Get Mystery Box with random crypto!

ያሬዳውያን

የቴሌግራም ቻናል አርማ eotcmahlet — ያሬዳውያን
የቴሌግራም ቻናል አርማ eotcmahlet — ያሬዳውያን
የሰርጥ አድራሻ: @eotcmahlet
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.48K
የሰርጥ መግለጫ

የየበዓላቱ ስርአተ #ዋዜማ ፤ #ማህሌት ፤ #ወረብ ከ7 ቀናት እንዲሁም የየሳምንቱ መዝሙራት እና ምስባክ በጽሑፍ እና በድምጽ የሚቀርቡበት ቻናል ነው
#ሁሉም_ነገር_ስለ_ማህሌት
ማህሌታውያን ቻናሉን share ያርጉ
ጥያቄ አስተያየት በግሩፓችን ይላኩ 🙏
እናመሰግናለን

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-12 17:33:48
ሥርዓተ ማኅሌት ዘግንቦት ቅዱስ ያሬድ

"ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ነግሥ
ሰላም ለአብ ገባሬ ኲሉ ዓለም፤ ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤ ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ዜኖኩ ጽድቀከ ወነገርኩ አድኅኖተከ፤ ከሠትኩ ቃላቲከ ለሕዝብከ ኢትዮጵያ፤ በጸጋሁ ለመንፈስ ቅዱስ ወመሐርክዎሙ አነ፤ ይቤ ያሬድ ካህን።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክአ ያሬድ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘተጸውዖቱ መዓር፤ ወለሥዕርትከ ጽዕድው ከመ ዘጌዴዎን ፀምር፤ ማኅሌታይ ያሬድ ወነባቤ ሐዋዝ መዝሙር፤ እመ ኮነ ብርዓ ሊባኖስ ወቀለመ ባሕር፤ እምኢኀልቀ በተጽሕፎ ዘዚአከ ክብር።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ
ያሬድ ማኅሌታይ ለእግዚአብሔር ካህኑ፤ ስብሐተ ትንሣኤሁ ዘይዜኑ፤ ኦሪት ቶታኑ ወወንጌል አሣዕኑ፤ ትርድአነ ነዓ በህየ መካኑ፤ ከመ ፀበል ግሁሣነ ፀርነ ይኩኑ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
ያሬድ "ካህኑ ለእግዚአብሔር"/፪//፪/
ትርድአነ ነዓ በህየ መካኑ ያሬድ ነዓ ትርድአነ/፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክአ ያሬድ
ሰላም ለአእናፊከ እንበለ ሕፀፅ ወንትጋ፤ ወለከናፍሪከ ዘነበባ ለቤተክርስቲያን ማኅሌተ ሕጋ፤ ሊቀ ካህናት ያሬድ መስተሥርየ ጌጋይ ኮናኔ ሥጋ፤ እለ ኪያከ የአኲቱ ወይዌድሱ እንግልጋ፤ እምነ ትሩፍ ጸጋከ ኢይኅጥኡ ጸጋ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ጸጋ ነሣዕነ ወሕይወተ ረከብነ፤ በኃይለ ጸሎቱ ለያሬድ አቡነ፤ ኪያከ እግዚኦ ነአኲት ነሢአነ ጸጋ ዘእመንፈስ ቅዱስ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
ጸጋ ነሣዕነ ወሕይወተ ረከብነ በኃይለ ጸሎቱ ለያሬድ አቡነ/፪/
ኪያከ ነአኲት ነሢአነ ጸጋ ዘእመንፈስ ቅዱስ/፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክአ ያሬድ
ሰላም ለዘባንከ ዘተአጽፈ ክብረ፤ ወለዕንግድዓከ ዘቦቱ ኃብተ አዕምሮ ኃደረ፤ ያሬድ ትቤ እንዘ ትዌጥን መዝሙረ፤ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ፤ ወለሙሴ አርአዮ ዘይገብር ግብረ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ
ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ፤ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ፤ በከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ/፪/
ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ በከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ/፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክአ ያሬድ
ሰላም ለልብከ ዘአፈድፈደ ጥበበ፤ ወለኲልያቲከ ካዕበ፤ አንቀጸ ብርሃን ያሬድ አመ ወጠንከ ነቢበ፤ በመቅደሰ አክሱም ሰኮናከ ዘበማየ ጸጋ ተሐጽበ፤ መጠነ ዓመት እምነ ምድር ልዑለ ተረክበ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
ያሬድ አመ ወጠንከ ነቢበ አንቀጸ ብርሃን/፪/
መጠነ ዓመት ሰኮናከ ልዑለ ተረክበ እምነ ምድር/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ውስተ ሰማያት ተመስጠ ግብተ፤ እምነ ሱራፌል ነሥአ ስብሐተ፤ ትንሣኤሁ ለወልድ ያሬድ ከሠተ፤ ተለዓለ መልዕልተ እምነ ምድር አመተ፤ እንዘ የኃሊ ዘድንግል ማኅሌተ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክአ ያሬድ
መዝሙረ ማኅሌት ሐዋዝ ዘመዋዕለ ክረምት ወሐጋይ፤ ዘመፀው ወዘፀደይ፤ ዘሠራዕከ ያሬድ ካህነ ዝማሬ ሠናይ፤ ሰላምየ ድሉ እግዚኦ መካልየ ልዑል ሰማይ፤ አኮ ዘወርቅ ወብሩር ጽሩይ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኃ ሰማይ፤ ወስዕለተነ ከመ መዓዛ ሠናይ፤ ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኃ ሰማይ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
ተወከፍ ጸሎተነ "ውስተ ኑኃ ሰማይ"/፪//፪/
ወስዕለተነ "ከመ መዓዛ ሠናይ"/፪//፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክአ ሐና
ሰላም ለአጥባትኪ ውስተ ምሥዋዓ ሕግ ጠረጴዛ፤ ሀሊበ ቅዳሴ ንጹሐ እለ ከመ ፈለግ አውኃዛ፤ እምቅንዓተ ዓለም ሐና ዘምግባረ ጠዋይ ግዕዛ፤ አግዕዝኒ እግዝእትየ ወኩንኒ ቤዛ፤ ከመ በደሙ ክርስቶስ ለሔዋን አግዓዛ።

