Get Mystery Box with random crypto!

E͟n͟t͟r͟a͟n͟c͟e͟ H͟u͟b͟ E͟t͟h͟i͟o͟p͟i͟a͟

የቴሌግራም ቻናል አርማ entrancehubethiopia — E͟n͟t͟r͟a͟n͟c͟e͟ H͟u͟b͟ E͟t͟h͟i͟o͟p͟i͟a͟ E
የቴሌግራም ቻናል አርማ entrancehubethiopia — E͟n͟t͟r͟a͟n͟c͟e͟ H͟u͟b͟ E͟t͟h͟i͟o͟p͟i͟a͟
የሰርጥ አድራሻ: @entrancehubethiopia
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.30K
የሰርጥ መግለጫ

📝በEntrance Hub Ethiopia
ለመመዝገብ➜ @EntranceHubbot
እኛን ለማግኘት ➜ @Entrancehub_Admin
0917318110
0948398047

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-29 22:07:26 አንድ ድንቅ ተማሪ ያደገረው ጀበድ ፤ እውነተኛ ታሪክ
ክፍል ሁለት( ፪)


የግቢው አሳላፊዎችን ያዩትን ለማመን የሚከብድ ታሪክ የትምህረት ቤቱ አስተዳዳሪ ለሆነችው እንስት በመገረም ነገሯት ፣እናቱ አስጠርተውም አወሩ። የሚገርመው ነገር ግን ምንም እንኳ እናትየው ምሳ የምትቋጥርለት ለልጇ ባይኖራትም አንድ ቀን እንኳ ጠይቋት አያቅም!እንዴትስ አልጠየቃትም? ሌላ ህፃን ልጅ እንኳን ምግብን የመሰለ አስፈላጊ ነገር ይቅርና ለከረሚላ እንኳን የሚነዘንዝ ስንቱ ባለበት ሰፈር እሱ እንዴት ይሄን አላደረገም?የሆነው ሆኖ አሁን በትምህርት ቤቱ ወጪ ምሳ ከሚመገቡ ተማሪዎች ዝርዝር ውስጥ ገብቶ ፤ አሁን ያለምንም ችጋር እና ጠኔ ሳይገለው ትምህርቱን በጥሩ ሁኔታ ቀጥሏል!

ስማ ብሮ ፤ ማሙሽ በጣም ስለተባረከ ነው ይሄን ሁሉ ፀጋ የተላበሰው። ከዚ መልዕክት ምን ተማረችሁ ብዬ ብጠይቃችሁ፤ ብዙዎቻችሁ የራሳቹን ብያኔ ልትሰጡ ትችሉ ይሆናል! ነገር ግን ይህ ልጅ የሚከተሉትን ድንቅ ነገር አስተምሮናል ።

የሚፈልገውን ት/ቤት ለመግባት ባሉካዋን ከመጠየቅ ወደኋላ አላለም!

በዚህም በንፈልገው ማንኛውም ነገር ቆራጥ አቋም ወስደን ልንጀምረው ይገባል!

ትምህርት ቤት ከተቀላቀለ ቡኋላ አሪፍ ውጤት ማስመስገቡን አላቆመም

ማሙሽ በርግጥ እቅዱ እዛ ምቹ ት/ቤት መማር አደለም ፤ በዛ ት/ቤት ውስጥ ተምሮ ለውጥ ማምጣት እንጂ ፤ ጋይስ ንቁ እንጂ እቅዳችሁ ካምፓስ ለመግባት እንዳይሆን ፤ ካምፓስ በምትፈልጉት ሞያ ላይ አሪፍ ስንቅ ይዛችሁ ሀገራችሁን ልትቀይሩ ይገባል!

ማሙሽ እናቱን ምሳ ምሳ ብሎ እናቱን አልነዘነዛትም ፤ ይሄ ደሞ የቤተሰብን አቅም አውቆ ባለን ነገር ደስተኛ መሆን እንዳለብን ያስተምረናል ፤ ቤተሰቦቻችን ላይ ጫና አለማሳደር ጥቅሙ ለኛ ነው።እንመረቃለን ፤ ቢያንስ ባይመርቁን እንኳ አይረግሙንም።ይሄ ደሞ ለህይወታችን ለሚመጡ ድሎች በር ከፋች ነው!

