Get Mystery Box with random crypto!

ሀጥያት ለቤተክርስትያን አባቶች ለምን እንናዘዛለን?? መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይላል ለቤተክርስትያን የሰ | Ermi HD

ሀጥያት ለቤተክርስትያን አባቶች ለምን እንናዘዛለን??
መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይላል ለቤተክርስትያን የሰጣት ስልጣንስ በትንሹ ምን ይመስላል????
ቤተ ክርስትያን የእውነት ሁሉ መገኛ ነች
1ኛ ጢሞቴዎስ 3
15፤ ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።
ቤተ ክርስትያን የክርስቶስ አካል ክርስቶስም የቤተ ክርስትያን ራስ ነው

ወደ ኤፌሶን 1
22፤ ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው።

23፤ እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት።

በቤተ ክርስትያን ያሉ ቅዱሳን ሁሉ ደግሞ የክርስቶስ ቤልቶች ናቸው

1ኛ ቆሮንቶስ 12
27፤ እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ እያንዳንዳችሁም ብልቶች ናችሁ።

ስለዚህም ክርስቶስ አካሉ በሆነች ቤተ ክርስትያን ውስጥ አካል በመሆን የሚገለግሉ ቅዱሳንን ስራውን ይሰራባቸዋል
ዛሬ ስለ ሀጥያት ስርየት ስልጣን እንዴት አካሉን እንደሚጠቀም እንይ
1ኛ ዮሐንስ 1
8፤ ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።

9፤ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።

ስለዚህ ሀጥያታችንን ስንናዘዝ ከሀጥያት በደሙ እንደሚያጦበን ይነግረናል ሀጥያትን ደግሞ ሰው ለሰው መናዘዝ እንዳለበት መፅሀፍ እንዲህ ይላል
የያዕቆብ መልእክት 5
14፤ ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።

15፤ የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል።

16፤ እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።

በተጨማሪም ክርስቶስ አካሉ ለሆኑ ቅዱሳን የመንግስተ ሰማያትን ቁልፍ ሰጥቶ የማሰርና የመፍታት ስልጣን ሰጥተአል
የማቴዎስ ወንጌል 16
19፤ የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።

ይህንንም በማያወላዳ መልኩ ስለ ሀጥያት ስርየት ለሀዋርያት የተሰጠ ስልጣን መሆኑን ይናገራል
የዮሐንስ ወንጌል 20
23፤ ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል፡ አላቸው።

ለዚ ነው በሀዋርያዊ ቅብብሎሽ በመልእክት ብቻ ሳይሆን በቃልም ሀዋርያትን እና የነሱን አምላክ ክርስቶስን አስተምሮ ተቀብላ 2ኛ ተሰሎንቄ 2
15፤ እንግዲያስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፥ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ።
የእውነት ሁሉ አምድና መገኛ የሆነችው ቤተ ክርስትያናችን ሀጥያትን ስለ መናዘዝ የምታስተምረው ለዚህ ነው

ብዙ ጥቅሞችም አሉት በመጀመርያ

1ኛ ዮሐንስ 4
20፤ ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ፥ እያለ ወንድሙን ቢጠላ፥ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?

ይህን ቃል ወስደን እኛ በሰው ፊት የማናደርገውን በእግዚአብሄር ፊት ደግሞ ለመስራት ደፍረናልና ለሰዎች ስንናገር ሀጥያቱን ድጋሚ ላለመስራት እንሞክራለን ከሰራን ግን እግዚአብሄርን ፈርተን የግድ ለሰዎች መናዘዝ ስላለብን ሀጥያትን የመለማመድ እድላችን ይቀንሳል።

ሌላው ደግሞ ከሀጥያት እንዴት መመለስ እንዳለብን ምክር እናገኛለን

ፀሎትን ስለኛ ያደርጉልናል በፀሎት ያግዙናል
የያዕቆብ መልእክት 5
14፤ ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።

ወደ ሀጥያት እንዳንመለስ ሰይጣንን የምናሸንፍበትን መሳርያ (ፆም እና ፀሎት) ያስታጥቁናል

የማቴዎስ ወንጌል 17
21፤ ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም፡ አላቸው።

የፃፍኩት ጌታዬና መዳኒቴ ክርስቶስ ኢየሱስ በረዳኝ ልክ ነው ምናልባትም የኔ ደካማነት ጌታ ከዚ በላይ እኔን እንዳይጠቀም አድርጎም ይሆናል

ግልፅ ያልሆነ ነገር ኬለ ጠይቁ @ermi_hd

2ኛ ቆሮንቶስ 9
15፤ ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን። በ @ermi_hd የተሰጠ መልስ