ዚቅ
ለዛቲ ብእሲት ሠረቀ ላዕሌሃ ብዕለ ጸጋሁ ለአብ፤ ወአግዓዛ እምእኩይ ውስተ ሠናይ፤ እሞት ውስተ ሕይወት ወረሰየ ይዝክሩ ስማ፤ ውስተ ኲሉ ምድር።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል፤ ወጸገይኪ ጽጌ በኢተሰቅዮ ማይ ወጠል፤ ወበእንተዝ ያሬድ መዓርዒረ ቃል፤ ምስለ ሱራፌል ይዌድሰኪ ወይብል፤ ሐጹር የዓውዳ ወጽጌረዳ በትእምርተ መስቀል።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ
ናስተበቊአከ በእንተ ቃለ መዓርዒር ዘሱራፌል፤ ወበእንተ መዓዛ ውዳሴሃ ለማርያም፤ ንስእለከ ዝስኩ ማኅሌታይ ያሬድ።
@EOTCmahlet
ምልጣን፦
አልቦ እምቅድሜሁ ወአልቦ እምድኅሬሁ፤ ማኅሌታይ ሰብእ ዘከማሁ፤ ያሬድ ካህን ለክርስቶስ ሰበከ ትንሳኤሁ ፤ ኢየዓዱ እንስሳ ወሰብእ፤ እምነ ሠላስ ዜማሁ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ፦
አልቦ እምቅድሜሁ ወአልቦ እምድኅሬሁ ዘከማሁ ዘከማሁ ማኅሌታይ/2/
ያሬድ ካህን ሰበከ ለክርስቶስ ትንሳኤሁ ሰበከ/2/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
እስመ ለዓለም ፦
እምድኅረ ተንሥአ እሙታን መልዓ ስብሐቲሁ በጽዮን፤ ወተነግረ በመኃልየ መኃልይ ዘቤተ ክርስቲያን፤ በዘተሰምዩ ውሉዱ ውሉደ ብርሃን፤ ይኬልሕ ከመ ሱራፌል፤ ወጒህና ቃሉ ከመ ቃለ ቀርነ፤ አማን ጳዝዮን ዕንቊ ብርሃን ያሬድ ካህን።
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
ወጒህና ቃሉ ከመ ቃለ ቀርነ/2/
አማን ጳዝዮን ዕንቊ ብርሃን ያሬድ ካህን/4/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ፦
እምድኅረ ተንሥአ እሙታን በጽዮንመልዓ ስብሐቲሁ ፤
ወተነግረ ወተነግረ በመኃልየ መኃልይ ቤተ ክርስቲያን


@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet


@EOTCmahlet
# Join & share #
2.9K views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 17:33:48
አመ ፲፩ ለግንቦት በዓለ ቅዱስ ያሬድ ዋዜማ

ዋዜማ፦
ሃሌ ሉያ
ንዑ ንትፈሣሕ በመኃልይሁ፤ ወንንግር ለካህን ውዳሴሁ፤ ከመ ሱራፌል ለያሬድ ክላሁ፤ ለክርስቶስ ሰበከ ትንሣኤሁ: ማኅበረነ፤ ይባርክ በእዴሁ።
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
ማኅበረነ ይባርክ በእዴሁ/2/
ማኅበረነ ይባርክ በእዴሁ/4/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ፦
ያሬድ ጸሊ በእንቲአነ ጸሎትከ ወትረ ይብጽሐነ ያሬድ ጸሊ በእንቲአነ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
እግዚአብሔር ነግሠ፦
ያሬድ ማኅሌታይ ለእግዚአብሔር ካህኑ፤ ስብሐተ ትንሣኤሁ ዘይዜኑ፤ ኦሪት ቶታኑ ወወንጌል አሣዕኑ፤ ትርድአነ ነዓ በህየ መካኑ፤ ከመ ፀበል ግሁሣነ ፀርነ ይኩኑ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ይትባረክ፦
ለእለሰ ይዌድሱ ትንሣኤሁ ወይቄድሱ ያሬድ ካህን ምስሌሆሙ ያንሶሱ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ሰላም፦
ሃሌ ሃሌ ሉያ
አንበሳ ዘሞዓ ፍጹም ውእቱ እምሥርወ ዳዊት ወፈትሐ መጽሐፈ ትምህርት ያሬድ የኃሊ ትንሣኤሁ ወለብሰ ሰላመ ዚአሁ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
ያሬድ የኃሊ ትንሣኤሁ የኃሊ ትንሣኤሁ/2/
ወለብሰ ሰላመ ዚአሁ/4/