ማሙሽ እናቱን ሰው ፊት አላሳ'ጣትም(ይጠብቃል)!

ይህን ያረገው ነገር ደግሞ ትልቅ ህልም ስለነበረው ፣ ነገ ተምሮ የራሱን ኑሮ መኖር ሲጀምር እንኳን እሱን ይቅርና እናቱን ሳይቀር እንጀራ የሚያበላበት ፤ የሚጦርበት አቅም እንደሚኖረው ስለሚያውቅ ዛሬን ተርቦ መማር መረጠ!

ዕድል ያለ ጥረት ባዶ ነው።

ስንቶቻችን ነን ፤ አባቴ ንባብ ለማንበብ ስልክ ያስፈልገኛል በእጅ የሚጠረገውን ስልክ ግዛልኝ ብለን ተቀብለን ፤ በSocial Media ብቻ የምንጋተትበት!

ማሙሽ የሚፈልገው ነገር አሪፍ ት/ቤት መማር ነበር ፣ ለዛም ዕድል በሯን ከፍታለታለች ፤ እሱ ደግሞ ችክል አርጎ በማንበብ እድሉን ተጠቀመባት።

GUYZ የናንተን ዕድል ስንት ሰው እንደሚመኘው ብታቁ ፤ ትጠቀሙበት ነበር!

ስንት ሰው ምሳ እና መክሰስ መብላት እንደሚፈልግ ታውቃላችሁ?

ስንቱ ነው እንደናንተ ሲደብረው TV እያየ EDM Music እየከፈተ ጮቤ እየረገጠ መዝናናት የማይፈልገው?

ክፍለ ሃገር ባያቹ ፤ ዱር ለዱር ሰብል በመሰብሰብ ቤተሰቦቻቸውን እንዴት እነደማያግዙ።በቃ ቀኑን ሙሉ እረፍት የለም፤ ማታ አካላቸው ይዝላል ይተኛሉ።አንዳንድ ቀን ደሞ መብራት አይኖርም ይተኛሉ።አለቀ


ስሚ የኔ እህት እንዳቺ በየወሩ የፕሪሚየም አልግሎት ከቴሌ ገዝቶ በየቀኑ PDF መፃፎችን እያወረደ ማንበብ የማይፈልገው ማን ይመስልሻል ? ሁሉም!!
5ኛው መልዕክት ደግማችሁት እዩት ያልተጠቀማችሁት ወርቃማ ዕድል አለ!

ቢያንስ እስቲ አሁን እንኳን ንቁ አረ ንቁ

ሰላም ሁኑልን ፣ ክፉ አይንካብን ።

ቻናሉን በማስተዋወቅ እገዛቹን ስጡን ፣ እናመሰግናለን
D_Marvel Tutorials

Join @eruditional
617 views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 22:07:26 አንድ ድንቅ ተማሪ ያደገረው ጀበድ ፤ እውነተኛ ታሪክ


ታሪኩን በቲቪ ነው የሰማውት ፤ ግን የልጁን ስም መናገር ስላተፈለገ አቡሽ እያልን እንጠራዋለን።አቡሽ ጥልቅ ትምህርት የመማር ፍቅር የነበረው የደሃ ልጅ ነው።

ለዚህም ነው አሪፍ ትምህርት ለማግኘት ሰፈራቸው ካለው የግል ትምህርት ቤት ፤ የአስገቡኝ ጥያቄ ሊያቀርብ የወሰነው።የትምህርት ቤቱ ባለቤት እና አስተዳዳሪ የሆነችውን እንስት ሁሌ ከስራ ስትወጣ ሊያወራት አስቦ ብዙ ጊዜ ነው በነዛ በሚያሳዝኑ የጨቅላ አይኖቹን ጎሽሟው የምታልፈው። የዚህ ብላቴና ሁኔታ መደጋገም ያሳሰባት እንስትም ልክ እንደተለመደው ከስራ ስቶጣ አገኘችው ወደ ህፃኑ ቀረብ ብላ ጎንበስ አለችና (ፀጉሩን በእጆቿ እየደባበሰች)''ማሙሽዬ ፤ ምነው ርቦህ ነው አለችው ?

