Get Mystery Box with random crypto!

EBC(Ethiopian Brodcasting Corboration(EBC)

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebc_news_zena — EBC(Ethiopian Brodcasting Corboration(EBC) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebc_news_zena — EBC(Ethiopian Brodcasting Corboration(EBC)
የሰርጥ አድራሻ: @ebc_news_zena
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.01K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-05-09 23:24:37 የኒኩሌር ጦርነትን የሚቋቋመው የሩሲያ “የምጽአት ቀን” አውሮፕላን አውሮፕኑ ማንኛውንም አይነት የኒኩሌር ጥቃተን መቋቋም የሚችል ነው

“የዓለም ፍጻሜ ይሆናል” በሚባለው የኒኩሌር ጦርነት ወቅት አውሮፕላኑ የፕሬዝዳንት ፑቲን ማዘዣ ሆኖ ያገለግላል

የኒኩሌር የጦር መሳሪያን መቋቋም የሚችለው እና “የምጽአት ቀን” (ዶምስዴይ) የሚል መጠሪያ የተሰጠው የሩሲያ አውሮፕላን።

በሩሲያ “ኢሊዩሺን አይ.ኤል-80” የሚል መጠሪያ ያለው አውሮፕላኑ የዓለም ፍጻሜ ሊሆን ይችላል ተብሎ በሚነገርለት የኒኩሌር ጦርነት ወቅት የሩሲያ ፐሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ያለምንም ችግር ሀገሪቱን እንዲመሩ ያስችላቸዋል ተብሏል።

እንዲሁም ፕሬዝዳንቱ ጦራቸው የኒኩሌር ማሳሪያ ጥቃት እንዲፈጽሙ ትእዛዝ እንዲሰጡ የሚያስችላለቸው መሆኑንም ነው የተገለፀው።

ትንሹ የሩሲያ ቤተ-መንግስት (ክሬምሊን) ነው የተባለለት አውሮፕላኑ በኒኩሌር ጥቃት ወቅት ፕሬዝዳንት ፑቲን ከየትኛውም የኒኩሌር ጉዳት ለመጠበቅ የሚረዳ ነው ተብሏል።

“የምጽአት ቀን” አውሮፕላን የሚባለው ኢሊዩሺን አይ.ኤል-80 የመጀመሪያ በረራውን በፈረንጆቹ በ1987 ያደረገ ሲሆን፤ በ2008 ደግሞ የማሻሻያ እና ማዘመኛ ስራዎች ተሰርተውለታል።

የአውሮፕላኑ ቁመት 60 ሜትር የሚረዝም ሲሆን፤ የክንፉ ስፋት ደግሞ 48 ሜትር ነው።

በአየር ላይ እያለ ነዳጅ ሚሞላለት አውሮፐልኑ በሰዓት 850 ኪሎ ሜትር ፍጥነት እንደሚጓዝ እና ያለማቋረጥ ከ3 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር በላይ የሚበር መሆኑ ተነግሯል።

በኢሊዩሺን ኩባያ የተመረተው አውሮፕላኑ ኩዝኔቶቭ ኤን ኬ-86 የተባለ ሞተር የሚጠቀም ሲሆን፤ አሁን ላይ ሩሲያ በአጠቃላይ 4 ምጽአት ቀን አውሮፕላኖች አሏት።

የአሜሪካ “የምጽአት ቀን” አውሮፕላን

አሜሪካም ከሩሲያ “የምጽአት ቀን” (ዶምስዴይ) አውሮፕላን ጋር የሚገዳደር የኒኩሌር ጦርነትን የሚቋቋም አውሮፕላን እንዳላት ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል።

GRIM99” የሚል መለያ ኮድ ያለው አውሮፕላኑ “በራሪው ፔንታጎን” የሚል ቅጽል ስም ያለው ሲሆን፤ በኒኩሌር ጦርነት ወቅት የዘመቻዎች መዘዣ ማዕከል በመሆን ያገለግላል ተብሏል።