@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet


@EOTCmahlet
# Join & share #
2.9K views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 13:34:17 ከሌላ ቻናል የተላከ
4.1K views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 13:34:17 ሐናና ኢያቄም ይባረኩ ዘንድ ወደ ቤተመቅደስ ሔዱ። ዘካርያስም መልአኩ ለሐና እንዲነግራት ያዘዘውን ልትባረክ ስትመጣ ይነግራት ጀመረ።"ሐና የምነግርሽን ነገር ስሚ፤ በልቦናሽም ጠብቂው ከዚህ በኋላ ከባልሽ ከኢያቄም ጋር አትተኚ፤ በማኅጸንሽ ያለው ፍሬ ለእግዚአብሔር ንጹሕ መሥዋዕት ነውና። ይኸውም በዚያን ዘመን ሙሴ የተመለከተው ዕጽ ነው። በውስጡም እሳት ይነድ ነበር፤ ፍሬውንም አላቃጠለውም፤ ይኽም በበረሓው ድንኳን ውስጥ ያስቀመጡትን የወርቅ መሶብ፣ ከሰማይ የወረደ፣ ለዓለሙ ሁሉ ሕይወትን የሚሰጥ የተሰወረ መና ያለበት ነው። ዛሬም ለእግዚአብሔር የተቀደሰና ንጹሕ ቁርባንን እስከምትወልጂ ድረስ (ከጉድፍ) ከጉስቁልና ትጠበቂ ዘንድ አዝዝሻለው። ሥራውንም ለዓለሙ ሁሉ ለልጅ ልጅ ይናገራሉ አላት።" ሐናም ይኽን ነገር በልቧ እየጠበቀች በረከትን ተቀብላ ወደቤቷ ሔደች።

ዘመዶቿና ጎረቤቶቿም በሐና መጽነስ ተደስተው ይጎበኟቸው ነበር። ከእነዚህም መካከል ሀና ቤርሳቤህ የተባለች የአጎቷ የአርሳባን ልጅ ተደንቃ ማኅጸኗን ስትዳስሳት አይኗ በርቶላታል።

ሌላም ሐና የምትወደው ሳሚናስ ወልደ ጦሊቅ በሞተ ጊዜ ተግንዞ ወደተኛበት ሄዳ የአልጋውን ሸንኮር ይዞ በምታለቅስበት ወቅት ጥላዋ ቢያርፍበት ከተኛበት ተነስቶ .. ሰማይንና ምድርን ለፈጠረው አምላክ አያቱ የተባልሽ ሐና ሰላም ላንቺ  ይሁን .. አላት፤ አይሁድም ደንግጠው ምን አይተህ እንዲህ አልክ? አሉት።

እርሱም "ከዚህ ከሐና ማኅጸን የምትወለደው ሕጻን ሰማይ ምድርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኗት ሰማኋቸው፤ እኔንም ያነሣችኝ እርሷ ናት" አለ በዚህም አይሁድ በማኅጸን ባለች ጽንሷ እንዲህ ካደረገች በእኛ ልትሰለጥን አይደለምን ብለው በምቀኝነት ተነሳሱባት። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ለኢያቄም ተገልጾ ሐናን ሊባኖስ ወደሚባል ተራራ እንዲወስዳት ነገረው።#ጊዜ_ልደት_በደብረ ሊባኖስ

ሐናና ኢያቄምም በደብረ ሊባኖስ እያሉ ግንቦት 1 ቀን ሐና እመቤታችንን ወለደች። ቅዱስ ያሬድም ይህንን በማሰብ ...ኢያቄም ወሀና ወለዱ ሰማየ፤ ሰማዮሙኒ አስረቀት ፀሐየ። ኢያቄምና ሀና ሰማይን ወለዱ፤ ሰማይቱም ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስን አወጣችልን  ... አለ።

ስለ ጊዜ ልደቷም ሲናገር "በእንተ ልደታ ለማርያም አድባር ኮኑ ኅብስተ ሕይወት ወእምዕጸወ ገዳምኒ ፈረዩ አስካለ በረከት" .. ድንግል ማርያም ስትወለድ ድንጋዮቹ ተራሮቹ ሁሉ የሕይወት እንጀራ (ምግብ) ሆኑ እጽዋትም ሁሉ የሕይወት ፍሬ አፈሩ በማለት ይገልጽልናል።

ሐናና ኢያቄምስ ወላጅነታችሁ ድንቅ ነው። በእውነት በመጽሐፍስ መካን የነበሩ ብዙ ደጋግ ቅዱሳን የተባረከ ልጅን ወልደዋል። እናንተ ግን ለፍጥረተ ዓለም በጸጋ፤ ለፈጣሪ ደግሞ በግብር እናት የምትሆንን ልጅ ወልዳቹሃልና። ለእናንተ ልጅ ናት ለኢየሱስ ክርስቶስ ግን አንድያ እናቱ ናት።

አብርሃምና ሣራ ብሩክ ዘር የሚሆን ይስሐቅን ወለዱ፤ ሐናና ኢያቄም ግን የምድርን አሕዛብ ይባርክ ዘንድ አምላክ የሚወለድባትን ዘር ለዓለም ሰጡ።

ሐና አልቅሳ ለእሥራኤል መስፍን ለቤተ መቅደስም አገልጋይ የሚሆን ሳሙኤልን ወለደች፤ ሐናና ኢያቄም ግን ለአማናዊው ድኅነት መፈጸሚያ የሆነች ቤተመቅደስን ወለዱ።

ራሔል አልቅሳ ያዕቆብንና ዘሩን ከምድራዊ ረኃብ ከጊዜያዊ ሞት ለጊዜው የሚቤዣቸውን ዮሴፍን ወለደች፤ ሐናና ኢያቄም ግን አዳምን ከነልጆቹ ከዘለዓለማዊው ሞት አንስቶ ለዘለዓለማዊ ድኅነት በማብቃት የሚቤዣቸውን ክርስቶስን  የምታስገኘውን፤ እርሷም በፍቅሯ እየጠራች ስለኃጢአታቸውም ምሕረትን እየለመነች የምታድናቸውን መድኃኒት ወለዱ።