ብላቴናውም ''አይ ፣ አንቺ ትምህርት ቤት መማር ፈልጋለሁ ግን እናቴ የትምህርት ቤቱን ወጪ የምትከፍልበት አቅም የላትም'' አላት እምባ እየተናነቀው።እንስቷም የብላቴናውን የመማር ፍቅር አይታ እሷ ትምህርት ቤት የነፃ ትምህርት እድል (SCHOLARSHIP) ሰጠችዉ። ማሙሽም እንደ ማንኛውም ቤተሰብ ያለው ተማሪ ምሳ ከቤቱ ማምጣት ስለነበረበት ፤ ምሳ መቋጠር የናቱ ድርሻ ሆነ።

ማሙሽ አዲስ በገባበት ትምህርት ቤት ውስጥ በመንፈቅ አመቱ አሪፍ ውጤት ማስዝገብ ጀመረ። ከዛች የመጀመሪያ ስኬት ጀምሮ ማን ይቻለው? ይበልጥ እያየለ መጣ ፣ በቃ እንዳለ ውጤቱን ሰቃቀለው!

ነገር ግን ይሄ ሁሉ ሆኖ እያለ ፣ አንድ ቀን እንኳ የተቋጠረለትን ምሳ ከጓደኞቹ ጋር በልቶ አያቅም። በቃ ልክ ምሳ ሰዓት ሲደርስ የተቋጠረለትን ምሳ ዕቃ ይዞ የት እንደምገባ አይታወቅም። ልክ ሲደወል ነው የሚመጣው።''ምን አይነት ስግብግብ ነው?'' ጓደኞቹ ጠሉት!

ነገሩ ሁሌ የተደጋገማባቸው የትምህርት ቤቱ አሳላፊዎቹ ማሙሽን በቅርብ ይከታተሉት። ዛሬም እንደ ሁል ጊዜው ማሙሽ የምሳ እቃውን ለብቻው ይዞ ከጓዶቹ ተነጠለ ፤ ድብቅ የሆነ ቦታ ላይ ሲደርስ ጋደም ብሎ ምሳ ዕቃውን በእጁ እያነከባለለ ይጨወት ጀመር!ምሳ ዕቃው በዶ መሆኑ ነው!!''ይሄን ተደብቀው የሚመለከቱ የትምህርት ቤቱ አሳለፊዎች የበታችነት ስሜት በማይነበብው የማሙሽ ፊት ላይ የደስታ እና የምስግና ስሜት ሲመለከቱ አለቀሱ ፤ ተሰማቸው!

ማሙሻም ልክ ድሮ እንደሚያረገው ወደ ክላስ የሚል ደውል ሲደወል ባዶዋን ምሳ እቃ ይዞ ወደ ክፍሉ ተመለሰ!

ይቀጥላል........
610 views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 19:57:35



አንድ ተማሪ እኮ ነው የ 1 ብሯን ሳንቲም ወደ ሰማይ ፊር አርጎ
ሚዛን ከሆነ ፊልም አያለው
አምበሳ or ጎፈር ከሆነ Music ሰማለው
ነገር ግን ይቺ ሳንቲም በጠርዛ ከቆመች ወደ ንባብ ሄዳለሁ'' ብሎ እርፍ


''አደራችሁን እራሳችሁን በጊዜ እና በሁኔታዎች አትወስኑ ''

ስንቶቻቹ ናችሁ ቆይ ዛሬ አሪፍ ቢቲንግ አለ እሷን ጋማ ልበልና ነገ አነባለው ብላቹሁ ሳታነቡ የቀራችሁት ?

አሁን መላ ልፈልግ ፤ አሁን ግጥም ልፃፍ ፤ አሁን ዜና ልስማ .....በኋላ አነባለው ትላላቹ ።

በኋላ + በኋላ +በኋላ= ወደኋላ


'' ስራን ወደ በኋላ እንዳታስተላለፉ የሚረዱ ነጥቦች

ያላችሁበትን ጊዜ ፤ ሁኔታ ፤ አቅም እና ተነሳሽነት በደም ለይቶ ማወቅ!

