Get Mystery Box with random crypto!

ያሬዳውያን

የቴሌግራም ቻናል አርማ eotcmahlet — ያሬዳውያን
የቴሌግራም ቻናል አርማ eotcmahlet — ያሬዳውያን
የሰርጥ አድራሻ: @eotcmahlet
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.48K
የሰርጥ መግለጫ

የየበዓላቱ ስርአተ #ዋዜማ ፤ #ማህሌት ፤ #ወረብ ከ7 ቀናት እንዲሁም የየሳምንቱ መዝሙራት እና ምስባክ በጽሑፍ እና በድምጽ የሚቀርቡበት ቻናል ነው
#ሁሉም_ነገር_ስለ_ማህሌት
ማህሌታውያን ቻናሉን share ያርጉ
ጥያቄ አስተያየት በግሩፓችን ይላኩ 🙏
እናመሰግናለን

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-15 16:54:42 ሥርዓተ ማኅሌት ዘትንሣኤ ደወል እንደተደወለ ከሁሉ አስቀድሞ ነቢያት ተደግሞ ውዳሴ ማርያም በዜማ ይደርሳል። @EOTCmahlet "ተፈሥሂ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ" ይባላል። መልክአ ስዕል አይባልም። @EOTCmahlet ከዚያም ተአምረ ማርያም እና ተአምረ ኢየሱስ ይነበባል። ቀጥሎም ወተንሥአ ይሰበክና ከአራቱ ወንጌላት 3ቱ ተነበው "አርያም"…
6.1K views13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 08:12:55
ሥርዓተ ማኅሌት ዘትንሣኤ


ደወል እንደተደወለ ከሁሉ አስቀድሞ ነቢያት ተደግሞ ውዳሴ ማርያም በዜማ ይደርሳል።
@EOTCmahlet
"ተፈሥሂ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ" ይባላል። መልክአ ስዕል አይባልም።
@EOTCmahlet
ከዚያም ተአምረ ማርያም እና ተአምረ ኢየሱስ ይነበባል። ቀጥሎም ወተንሥአ ይሰበክና ከአራቱ ወንጌላት 3ቱ ተነበው "አርያም" በተባለው ምስጋና ማኅሌቱ ይጀመራል።
@EOTCmahlet
ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፸፯ : ፷፭

ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም፤
ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን፤
ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ።

@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
አርያም፦
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ ቀዳሚ ዜማ ግበሩ በዓለ በትፍሥሕት እስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ፤ ዛቲ ፋሲካ ቀዳሚት ሕግ።
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ ይገብሩ በዓለ ሰማያት፤ ይገብሩ በዓለ ደመናት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ምልጣን፦
ዮም ፍሥሃ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን፤ እስመ ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን፤ ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል አልዓላ፤ አማን ተንሥአ እምነ ሙታን።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
'አማን በአማን'/፪/ ተንሥአ 'አማን በአማን'/፪//፩/
ተንሥአ እምነ ሙታን/፬/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን/፪/
ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል/፪/
@EOTCmahlet
እስመ ለዓለም፦
ትንሣኤከ ለእለ አመነ፤ ብርሃንከ ፈኑ ዲቤነ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
ትንሣኤከ ለእለ አመነ/፪/
ፈኑ ዲቤነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ/፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ከእስመ ለዓለሙ ጋር ተያይዞ ሰላም ይፃፋል
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ሰላም፦
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ይእቲ ማርያም እምነ፤ ወእሙ ለእግዚእነ፤ ሰአሊ በእንቲአነ፤ ከመ ይምሐረነ ወይሣሐለነ፤ ያስተርኢ ኂሮቶ ላዕሌነ፤ ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ ፍሥሐ ወሰላም ለእለ አመነ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
ሠርዓ ለነ ሰንበት ለዕረፍተ ዚአነ/፪/
ፍሥሐ ወሰላም ለእለ አመነ/፬/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ኪዳንን ከተደረሰ በኃላ
መዝሙር በ፩፦
ሃሌ ሉያ ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትኃሠይ ምድር፤ ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ፤ ወይወውኡ አድባር ወአውግር፤ ወኲሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዓባይ ፍሥሐ በሰማያት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ፤/2/
ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ/4/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ሰላም
ፍጹመ ንጉሠ ኮነንዎ አይሁድ፤ ተካፈሉ አልባሲሁ ሐራ ሠገራት፤ ወኮርዕዎ ርእሶ በኅለት፤ ረገዝዎ ገቦሁ በኲናት፤ ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት፤ ሰላመ ይጸጉ ለነገሥት፤ ለአሕዛብ ወለበሐውርት።


ከዚህ በኃላ ወደ ስርዓተ ቅዳሴ



@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet


@EOTCmahlet
#Join & share #
1.7K views05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 08:12:35 @Memhir_sirak
1.6K views05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 19:28:49 እንኳን አደረሳችሁ
3.7K views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 13:44:57 ሐሙስ
1.ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፦
ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።

2.ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል።

3. የምስጢር ቀን ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።

4. የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡-
መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።

5. የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡-
ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።


@EOTCmahlet                  
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet


      @EOTCmahlet
    #Join & share
1.1K views10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 12:05:39 በያሬዳውያን በኛው ቻናል ውስጥ ለትምህርት አገልግሎት የተከፈተ ቻናል ነው ጆይን በሉ ሼር አድርጉ
@eotcwengel