ሐናና ኢያቄምስ ከዚህ በፊት ከነበሩት ወላጆች ሁሉ ከበሩ፤ በክብር በሞገስም ከፍ ከፍ አሉ ለአምላክ አያቱ ሆነዋልና፤ ዘርን በማስቀረት ረድኤቱን በማድረግ ለአዳምና ለልጆቹ ሲሰጥ ለነበረ አምላክ እናቱን ስጦታ/መባዕ አድርጋችሁ ሰጥታቹሃልና። ይኸውም መባዕ ቅድሚያ ብቸኛ እናት ልትሆነው የምትችለውን (እስከ እርጅና ያለልጅ የቀራችሁበትን ጊዜ በእምነት ታግሳችሁ ከሌላ ሳትሄዱ) በመውለዳችሁ፤ ሁለተኛም ለእርሱ አገልጋይ ሆና ነየ አመቱ ለእግዚእነ ... እኔ ለጌታ ባሪያው ነኝ .. የምትል ለታላቂቱ አገልግሎት (ለድኅነተ አዳም) የተመረጠች ልጅን ስለሰጣችሁ ነው።

"ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ነዪ፤ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ ከአማና (ሃይማኖት) ራስ ከሳኔርና ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች።"

              መኃ 4፥8

ጠቢቡ ሰሎሞን በትንቢት መነጽር ልደቷን ተመልክቶ በሊባኖስ እንደምትወለድ በሳኔር በተመሰለ ከኢያቄም በኤርሞንም በተመሰለች ከሐናም እንደምትወለድ፤ የአንበሶች የነብሮች ተራራ በማለት ከሁለቱ ኃያላን ከቤተ መንግሥት እና ከቤተ ክህነት ወገን እንደምትወለድ ተናግሯል።

የእመቤታችን ልደት የተከናወነው በደጅ፤ ከፍ ባለ ተራራ ላይ ነው። በዚህ መወለዷም የእርሷ ልደት ለዓለም ሁሉ ጥንተ መድኃኒት መሆኑና ለሁሉ የተሰጠች ስጦታ መሆኑን ለማመልከት ነው።

በስደት ላይ ያለ ሰው የላመ የተዘጋጀ ምግብ የለውምና ሐናና ኢያቄም ንፍሮ እየበሉ እመቤታችንን በደብረ ሊባኖስ መውለዳቸውን በማሰብ በዓሉን ከደጅ ወጥተን ንፍሮ በመብላት እናከብረዋለን። በበዓሉም ምዕመናን ለከርሞ ብንደርስ በማለት ብጽዓት/ ስእለት ይሳላሉ። ዕለቱን ከኪዳን ከማኅሌት ከቅዳሴው በመሳተፍ፣ ቅዱስ ቁርባኑን በመቀበል፣ ጸበል በመጠጣት በመጠመቅ፣ የእመቤታችንን የምስጋና መጻሕፍትን በተለይም መልክአ ልደቷን በማድረስ፣ በመመጽወት የታመሙትን የታሰሩትን በመጠየቅ ማክበር ይገባናል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።                                 
                              ዋቢ መጻሕፍት
1.መጽሐፍ ቅዱስ የ፳፻ ዕትም
2.ድርሳነ ማርያም
3. መኃልይ መኃልይ ዘሰሎሞን ማብራሪያ በመጋቤ ሐዲስ ስቡሐ አዳምጤ
4. መዝሙረ ዳዊት ትርጓሜ ትንሳኤ ዘጉባኤ እትም
5.የእመቤታችን በዓላት በመ/ር ተስፋሁን ነጋሽና መ/ር ኤርምያስ ወ/ኪሮስ
4.2K views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 13:34:17 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ አሜን።

ክርስቶስ ተንሥአ እምሙታን በዐቢይ ኃይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሠላም።

             ልደታ ለማርያም

{ መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን }
                መዝ 86÷1

እመቤታችን ልደቷ እንደእንግዳ ደራሽ እንደውኃ ፈሳሽ ሆኖ ሳይነገር ሳይታወቅ ሳይጠበቅ የመጣ አይደለም፤ እንደልጇ ሁሉ አበው ሲሿት በምሳሌ ጥላነት ሲያዩዋት፣ ነቢያቱ ሲተነበዩላት ዳዊት ልጄ ሆይ ስሚኝ በማለት ሰሎሞንሞ እቴ ሙሽራዬ እያለ በትንቢት መነጽርነት ሲያናገራት የነበረች ናት እንጂ ።

አስቀድሞ ለአዳም በገባለት ቃልኪዳን ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንኃለው በማለት እርሱ ይወለድባት ዘንድ ያላት የመረጣት የአዳም የልጅ ልጅ እንደምትወለድና ከእርሷም እንደሚወለድ ነግሮታል።

ከዚህ በጎላ እና በተረዳ ግን ነቢዩ ኢሳይያስ "ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዓዐርግ ጽጌ እምኔሃ" ... ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከግንዱ ይወጣል ... በማለት በትር ብሎ በትረ አሮን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእሴይ ሥር ከዳዊት እንደምትወለድና ከእርሷም ጽጌ የተባለ ክርስቶስ እንደሚወለድ ተናግሯል።

የእመቤታችን ልደት ሊቁ "መኑ ይእቲ እንተ ትሔውጽ ከመጎኅ ያላት" ... ይህች እንደማለዳ ፀሐይ ያለች ማናት ... በማለት የገለጣት ለአማናዊው ፀሐይ ጎኅ፤ ለአማናዊው ወንጌል ንዑስ ወንጌል የሆነች የእመቤታችን ልደቷ ለልደተ ክርስቶስ ጎኅ ሆኖልን፤ በእርሷ መወለድ የእርሱን ሰው ሆኖ መወለድ እውን ሆኖልን ያረጋገጥንበት ነው።