አንዳንድ ተማሪዎች በሮኬት principle የሚሰሩ አሉ....ጭራቸው ላይ እሳት እስካልተቀጣጠለ ድረስ የማይቀሳቀሱ እንደዛ እንዳንሆን እቅማችን እና ችሎታችንን መመዘን ያስፈልጋል!

ከራስ ጋር በደምብ ማውራት!

እስኪ አሁን ቁጭ በሉና ሁሌ ልታነቡ ስትሉ የሚረብሻቹ ነገር ምን ምን እንደሆኑ ለዩና ማስታወሻ ላይ ዘርዘሩ !

እነኚ ረባሽ ሁኔታዎች ለምን በተደጋጋሚ እንደሚከሰቱ ምክንያቱን ፃፉ!

ምክንያታቸው ካወቃችሁ በኋላ ሊደረግላቸው የሚገቡ ቅደመ መከላከያ ዘዴዎችን አውጡላቸው !

ከዛን ድግምት ድገሙባቸው! ፈሪ ሁላ አይዟቹ አደንግጡ ፤ ያወጣችሁትን ረቂቅ ማፅደቅ እንዲሁም መፈፀም እንድትችሉ አምላካችሁን ለምኑ ጠይቁ ማለቴ ነው!

*ከዛን ነቲን ስፓስ ዩ*


ይሄን ፊልም የት ነበር ያየውት

: ምንደነው ዘመዴ ስትበር ግቢ ካለገባው ብለህ ሰዎቼን ያስቸገርከው ?

አረ አፍጥነው ምንድነው መፍዘዝ ነቃ ነቃ በል እንጂ Entrance እኮ ቀርቧል ።

ወዳጄ አረ ተይ እንደዚህ አይሆንም ቡሃላ እርሾ እና ጨው የሌለው ዳቦ እንዳትጋግሪ

መልካም ግዜ ይሁንላችሁ

ቻናላችንን Share አድርጉ

@eruditional
880 views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 18:57:14

CIVICS EGESCE (grade 9&10{ 2002_2005
ጥያቄዎች ሙሉ ከበቂ መብራሪያ ጋር ዛሬ በ Entrance Hub tutorial class ይቀርባል


በሚገርም Quality ተዘጋጅቷል
ሙሉ PDF ለማግኘት ወደ Tutorials Channel ይቀላቀላሉ

የ Entrance Hub tutorial class ቤተሰብ ያልሆናችሁ አሁኑኑ ተመዝግበው ቤተሰብ ይሁኑ
@Entrance_Hub_Register_Bot
4.8K views15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 18:51:34
Biomolecules ምርጥ ኖት በEntrance ዛሬ እንዳያመልጣችሁ

በሚገርም Quality ተዘጋጅቷል
ሙሉ PDF ለማግኘት ወደ Tutorials Channel ይቀላቀላሉ

የ Entrance Hub tutorial class ቤተሰብ ያልሆናችሁ አሁኑኑ ተመዝግበው ቤተሰብ ይሁኑ
@Entrance_Hub_Register_Bot
4.2K views15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 18:51:18
Biomolecules ምርጥ ኖት በEntrance ዛሬ እንዳያመልጣችሁ

በሚገርም Quality ተዘጋጅቷል
ሙሉ PDF ለማግኘት ወደ Tutorials Channel ይቀላቀላሉ

የ Entrance Hub tutorial class ቤተሰብ ያልሆናችሁ አሁኑኑ ተመዝግበው ቤተሰብ ይሁኑ
@Entrance_Hub_Register_Bot
3.1K views15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 12:45:49
#Update


የEntrance Hub መመዝገቢያ update bot ለመጠቀም /start ብለው ይላኩ


Link - https://t.me/entrance_hub_register_bot
1.7K viewsedited  09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 09:14:00 Determinans mind map (Entrance Hub Ethiopia)
ሀሉንም Chapter ዛሬ በዚህ አይነት መልኩ በ Entrance Hub Tutorial class ማግኘት ትችላላችሁ
ቤተሰብ ያልሆነ አሁኑኑ ይመዝብ
@Entrance_Hub_Register_Bot

