Get Mystery Box with random crypto!

. የመጨረሻው ምዕራፍ የመጨረሻው ጥረት የመጨረሻው ተጋድሎ | E͟n͟t͟r͟a͟n͟c͟e͟ H͟u͟b͟ E͟t͟h͟i͟o͟p͟i͟a͟

. የመጨረሻው ምዕራፍ
የመጨረሻው ጥረት
የመጨረሻው ተጋድሎ


ቀናቶች ቆጠረዋል ፣ አሁን ተቃርበዋል ፣ እያበቁ ነው 30 ቀናት ብቻ ቀርተዋል ፣ የመጨረሻው ምዕራፍ ፣ እንሆ ከዛሬ ይጀምራል ። በዚህ ወራት ውስጥ ቀናት ፣ ሰዓታት ፣ ደቂቃም ጨምሮ ዋጋ አላቸው ።

እነኝህ የመጨረሻዎችሁ አዲሱ ምዕራፍ ቀናቶች ፣ በ4 መሰረታዊ ክፍሎች ልከናወኑ ይገባል ።

በመጀመሪያ ልኩን ለ አራት ቦታ እኩል በመክፈል አስምሩ (quarter) ከዛም ፦

በመጀመሪያው ሳጥን ዛሬውኑ ማለቅ ያለባቸው ነገሮች እናስገባለን (most important and urgent)
እነዚህ ነገሮች የግድ ዛሬ ማከናወን ያሉብን ነገሮች ናቸው።

ለምሳሌ እድር መክፈል ይሄን ምሳሌ ያደረኩበት ምክንያት አንድ ቀን ካመለጠን 30 ቀናትን ጠብቀን ነው መክፈል የምንችለው በዛ ላይ በነቅጣት።

ልብ በሉ፣ ይህ ቀን ዛሬ በዚህች ሰዓት ምናልባት Biologyን ብሎም Unit 3ን የምናጠናበት ፣ የምንረዳበት፣ የምናጠናቅቅበት፣ የምንዘጋጅበት፣ የምንመረምርበት ግዜ ሊሆን ይችላል ። ይህ ግዜ ካለፈ አለፈ ነው አበቃ ፣ Biology Unit 3 ከ Matric Exam ተዘለለ።

ምክንያቱም ምናልባት ቀጣይ ቀን የUnit 2 , የUnit 4 ፣ ወይም የ Chemistry ፣ የHistory ብቻ የሌሎቹም ሊሆን ስለሚችል ፣ የሌሎቹን ቀን ቀንሰን ስንጠቀም በተዘዋዋሪ፣ በሒዎታችን አስፈላጊ የሆነው ነገር ማስቀረታችን እንደሆነ ግንዛቤ ውስጥ አስገቡ ።

ስለዚህ ዋጋ ሊያስከፍሉን የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ልናሰምርባቸው ይገባል ።

በሁለተኛ ሳጥን ውስጥ ደግሞ ዛሬ መፈፀም ያለባቸው ነገር ግን አስቸኳይ ያልሆኑ።

ቀጣይ ቀን መስራት እንችላለን ነገር ግን ዛሬም የመፈፀም አቅም አለን ። ለምሳሌ ከትንሽ ደቂቃዎች በፊት Geography ወይም ደግሞ Chemistry Unit 2 አጥንተናል እንበል ። ጽንሰ ሃሳቡን ተረድተናል ፣ ከ3 ሁሉንም ዋና ዋና የሚባሉ ለMatric የሚያስፈልጉንን ጉዳዮች ተረድተናል ። ነገር ግን ከዚህ Unit ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ያለፉትን Matric Exam አልሰራንም ። ነገር ግን ቀጣይ ቀን መስራት እንችላለን፣ ግን ዛሬ ስንሰራው ሁለት ነገሮችን በዋነኝነት እናገኛለን ።
1ኛ ፡ ለነገ መጨነቁን እናቆማለን(repression)

2ኛ ፡ በትንሽ ነገር በራሳችን መተማመን እነጨምራለን ።

so this is the MOST IMPORTANT PART OF THE DAY.

በ3ኛ ላይ በዚህ በቀሩን ቀናቶች ውስጥ ማከናወን ያሉብን ድርጊቶች አንዱ፡ በዚህ ጊዜ ስራ ጨርሳችሁ "ጨርሻለሁ" አሁን ትንሽ እረፍት ያስፈልገኛል ፣ የምትሉበት ጊዜ ሊኖራችሁ ይገባል። በቃ ከቤተሰብ ጋር ከጓደኛችሁ ጋር የምትሆኑበት ጊዜ፣ ሃይምሯችሁን Refresh ዘና የምታደርጉበት ግዜ....

በዚህ ጊዜ ከአቀዳችሁት ሰአት ውጪ ላለማሳለፍ መሞከር አለባችሁ ።

ለምሳሌ ሁለት ሰአት ከጓደኛችሁ ጋር አቅዳችሁ ጨዋታው ሲደራ መቼም የሚፈጠረውን ነገር ይገባችኋል ብዬ አስባለሁ። በዚህ ግዜ በጣም ጥንቃቄ አድርጉ፣ በቃ አንድ መስሪያ ቤት ሰዓት ካረፈደ ከደሞዙ ላይ እንደሚቆረጥ ፣ ሁሉ እናንተም ከእቅዳቹት ግዜ ላይ ስታረፍዱ ፣ ከ ማትሪክ ነጥባችሁ እንደሚቆረጥ አስቡ ።


4 ኛው በዚህ ጊዜ ለራሳችሁ ጊዜ የምትሰጡበት ተራ ነው። በዛሬ ቀን ምን ሰራው ፣ ምንስ አወኩኝ፣ በዚህ ተግባሬ ምን አተረፍኩኝ የምትሉበት ግዜ ነው።

የእራሳችሁን ስሜት የምታዳምጡበት ጊዜ።
በተረፈ ፣ እንደየ እምነታችሁ ፣ መዝሙር ፣ መንዙማ ብቻ ብዙ ነገር የምትሰሙበት እና እራሳችሁን የምታረጋጉበት ግዜ ሊኖራችሁ ይገባል ።

ተወዳጆች ሆይ ፣ በእነኝህ በቀሩን 30 ቀናቶች የምታደርጓቸው ተግባራት የእናንተን የወደፊት ህልም ሙሉ ለሙሉ ሊቀይሩ ስለሚችሁ ልብ ልትሏቸው ይገባል ።

በተረፈ መስከረም 9 እስከ 12 በEntrance Hub Website ገጽ ፈተናዎችን ተፈተኑ።

ሰላም ቆዩልኝ

አመሰግናለሁ፣ ደስታ ነበርኩኝ ።

ሁሌም አብረናችሁ ነን ።

D_Marvel Tutorials
የእናንተ ለወዳጆቹ የሚተጋ



D_Marvel Tutorials


Join:
@eruditional
Join:
@eruditional