@eotcwengel
@eotcwengel @eotcwengel @eotcwengel
ሠናይ ሰሙነ ሕምማት ይኩን ለኩልነ
1.4K viewsedited  09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 10:29:25 ረቡዕ
1.ምክረ አይሁድ ይባላል፦
ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል።

2. የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል።

3.የእንባ ቀን ይባላል፡-
ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል።


@EOTCmahlet                  
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet


      @EOTCmahlet
    #Join & share
3.9K viewsedited  07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 14:14:26 ማክሰኞ

1. የጥያቄ ቀን ይባላል
ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።

2.የትምህርት ቀን ይባላል፡-
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።


@EOTCmahlet                  
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet


      @EOTCmahlet
    #Join & share #
5.1K views11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 08:31:56 ሰኞ

1. መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል።

2.አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ይባላል፡
ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና።


@EOTCmahlet                  
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet


      @EOTCmahlet
    #Join & share #
1.4K views05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 07:29:27 ​​​​​​በሰሞነ ሕማማት የሚጸለዩት እና የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?

#ሼር በማድረግ ለሌሎችም አሳውቁ

በሰሞነ ሕማማት የምንጸልያቸው ጸሎቶች
የትኞቹ ናቸው?

➦በሰሞነ ሕማማት አጥብቀን የምንጸልያቸው ጸሎቶች ውዳሴ ማርያም:ዳዊት: ሰይፈ ሥላሴ:ሰይፈ መለኮት:ድርሳነ ማሕየዊ ውዳሴ አምላክ ናቸው።

➦እመቤታችን ድንግል ማርያም በዚህ በሰሞነ ሕማም በልጅዋ ምክንያት ብዙ እንግልት ስለደረሰባት የእሷን ምስጋና የሆነውን ውዳሴ ማርያም አናስታጉልም። ውዳሴ ማርያም ማመስገኛ መማጸኛ ስለሆነ እንጸልያለን። ምክንያቱም በዚህ በሰሞነ ሕማማት መከራ ተቀብሎ ሞቶ ሕይወቱን የሰጠንን ጌታ በሥጋ ወልዳለችን በውዳሴዋ እናስባታለን።

➦የቅዱስ ዳዊት ድርሰት የሆነው ታላቁ መዝሙረ ዳዊት በትንቢት ክፍሉ ስለ ጌታችን ሕማም ስቃይ እና ሞት የሚናገርና በዳዊት ምስጋና በምድር የሰው ልጆች በሰማይ ቅዱሳን መላእክት ስለሚያመሰግኑ እንጸልየዋለን።

➦ሰይፈ ሥላሴ ከሦስቱ አካላት እግዚአብሔር ወልድን የሚያመሰግን አምላክነቱን የሚመሰክር እና የሚመሰጥር በመሆኑ እንጸልየዋለን።

➦ሰይፈ መለኮት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ስለ ምስጢረ መለኮት እና ስለ ጌታችን አምላክነት ስለሚናገር እንጸልየዋለን።

➦ድርሳነ ማሕየዊ በቅዱስ ዮሐንስ ወልደ-ነጎድጓድ የዓይን እማኝነት እና የቃል ምስክርነት የተጻፈና የጌታችንን መከራ ስቃይ እንግልት እና ሞት በልዩ ሁኔታ የሚናገር በመሆኑ ልክ እንደ ውዳሴ ማርየም የየእለት/የየቀን ስላለው ብንጸልየው በዓይነ ሕሊና ቀራንዮ ወሰዶ በነፍሳችን የጌታችንን ሰማያዊ ውለታ የሚስልብንና በመጸለያችን ልዩ ጸጋና ክብር የሚያሰጥ የቃል-ኪዳን ጸሎት በመሆኑ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ብንጸልየው እጅጉን እንጠቀምበታለን። ውዳሴ አምላክም የጌታችን ምስጋና በመሆኑ መጸለይ እንችላለን።

በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?

➦በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩትን ጸሎቶች ጠቅለል አድርገን ስናያቸው ድርሳናት ገድላት እና መልካ መልኮች ናቸው። ይህም የሆነው በሰሞነ ሕማማት ጌታችን ለእኛ ለሰው ልጆች ብሎ የተቀበላቸውን ስቃይ እና መከራ ሞት የምናስብበት እና የምናለቅስበት እንጂ ሌሎቹን በድርሳናቸው በገድላቸው በመልካቸው የምናመሰግንበት ጊዜ ስላልሆነ ነው።

➦በተረፈ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ለራሳችሁ ለሀገራችሁ ብቻ አትጸልዩ ለዓለም ሕዝብ ለአሕዛብ በሙሉ ጸልዩ። ምክንያቱም ለእነሱ የመጣ ሰማያዊ ቁጣ በቀጥታም በተዘዋዋሪም ለእኛም ይተርፋልና። እነሱ ሲለበለቡ እኛ መቃጠላችን እነሱ ሲሰበሩ እኛ ወለም ማለታችን እነሱ ሲሞቱ ሞት ደጃፋችን መቆምን በማሰብ ለእነሱም እንጸልይ። የእነሱ መከራ ሲርቅ ነው የኛም የሚርቀው።
✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞

#ምንተስኖት ሁንዴ
1.7K views04:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