላላቸው ስእለ አድኖ ማስጠንቀቂያ ይጠቀሙበታል


ይህም ችግር መፅሀፍ ቅዱስን ካለማወቅና 1ጥቅስ ብቻ ከመያዝ የሚመጣ ነው ያለዚያማ እግዚአብሄርን ራሱ የሚጋጅ ነገር ይናገራል ብሎም ውሸታም እንደማድረግ ነው
ለምሳሌ ዘፀአት20፣4-5 እግዚአብሄር ምንም አይነት ምስል እንዳይስል እንዳይቀርፅ ለራሱም እንዳያደርግ ይናገራል እዛው ዘፀአት 25፣18-20 ደግሞ የመላእክቱን ኪሩቤል ምስል እንዳቀርፅ ያዝዛል
ይህን ቃል በደፈናው የመፅሀፍ ቅዱስ ግጭት የማመስል ነገር ግን መፅሀፍን ካለማወቅና ልክ ከላይ እንደፃፍኩት የቱ እንደተከለከለና የቱ እንደታዘዘ ካለማወቅ የሚመጣ የአእምሮ ግጭት ነው
ያው ጥቂቱን ነው የነገርኩሽ ከማውቀው በጎደለው ጌታ ኢየሱስ ይሙላበት ከነገርኩሽ ግን ግር ያለሽ ነገር ካለ ጠይቂኝ
ስለ ስእለ አድኖ ግልፅ ከሆነ ወደ ቀጣዩ ጥያቄሽ እንግባ በ ኤርሚያስ የተሰጠ ምላሽ ለ ጥያቂ እና አስተያየት @ermi_hd