Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ድንቅ ተማሪ ያደገረው ጀበድ ፤ እውነተኛ ታሪክ ታሪኩን በቲቪ ነው የሰማውት ፤ ግን የል | E͟n͟t͟r͟a͟n͟c͟e͟ H͟u͟b͟ E͟t͟h͟i͟o͟p͟i͟a͟

አንድ ድንቅ ተማሪ ያደገረው ጀበድ ፤ እውነተኛ ታሪክ


ታሪኩን በቲቪ ነው የሰማውት ፤ ግን የልጁን ስም መናገር ስላተፈለገ አቡሽ እያልን እንጠራዋለን።አቡሽ ጥልቅ ትምህርት የመማር ፍቅር የነበረው የደሃ ልጅ ነው።

ለዚህም ነው አሪፍ ትምህርት ለማግኘት ሰፈራቸው ካለው የግል ትምህርት ቤት ፤ የአስገቡኝ ጥያቄ ሊያቀርብ የወሰነው።የትምህርት ቤቱ ባለቤት እና አስተዳዳሪ የሆነችውን እንስት ሁሌ ከስራ ስትወጣ ሊያወራት አስቦ ብዙ ጊዜ ነው በነዛ በሚያሳዝኑ የጨቅላ አይኖቹን ጎሽሟው የምታልፈው። የዚህ ብላቴና ሁኔታ መደጋገም ያሳሰባት እንስትም ልክ እንደተለመደው ከስራ ስቶጣ አገኘችው ወደ ህፃኑ ቀረብ ብላ ጎንበስ አለችና (ፀጉሩን በእጆቿ እየደባበሰች)''ማሙሽዬ ፤ ምነው ርቦህ ነው አለችው ?

ብላቴናውም ''አይ ፣ አንቺ ትምህርት ቤት መማር ፈልጋለሁ ግን እናቴ የትምህርት ቤቱን ወጪ የምትከፍልበት አቅም የላትም'' አላት እምባ እየተናነቀው።እንስቷም የብላቴናውን የመማር ፍቅር አይታ እሷ ትምህርት ቤት የነፃ ትምህርት እድል (SCHOLARSHIP) ሰጠችዉ። ማሙሽም እንደ ማንኛውም ቤተሰብ ያለው ተማሪ ምሳ ከቤቱ ማምጣት ስለነበረበት ፤ ምሳ መቋጠር የናቱ ድርሻ ሆነ።

ማሙሽ አዲስ በገባበት ትምህርት ቤት ውስጥ በመንፈቅ አመቱ አሪፍ ውጤት ማስዝገብ ጀመረ። ከዛች የመጀመሪያ ስኬት ጀምሮ ማን ይቻለው? ይበልጥ እያየለ መጣ ፣ በቃ እንዳለ ውጤቱን ሰቃቀለው!

ነገር ግን ይሄ ሁሉ ሆኖ እያለ ፣ አንድ ቀን እንኳ የተቋጠረለትን ምሳ ከጓደኞቹ ጋር በልቶ አያቅም። በቃ ልክ ምሳ ሰዓት ሲደርስ የተቋጠረለትን ምሳ ዕቃ ይዞ የት እንደምገባ አይታወቅም። ልክ ሲደወል ነው የሚመጣው።''ምን አይነት ስግብግብ ነው?'' ጓደኞቹ ጠሉት!

ነገሩ ሁሌ የተደጋገማባቸው የትምህርት ቤቱ አሳላፊዎቹ ማሙሽን በቅርብ ይከታተሉት። ዛሬም እንደ ሁል ጊዜው ማሙሽ የምሳ እቃውን ለብቻው ይዞ ከጓዶቹ ተነጠለ ፤ ድብቅ የሆነ ቦታ ላይ ሲደርስ ጋደም ብሎ ምሳ ዕቃውን በእጁ እያነከባለለ ይጨወት ጀመር!ምሳ ዕቃው በዶ መሆኑ ነው!!''ይሄን ተደብቀው የሚመለከቱ የትምህርት ቤቱ አሳለፊዎች የበታችነት ስሜት በማይነበብው የማሙሽ ፊት ላይ የደስታ እና የምስግና ስሜት ሲመለከቱ አለቀሱ ፤ ተሰማቸው!

ማሙሻም ልክ ድሮ እንደሚያረገው ወደ ክላስ የሚል ደውል ሲደወል ባዶዋን ምሳ እቃ ይዞ ወደ ክፍሉ ተመለሰ!

ይቀጥላል........