ለበለጠ መረጃ
@EntranceHubEthiopia
ይጎብኙ
4.3K views06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 09:13:13

ዛሬ በ Entrance Hub እጅግ በጠም ወሳኝ የሆነ የMathematics ድግስ ተዘጋጅቷል

ከ G9_12 በጠም ወሳኝ የሆነ Unit ሁሉንም በምርጥ graphics ጥበብ የተዘጋጀ Mind map

ስለ Vectors እና 3D ሙሉ ግንዘብ ከሌላችሁ መድሐኒቱን ዛሬ ማታ ያገኛሉ
ስለ Vectors Key point የሆነ 30 ጥያቄ2ቋን ከበቂ ማብራሪያ ጋር ዛሬ ከ12:00 ጀምሮ ይጠብቁ?

ሁሌም አዲስ ነገር ከEntrance Hub
የEntrance Hub ቤተሰብ ካልሆኑ ዛሬውኑ በመመዝገብ ቤተሰብ ይሁኑ
ለመመዝገብ ይህን ይጠቀሙ
@Entrance_Hub_Register_Bot
ቤተሰብ ከሆኑ 12:00 በ Tutorial class እንገናኝ
ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎብኙ
@EntranceHuBEthiopaia

የMind map ዝግጅት ምን አይነት ምን እንደሆነ ለማወቅ ይህንን File ይመልከቱ
1.6K views06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 18:54:27 . የመጨረሻው ምዕራፍ
የመጨረሻው ጥረት
የመጨረሻው ተጋድሎ


ቀናቶች ቆጠረዋል ፣ አሁን ተቃርበዋል ፣ እያበቁ ነው 30 ቀናት ብቻ ቀርተዋል ፣ የመጨረሻው ምዕራፍ ፣ እንሆ ከዛሬ ይጀምራል ። በዚህ ወራት ውስጥ ቀናት ፣ ሰዓታት ፣ ደቂቃም ጨምሮ ዋጋ አላቸው ።

እነኝህ የመጨረሻዎችሁ አዲሱ ምዕራፍ ቀናቶች ፣ በ4 መሰረታዊ ክፍሎች ልከናወኑ ይገባል ።

በመጀመሪያ ልኩን ለ አራት ቦታ እኩል በመክፈል አስምሩ (quarter) ከዛም ፦

በመጀመሪያው ሳጥን ዛሬውኑ ማለቅ ያለባቸው ነገሮች እናስገባለን (most important and urgent)
እነዚህ ነገሮች የግድ ዛሬ ማከናወን ያሉብን ነገሮች ናቸው።

ለምሳሌ እድር መክፈል ይሄን ምሳሌ ያደረኩበት ምክንያት አንድ ቀን ካመለጠን 30 ቀናትን ጠብቀን ነው መክፈል የምንችለው በዛ ላይ በነቅጣት።

ልብ በሉ፣ ይህ ቀን ዛሬ በዚህች ሰዓት ምናልባት Biologyን ብሎም Unit 3ን የምናጠናበት ፣ የምንረዳበት፣ የምናጠናቅቅበት፣ የምንዘጋጅበት፣ የምንመረምርበት ግዜ ሊሆን ይችላል ። ይህ ግዜ ካለፈ አለፈ ነው አበቃ ፣ Biology Unit 3 ከ Matric Exam ተዘለለ።

ምክንያቱም ምናልባት ቀጣይ ቀን የUnit 2 , የUnit 4 ፣ ወይም የ Chemistry ፣ የHistory ብቻ የሌሎቹም ሊሆን ስለሚችል ፣ የሌሎቹን ቀን ቀንሰን ስንጠቀም በተዘዋዋሪ፣ በሒዎታችን አስፈላጊ የሆነው ነገር ማስቀረታችን እንደሆነ ግንዛቤ ውስጥ አስገቡ ።

ስለዚህ ዋጋ ሊያስከፍሉን የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ልናሰምርባቸው ይገባል ።