ደራሲም ድንግል በልደቷ ለአዳምና ለልጆቹ ከመርገሙ መዳኛ ስለመሆኗ እንዲህ ብሎ ይጠቅሳል :-

ማርያም ድንግል በልደትኪ መጠነ አቅሙ፤
አዳም ይዌድስኪ ምስለ ደቂቀ ኩሎሙ፤
እስመ ለአዳም ብኪ ተስእረ መርገሙ።
        መልክአ ልደታ

የእመቤታችን ልደት ከአምስቱ ልደታት አንዱ የሆነው እንደ ልደተ አቤል ያለ ይኸውም ከእናትና ከአባት የሚወለዱት ልደት ነው። ልደቷም መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን... መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው..  በማለት ቅዱስ ደዊት "አድባር ቅዱሳን" ብሎ ከገለጣቸው በምድር  ከተነሱት ሁሉ በግብራቸው በጽድቃቸው በትሩፋት በክብር  እንደ ተራራ ከፍ ብለው ከሚታዩት ከተነሱት ከታላላቅ ቅዱሳን ወገን ነው። ታሪክ በእንተ ልደተ ማርያም

ጰጥሪቃና ቴክታ የሚባሉ ደጋግ ቅዱሳን ባለጸጋ ለእንሶቻቸው የወርቅ ጉትቻ እስኪያረጉ ድረስ ሁሉ የተትረፈረፋቸው ሰዎች ነበሩ። እነርሱም መካን በመሆናቸው ያዝኑ ነበር። አብዝተውም እግዚአብሔርን ለመኑት ጠየቁትም  በኋላም ሕልምን አዩ።

ሕልሙንም ሕልም ፈቺ ዘንድ ሔደው ፍቺውን ጠየቁት። እርሱም ነጭ ጥጃ መልኳ ደምግባቷ ያማረ ምግባሯ የተወደደ ሴት ልጅ ናት። እንዲህ አይነቷ እሷን የምትመስል እየወለደች ትሔዳለች፤ የመጨረሻዋ ጥጃ ጨረቃ መውለዷም ከሰማይ ዝቅ ከምድር እና ከፍጥረታት ወገን ግን ከፍ ያለች ልጅ ናት የፀሐዩ ነገር ግን አልተገለጠልኝም አላቸው። እነርሱም ይህንኑ ሰምተው ሄዱ። ሄኤማንን ወለዱ። ሄኤሜን ዴርዴንን፣ ዴርዴን ቶናን፣ ቶና ሲካርን፣ ሲካር ሔርሜላን ወለደች። ሔርሜላና ማጣትም የጌታ አያቱ የምትሆን ሐናን ወለዱ።

ኢያቄም እና ሐና

ከነገሥታቱ ከይሁዳ ወገን የሚሆን ኢያቄም ቀለዮጳ የሚባል አንድ ባለጸጋ ሰው ነበር። እርሱም ከካህናቱ ከነገደ ሌዊ የምትወለደውን ሐናን አገባ። እነርሱም የተቀደሱ ደጋግ ነበሩ። በደቂቀ እሥራኤል ዘንድም አብዝተው መስዋዕትን ያቀርቡ ነበር።

ከእለታት አንድ ቀንም ከደቂቀ እሥራኤል ወገን የሆነ ሮቤል የተባለ ሰው መጣና " በእኛ ፊት መሥዋዕትን ታቀርብ ዘንድ አይገባም፤ በእሥራኤል መካከል ዘር የለህምና" አለው። አይሁድ እና ካህናቱም ልጅ ስለሌላቸው ይንቋቸው ይጠሏቸው፤ መሥዋዕታቸውንም ለመቀበል እምቢ ይሉ ነበር።

ኢያቄምም ፈጽሞ አዘነና ስእለቴን እስኪሰጠኝ ወደእኔና ወደሚስቴም እስኪያይ ድረስ አልመገብም አልጠጣምም ብሎ ሱባኤ ለመያዝ ወደ ገዳም /በረሓ ወጣ። ሰባቱ ሰማያት እንደመጋረጃ ተገልጠው ነጭ ወፍ ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀመጥ በራእይ አየ።

ታላቁ የፋሲካ በዓል በደረሰ ጊዜ አንዲት የመንደሩ ሴት ወደሐና መጥታ ለምን ታዝኛለሽ? ራስሽንስ ለምን ትጎጃለሽ? በዓል ስለደረሰ መምህሬ የሰጠኝን ይህንን ልብስ ልበሺ ልብሱ የነገሥታት ልብስ ነውና አንቺ ትለብሽው ዘንድ ይገባሻል አለቻት።

ሐና ግን አዝና ነበርና ብቸኛ በመሆኔ፣ ልጅም ስለሌለኝ ኀዘንተኛ ነኝና ያማረ ልብስን አለብስም፤ ደግሞም ማን እንደሰጠሽ በምን አውቃለሁ? እኔንም ከኃጢአትሽ ልትጨምሪኝ ነውን? አለቻት። ሴቲቱም በምላሹ ተናዳ እግዚአብሔር ማኅጸንሽን በመዝጋቱ ደግ አድርጓል አለቻት።

