Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ድንቅ ተማሪ ያደገረው ጀበድ ፤ እውነተኛ ታሪክ ክፍል ሁለት( ፪) የግቢው አሳላፊዎችን | E͟n͟t͟r͟a͟n͟c͟e͟ H͟u͟b͟ E͟t͟h͟i͟o͟p͟i͟a͟

አንድ ድንቅ ተማሪ ያደገረው ጀበድ ፤ እውነተኛ ታሪክ
ክፍል ሁለት( ፪)


የግቢው አሳላፊዎችን ያዩትን ለማመን የሚከብድ ታሪክ የትምህረት ቤቱ አስተዳዳሪ ለሆነችው እንስት በመገረም ነገሯት ፣እናቱ አስጠርተውም አወሩ። የሚገርመው ነገር ግን ምንም እንኳ እናትየው ምሳ የምትቋጥርለት ለልጇ ባይኖራትም አንድ ቀን እንኳ ጠይቋት አያቅም!እንዴትስ አልጠየቃትም? ሌላ ህፃን ልጅ እንኳን ምግብን የመሰለ አስፈላጊ ነገር ይቅርና ለከረሚላ እንኳን የሚነዘንዝ ስንቱ ባለበት ሰፈር እሱ እንዴት ይሄን አላደረገም?የሆነው ሆኖ አሁን በትምህርት ቤቱ ወጪ ምሳ ከሚመገቡ ተማሪዎች ዝርዝር ውስጥ ገብቶ ፤ አሁን ያለምንም ችጋር እና ጠኔ ሳይገለው ትምህርቱን በጥሩ ሁኔታ ቀጥሏል!

ስማ ብሮ ፤ ማሙሽ በጣም ስለተባረከ ነው ይሄን ሁሉ ፀጋ የተላበሰው። ከዚ መልዕክት ምን ተማረችሁ ብዬ ብጠይቃችሁ፤ ብዙዎቻችሁ የራሳቹን ብያኔ ልትሰጡ ትችሉ ይሆናል! ነገር ግን ይህ ልጅ የሚከተሉትን ድንቅ ነገር አስተምሮናል ።

የሚፈልገውን ት/ቤት ለመግባት ባሉካዋን ከመጠየቅ ወደኋላ አላለም!

በዚህም በንፈልገው ማንኛውም ነገር ቆራጥ አቋም ወስደን ልንጀምረው ይገባል!

ትምህርት ቤት ከተቀላቀለ ቡኋላ አሪፍ ውጤት ማስመስገቡን አላቆመም

ማሙሽ በርግጥ እቅዱ እዛ ምቹ ት/ቤት መማር አደለም ፤ በዛ ት/ቤት ውስጥ ተምሮ ለውጥ ማምጣት እንጂ ፤ ጋይስ ንቁ እንጂ እቅዳችሁ ካምፓስ ለመግባት እንዳይሆን ፤ ካምፓስ በምትፈልጉት ሞያ ላይ አሪፍ ስንቅ ይዛችሁ ሀገራችሁን ልትቀይሩ ይገባል!

ማሙሽ እናቱን ምሳ ምሳ ብሎ እናቱን አልነዘነዛትም ፤ ይሄ ደሞ የቤተሰብን አቅም አውቆ ባለን ነገር ደስተኛ መሆን እንዳለብን ያስተምረናል ፤ ቤተሰቦቻችን ላይ ጫና አለማሳደር ጥቅሙ ለኛ ነው።እንመረቃለን ፤ ቢያንስ ባይመርቁን እንኳ አይረግሙንም።ይሄ ደሞ ለህይወታችን ለሚመጡ ድሎች በር ከፋች ነው!

ማሙሽ እናቱን ሰው ፊት አላሳ'ጣትም(ይጠብቃል)!

ይህን ያረገው ነገር ደግሞ ትልቅ ህልም ስለነበረው ፣ ነገ ተምሮ የራሱን ኑሮ መኖር ሲጀምር እንኳን እሱን ይቅርና እናቱን ሳይቀር እንጀራ የሚያበላበት ፤ የሚጦርበት አቅም እንደሚኖረው ስለሚያውቅ ዛሬን ተርቦ መማር መረጠ!

ዕድል ያለ ጥረት ባዶ ነው።

ስንቶቻችን ነን ፤ አባቴ ንባብ ለማንበብ ስልክ ያስፈልገኛል በእጅ የሚጠረገውን ስልክ ግዛልኝ ብለን ተቀብለን ፤ በSocial Media ብቻ የምንጋተትበት!

ማሙሽ የሚፈልገው ነገር አሪፍ ት/ቤት መማር ነበር ፣ ለዛም ዕድል በሯን ከፍታለታለች ፤ እሱ ደግሞ ችክል አርጎ በማንበብ እድሉን ተጠቀመባት።

GUYZ የናንተን ዕድል ስንት ሰው እንደሚመኘው ብታቁ ፤ ትጠቀሙበት ነበር!

ስንት ሰው ምሳ እና መክሰስ መብላት እንደሚፈልግ ታውቃላችሁ?

ስንቱ ነው እንደናንተ ሲደብረው TV እያየ EDM Music እየከፈተ ጮቤ እየረገጠ መዝናናት የማይፈልገው?

ክፍለ ሃገር ባያቹ ፤ ዱር ለዱር ሰብል በመሰብሰብ ቤተሰቦቻቸውን እንዴት እነደማያግዙ።በቃ ቀኑን ሙሉ እረፍት የለም፤ ማታ አካላቸው ይዝላል ይተኛሉ።አንዳንድ ቀን ደሞ መብራት አይኖርም ይተኛሉ።አለቀ


ስሚ የኔ እህት እንዳቺ በየወሩ የፕሪሚየም አልግሎት ከቴሌ ገዝቶ በየቀኑ PDF መፃፎችን እያወረደ ማንበብ የማይፈልገው ማን ይመስልሻል ? ሁሉም!!
5ኛው መልዕክት ደግማችሁት እዩት ያልተጠቀማችሁት ወርቃማ ዕድል አለ!

ቢያንስ እስቲ አሁን እንኳን ንቁ አረ ንቁ

ሰላም ሁኑልን ፣ ክፉ አይንካብን ።

ቻናሉን በማስተዋወቅ እገዛቹን ስጡን ፣ እናመሰግናለን
D_Marvel Tutorials

Join @eruditional