በሁለተኛ ሳጥን ውስጥ ደግሞ ዛሬ መፈፀም ያለባቸው ነገር ግን አስቸኳይ ያልሆኑ።

ቀጣይ ቀን መስራት እንችላለን ነገር ግን ዛሬም የመፈፀም አቅም አለን ። ለምሳሌ ከትንሽ ደቂቃዎች በፊት Geography ወይም ደግሞ Chemistry Unit 2 አጥንተናል እንበል ። ጽንሰ ሃሳቡን ተረድተናል ፣ ከ3 ሁሉንም ዋና ዋና የሚባሉ ለMatric የሚያስፈልጉንን ጉዳዮች ተረድተናል ። ነገር ግን ከዚህ Unit ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ያለፉትን Matric Exam አልሰራንም ። ነገር ግን ቀጣይ ቀን መስራት እንችላለን፣ ግን ዛሬ ስንሰራው ሁለት ነገሮችን በዋነኝነት እናገኛለን ።
1ኛ ፡ ለነገ መጨነቁን እናቆማለን(repression)

2ኛ ፡ በትንሽ ነገር በራሳችን መተማመን እነጨምራለን ።

so this is the MOST IMPORTANT PART OF THE DAY.

በ3ኛ ላይ በዚህ በቀሩን ቀናቶች ውስጥ ማከናወን ያሉብን ድርጊቶች አንዱ፡ በዚህ ጊዜ ስራ ጨርሳችሁ "ጨርሻለሁ" አሁን ትንሽ እረፍት ያስፈልገኛል ፣ የምትሉበት ጊዜ ሊኖራችሁ ይገባል። በቃ ከቤተሰብ ጋር ከጓደኛችሁ ጋር የምትሆኑበት ጊዜ፣ ሃይምሯችሁን Refresh ዘና የምታደርጉበት ግዜ....

በዚህ ጊዜ ከአቀዳችሁት ሰአት ውጪ ላለማሳለፍ መሞከር አለባችሁ ።

ለምሳሌ ሁለት ሰአት ከጓደኛችሁ ጋር አቅዳችሁ ጨዋታው ሲደራ መቼም የሚፈጠረውን ነገር ይገባችኋል ብዬ አስባለሁ። በዚህ ግዜ በጣም ጥንቃቄ አድርጉ፣ በቃ አንድ መስሪያ ቤት ሰዓት ካረፈደ ከደሞዙ ላይ እንደሚቆረጥ ፣ ሁሉ እናንተም ከእቅዳቹት ግዜ ላይ ስታረፍዱ ፣ ከ ማትሪክ ነጥባችሁ እንደሚቆረጥ አስቡ ።


4 ኛው በዚህ ጊዜ ለራሳችሁ ጊዜ የምትሰጡበት ተራ ነው። በዛሬ ቀን ምን ሰራው ፣ ምንስ አወኩኝ፣ በዚህ ተግባሬ ምን አተረፍኩኝ የምትሉበት ግዜ ነው።

የእራሳችሁን ስሜት የምታዳምጡበት ጊዜ።
በተረፈ ፣ እንደየ እምነታችሁ ፣ መዝሙር ፣ መንዙማ ብቻ ብዙ ነገር የምትሰሙበት እና እራሳችሁን የምታረጋጉበት ግዜ ሊኖራችሁ ይገባል ።

ተወዳጆች ሆይ ፣ በእነኝህ በቀሩን 30 ቀናቶች የምታደርጓቸው ተግባራት የእናንተን የወደፊት ህልም ሙሉ ለሙሉ ሊቀይሩ ስለሚችሁ ልብ ልትሏቸው ይገባል ።

በተረፈ መስከረም 9 እስከ 12 በEntrance Hub Website ገጽ ፈተናዎችን ተፈተኑ።

ሰላም ቆዩልኝ

አመሰግናለሁ፣ ደስታ ነበርኩኝ ።

ሁሌም አብረናችሁ ነን ።

D_Marvel Tutorials
የእናንተ ለወዳጆቹ የሚተጋ



D_Marvel Tutorials


Join:
@eruditional
Join:
@eruditional
1.2K views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