ሐናም ከቀድሞው አብልጣ አዘነች። ፈጥና ተነስታም ወደቤተ መቅደስ ሔደች። አእዋፋትንም ከልጆቻቸው ጋር ባየች ጊዜ አንስሳት አራዊት ልጆች አላቸው፤ ምድር እንኳን ፍሬ አላት ለእኔ ግን ልጅ የለኝም፤ ለሁሉ ልጅ አለውና ለእነርሱ ልጅን የሰጠህ ወደእኔ ተመልከት ልጅንም ስጠኝ ብላ እያለቀሰች ትጠይቅ ነበር።

ቅድስት ሐና ሆይ እግዚአብሔርስ አንቺን ሳይመለከት ቀርቶ አይደለም። ከተናገረው ቀን ሳያጓድል ይመጣ ይወርድ ይወለድ ዘንድ ያለበትን ጊዜ እየጠበቀ ነበር እንጂ። እነሆም ቀኑ ደረሰ እግዚአብሔርም ወደአንቺ አየ ስእለትሽን ሰማ ልመናሽንም ተቀበለ ልጅንም ሰጠሽ፤ በአንቺም ዘንድ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም "ነጸረ አብ እምሰማይ ወኢረክበ ዘከማኪ" ያላትን ከፍጡራን መካከል አምሳያ የሚተካከል የሌላትን አንድያ እናቱን አገኘ።

ቅድስት ሐናም ነጭ ርግብ መጥታ በራሷ ላይ ተቀምጣ ከራሷ ላይም ወርዳ በጆሮዋ ገብታ በማሕፀኗ ስትተኛ በራእይ ተመለከተች። እነሆም በሐምሌ 30 ቀን የጌታ መልአክ (ቅዱስ ገብርኤል) ከሰማይ ወርዶ በፊቷ ቆመ፤ ጸሎትሽ ተሰምቷል ልምናሽንም ተቀብሏል ትፀንሻለሽ አላት። እርሷም ልጅን ከሰጠኝስ እስከ ዘመኑ ፍጻሜው ድረስ እንዲያገለግል ለእግዚአብሔር እሰጣለሁ አለች። መልአኩም ወደ ኢያቄምም ሔዶ ይህንን ብሥራቱን አበሠረው።ኢያቄምም ተደስቶ ሁለት በጎችንና 12 ላሞችን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ።

አንድ ሱባዔ ይዘው ከቆዩ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ንጽሕት ብጽእት ድንግል ማርያምም ነሐሴ 7 ቀን በብሥራተ መልአከ በንጹሕ መኝታ ተጸነሰች። ስለ ጽንሰቷም የብሕንሳው ሊቀጳጳስ አባ ኅርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ላይ "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ .... ድንግል ሆይ ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነሽ አይደለሽም በሕግ በንጹሕ መኝታ ከኢያቄምና ከሐና ተወለድሽ እንጂ... በማለት ንጹሕ ከሆነ አልጋ ንጹሕ ከሆነ መኝታ መገኘቷን ይናገራል። ጠቢቡ ሰሎሞንም.. ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ ምንም ነውር የለብሽም።.. (መኃ 4፥7) ብሎ ከማኅጸን ጀምሮ ጥንተ አብሶ እንደሌለባት ያስረዳናል።#ተአምረ_ማርያም_እምማኅፀነ_ሐና
3.8K views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 10:03:00 እንኳን ለእናታችን ለቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

የእናታችን ልደቷ የኛም ልደት ነው

እኛ የቻናሉ አድሚኖች መልካም በዓልን ለመላው ኦርቶዶክሳውያን የቻናላችን ቤተሰቦች እንመኛለን

ቀጣይ የሚመጡት ታላላቅ በዓላት ስርአተ ማህሌት እና ዋዜማ ቀደም ብለን እንደተለመደው እንልካለን ይጠብቁን

ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ልደት በረከቱን ያሳትፈን

የቆምነውን ቁመት ይቀበልልን

ድንግል ማርያም የአስራት ሀገሯን ኢትዮጵያን ዳሯን እሳት መሀሏን ገነት አድርጋ ትጠብቅልን

የአመት ሰው ይበለን

አሜን
https://t.me/EOTCmahlet
3.8K views07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 20:24:22 ምስባክ ዘግንቦት ልደታ

ዘነግህ፡-፵፬:፲፪
ምስባክ:-

ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር ፤
ኩሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን፤
በዘአጽፋረ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት።

ወንጌል ፡-ማቴ ፩:፩-፲፰

ዘቅዳሴ
መልእክታት -ገላ. ፬:፩-፲፫
                 -፩ጴጥ. ፩:፰-፲፫
                 -ግብ ሐዋ.፯:፵፬-፶፩

ምስባክ፡-፹፮:፩-፪

መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፤ ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናጽቀ ጽዮን፤
እምኵሉ ተዐየኒሁ ለያዕቆብ

ወንጌል፡-ሉቃ ፩:፴፱-፶፯
ቅዳሴ፡-ዘእግዝእትነ(ጎሥዐ)
4.8K viewsedited  17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 17:59:13 ለዛሬው አገልግሎት ይረዳ ዘንድ የተላከ

share
4.7K views14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 17:58:20 ክፍል ፫

( #በሕብረት_የሚባል )

ዳዊት ነቢይ በከመ ጸለየ፤እጼሊ ኀቤከ እግዚአብሔር አምላኪየ እንዘ ዕብል ከመዝ፤ፀወንየ ወኰኲሕየ፤ወታድኅነኒ ሊተ እምጸላዕትየ፤ወዐቃቤየ ትከውነኒ፤ወእትዌከል ብከ ምዕመንየ ወዘመነ ፍቃንርየ፤ረዳኢየ ወምስካይየ፤ወሕይወትየ ወታድኅነኒ፤
እምእደ ገፋዕየ፤ሃሌ ሉያ በስብሐት ዕጼውዓከ፤ንጉሥየ ወአምላኪየ፤ሚካኤል
መልአክ፤ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ፤ወበእንተ ነፍሰ ኵልነ፤ መልአኪየ ይቤሎ፤እመላእክት ሠምሮ፤መልአከ ኪዳኑ ለክርስቶስ

( #በሕብረት_የሚባል )

ሰላም ለክሙ ማኅበረ መላእክት ትጉሃን: ሰላም ለክሙ ማኅበረ ነቢያት ቅዱሳን: ሰላም ለክሙ ማኅበረ ሐዋርያት ፍንዋን:
ሰላም ለክሙ ማኅበረ ሰማዕት ወጻድቃን:
ሰላም ለክሙ ማኅበረ ሥላሴ ጉቡዓን: ወሰላም ለማርያም ዘእሳት ክዳን።

( #በሕብረት_የሚባል )

ማኅበረ መላእክት ወሰብእ፤ተዓይነ
ክርስቶስ ወእሙ፤ሰላም ለክሙ ሶበ እከሥት አፉየ ለውዳሴክሙ፤ፍሬ ማኅሌት እምልሳንየ ትቅስሙ፤ምስሌየ ሀልዉ ወምስሌየ ቁሙ።

( #ካህን_የሚለው )

#ሰላም ለአብ ወለወልድ
ቃሉ፤ለመንፈስ ቅዱስ ሰላም ዘአካሎሙ አካሉ፤ለማርያም ሰላም እንተ ተሳተፈት ስብሐተ እሉ፤ሰላም ለመላእክት ወለማኅበረ በኩር ኵሉ፤ጽሑፋነ መልክእ ወስም በሰማይ ዘላዕሉ።

#ሰላም ለአብ ገባሬ ኵሉ ዓለም፤ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ
ሰላም፤ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።

#ሰላም ለአብ ዘእምቅድመ ዓለም ነጋሢ፤ለወልድ ሰላም ሥጋ ማርያም
ለባሲ፤ለመንፈስ ቅዱስ ሰላም ኃጢአተ ዓለም ደምሳሲ፤ኃይልየ ሥላሴ ወፀወንየ
ሥላሴ በስመ ሥላሴ እቀጠቅጥ ከይሴ።

( #መልክዐ_ስላሴ_የሚባል_ከሆነ_እዚጋ_ይገባል )

#ሰላም ለክሙ ሚካኤል ወገብርኤል ሱራፌል ወኪሩቤል፤ዑራኤል ወሩፋኤል ሱርያል ወፋኑኤል፤አፍኒን ወራጉኤል ወሳቁኤል፤ወሰላም ለቅዳሴክሙ ትጉሃነ ሰማይ ዝክሩነ በጸሎትክሙ

#ሰላም ለክሙ ሚካኤል ወገብርኤል ሱራፌል ወኪሩቤል፤ዑራኤል ወሩፋኤል ሱርያል ወፋኑኤል፤አፍኒን ወራጉኤል ወሳቁኤል፤ሊቃናተ ነድ ዘሰማያዊት ማኅፈድ፤በእንተ በግዑ እቀብዋ ለዛቲ ዓፀድ

#ሰላም ለክሙ ሚካኤል ወገብርኤል
ሱራፌል ወኪሩቤል፤ ዑራኤል ወሩፋኤል ሱርያል ወፋኑኤል፤አፍኒን ወራጉኤል ወሳቁኤል፤ወሰላም ለከናፍሪክሙ ከመ እዕቀቡነ ተማህፀነ ለክርስቶስ በደሙ።

#ሚካኤል ወገብርኤል ሱራፌል
ወኪሩቤል :እለ ትሴብሕዎ፤መላእክተ ሰማይ ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ፤ቅድመ መንበሩ ለእግዚእነ

#ሰላም ለከ ሊቀ መላእክት
ሚካኤል :ወዲበ ሠናይትከ ዓዲ ለሰብእ ሣህል፤አሐዱ እምእለ ይባርክዎ ለቃል፤እዙዝ ዲበ ሕዝብ ከመ ትተንብል፤በእንተ ሥጋሁ ነበልባል ርእሰነ ከልል።

#ሰላም ለከ ንሥረ እሳት ዘራማ፤ማህሌታይ
ሚካኤል መዓርዒረ ዜማ፤ለረዲኤትከ ዲቤነ ሲማ፤ለማኅበርነ ከዋላሃ ዕቀብ ወፍጽማ፤እመራደ ነኪር አጽንዕ ኑኃ ወግድማ።

#ሰላም ለሚካኤል ዘነድ ሡራኁ፤ይትከሃን ወትረ በበምሥዋዒሁ፤እምቅዱሳን አሐዱ እምእለ ይተግሁ፤ሐዋዝ በአርያም መኃልይሁ፤ነጐድጓደ ስብሐት ግሩመ ይደምጽ ጉይናሁ

( #መልክዐ_ሚካኤል _የሚባል_ከሆነ_እዚጋ_ሰላም_ለልሳንከን_በመተካት_ይገባል )

#ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል፤ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል፤ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል፤አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል፤እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል።

#ንዌጥን ዝክረ ውዳሴሆሙ ለነቢያት ወሐዋርያት፤ለጻድቃን ወሰማዕት፤ለአእላፍ መላእክት ዘራማ ኃይላት፤ለምልዕተ ጸጋ ማርያም ቡርክት፤ወለሥግው ወልዳ ነባቢ እሳት።

#እዌጥን ዝክረ ወድሶታ ለመንፈሳዊት
ርግብ፤ዘመና ልሁብ፤እምከናፍሪሃ ይውኅዝ ሐሊብ፤ተፀውረ በማኅፀና እሳት ዘኮሬብ :ወኢያውዓያ ነድ ወላህብ።

#ማኅፀንኪ እግዝእትየ ማርያም ይከብር ምስብዒተ፤እምጽርሐ አርያም ዘላዕሉ ወእምኪሩቤል ትርብዕተ፤፺ተ አውራኃ ወ፭ተ ዕለተ፤ፆረ ዘኢይፀወር መለኮተ፤አግመረ ዘኢይትገመር እሳተ።


#ምንተ አዐስዮ ለእግዚአብሔር አሐተ፤በእንተ ኵሉ ዘገብረ ሊተ፤ረስይኒ እሙ አሥምሮ ግብተ፤ማርያም እግዝእትየ ዘሜጥኪ እሳተ፤ድኅረ በጽሐ ልሳኑ ዘለኪ ቤተ።

( #ቁመቱ_በላይ_ቤት_ሲሆን_የሚባል )

#ይትባረክ ስምኪ ማርያም ዘአውፃእከነ እምጸድፍ፤በርኅራኄኪ ትሩፍ፤ይዌድሱኪ ኪሩቤል በዘኢያረምም አፍ፤ሐራ ሰማይ ትጉሃን እኁዛነ ሰይፍ፤ኍላቌሆሙ አዕላፍ፤አምሳለ ደመና ይኬልሉኪ በክንፍ።

( በዓሉን_ወይም_ዘመኑን _የሚነካ_መልክአ_ኪዳነ_ምህረት_ካለ_እዚጋ_ይገባል )

#ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ውድ ማህሌታውያን ይህን ቻናል ለሌሎች ይደርስ ዘንድ #ሼር በማድረግ ይተባበሩን፤ እናመሰግናለን።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet

አስተያየት ካለ @eotcmahletawian ላይ


@EOTCmahlet                  
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet


      @EOTCmahlet
    #Join & #share

 
4.5K views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 17:58:20 ክፍል ፪

@EOTCmahlet
ቅኔ ማህሌት (ከ3ቱ የቤተክርስቲያን ክፍሎች አንዱ) በአስተዳዳሪው መቀመጫ (ግራ ወገን ና ቀኝ ወገን) በመባል ለ2 ቦታ ይከፈላል።  ሊቃውንቱም እንደየ ማዕረጋቸው በመቆም ማህሌቱን እየመሩ  ያስጀምራሉ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
"ስምዓኒ" ከመባሉ በፊት ግን የፀሎተ ሰአታት አካል የሆነው "ሚካኤል ሊቀ መላእክት..." ይደረሳል። ከዛ በኃላ ጸሎት ይደረሳል። ከዚህ በመቀጠል ከአንዱ ወገን "ስምዓኒ" ይመራል፤ ተመሪም መቋሚያውን አስቀምጦ ይመራል።
አባባሉም፦
@EOTCmahlet

መሪ፦ስምዓኒ እግዚኦ
ተመሪ፦ስምዓኒ እግዚኦ
መሪ፦ጸሎትየ
ተመሪ፦ጸሎትየ
መሪ፦ሃሌ ሉያ
ተመሪ፦ሃሌ ሉያ
መሪ፦ሃሌ ሉያ
ተመሪ፦ሃሌ ሉያ
መሪ፦ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ
ተመሪ፦ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ
መሪ፦ሃሌ ሉያ
ተመሪ:-ሃሌ ሉያ
መሪ፦  ሃሌ ሉያ
ተመሪ፦ ሃሌ ሉያ
መሪ፦ወኢትሚጥ ገጽከ እምኔየ
ተመሪ፦ወኢትሚጥ ገጽከ እምኔየ

@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
እስከ እዚ ከተመራ በኃላ ምሪቱ ይቆማል ግን ተመሪው ከመሪው ፊት አንዳለ እዛው እንዳለ ይጠብቃል(ወደ ቦታው አይመለስም)
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ምሪቱ ከ2ቱ ክፍሎች ከግራ ከጀመረ(ስምዓኒን   ከመሩ) ከቀኝ ወገን ማንሻ ያነሳሉ፤ ቀኝ ወገን ስምዓኒን ከመሩ ከግራ ወገን ማንሻ ያነሳሉ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማንሻውን የሚያነሱት(ግራም ይሁን ቀኝ) "አንሽ ወገን" ይባላሉ፤ መሪው ባለበት ያሉት ደግሞ "መሪ ወገን" ይባላሉ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet

አንሽ ወገን ካሉት 1ሰው፦ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ
አብረውት ያሉት(አንሽ ወገን)፦ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
መሪ ወገን፦ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ
አንሽ ወገን፦ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
መሪ ወገን፦ ወኢትሚጥ ገጽከ እምኔየ

ተመሪ፦ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ (ይህን ብሎ ወደ ቦታው ይመለሳል)

መሪ ወገን፦ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
አንሽ ወገን፦አመ ዕለተ አጽውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ

መሪ ወገን ና አንሽ ወገን አንድ ላይ፦ ለዓለመ ወለዓለመ ዓለም ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡፡ንወድሶ ለዘሀሎ እግዚአብሔር ልዑል፡፡ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኵሉ ዓለመ በአሐቲ ቃል


ውድ ማህሌታውያን ይህን ቻናል ለሌሎች ይደርስ ዘንድ #ሼር በማድረግ ይተባበሩን፤ እናመሰግናለን።

አስተያየት ካለ @eotcmahletawian ላይ


@EOTCmahlet                  
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet


      @EOTCmahlet
    #Join & #share
3.6K views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