የቦይንግ 747 ምርት አውሮፕላኑ ብሄራዊ የአደጋ ጊዜ የአየር ማዘዣ ማእከል በሚል ይፋዊ ስሙ የሚታወቅ ሲሆን፤ አራት መሰል አውሮፕላኖች ብቻ ናቸው ያሉት።

አውሮፕላኑ በአየር ወለዶች በሰማይ ላይ እያለ ነዳጅ እየተሞላለት ያለማቋረጥ ለ150 ሰዓታት መብረር ይችላል የተባለ ሲሆን፤ አራት የጄነራል ኤሌክትሪክ ሞተሮች እና በጣም ከፍተኛ መጠን የመያዝ አቅም ያለው የነዳጅ ታንከርም ተገጥሞለታል።

67 ሳተላይት ዲሾች የተገጠሙለት አውሮፕላኑ፤ ይህም የመከላከያ ሚኒስትሩ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከሚገኙ የአሜሪካ የጦር መርከቦች፣ ሰርጓጅ መርከቦች፣ የአየር እና የመድር ጦር ኃይሎች ጋር ለመገናኘት የሚያስችላቸው ነው።
537 views20:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 19:59:07 በወላይታ ዞን የ11ኛ ክፍል ተማሪ ኢ ቲ አር ኤስ 1 ኬ ኤም የተባለ ሮኬት ሰራ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን የ11ኛ ክፍል ተማሪ ኢ ቲ አር ኤስ1 ኬ ኤም የተባለ ሮኬት በዩኒቨርሲቲው ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ትብብር መሰራቱ ተገልጿል።

ወጣት ሳሙኤል ዘካሪያስ በወላይታ ዞን የ11ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት የገንዘብ ድጋፍና ትብብር( ETR S1KM ተብሎ የሚጠራ ሮኬት መስራቱን በዛሬው እለት አስታውቋል።

ወጣት ሳሙኤል ዘካሪያስ ከዚህ በፊት ከአከባቢው ያገኘውን የተለያዩ ቁሳቁስ በመጠቀም ኤክስካባተር መኪና እንዲሁም የቆሻሻ ማፈሻ መኪና ሰርቶ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በቅርቡም የተሳካ የማስወንጨፍ ሙከራ እንደሚያደርግ ተመላክቷል።

ወጣቱ የሰራው ሮኬት አንድ ኪሎ ሜትር ድረስ የመወንጨፍ አቅም ያለው መሆኑንና፥ ሮኬቱን የሚሸከመው መኪናም አብሮ መሰራቱ ታውቋል።

ለወጣት ሳሙኤል ዘካሪያስ የተደረገው ድጋፍ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መገለጹን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል።
592 views16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 20:40:38
ሜጀር ጀነራል ገ/መድህን ፍቃዱ (ወዲ ነጮ) አረፉ!

የመከላከያ የኮሚኒኬሽን ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር መምሪያ ሀላፊ የነበሩት ሜ/ጀ ገ/መድህን ፍቃዱ ጥቅምት 24ቀን 2013 ዓ/ም መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ የሬዲዮ ግንኙነትን በማቋረጥ እና የሬዲዮ መሳሪያ ለህውሐት ወታደራዊ ቡድን አሳልፈው ሰተዋል ተብለው በዓቃቢህግ የቀረበባቸውን ክስ በቃሊቲ ማረሚያቤት ሁነው ጉዳያቸውን እየተከታተሉ ይገኙ ነበር።

ሆኖም በዛሬው ዕለት በቃሊቲ በማረሚያ ቤቱ የቤተሰብ ጥየቃ ሰዓት ሊጠይቋቸው ከሄዱ ከባለቤታቸውና ከልጆቻቸው እየተጫወቱ በነበሩበት ወቅት በድንገት እራሳቸውን ስተው በመውደቅ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል።
639 views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 11:44:24 በጦርነትና በግጭት ውስጥ ሆነው ተፈትነዋል ተብለው የተለዩ የ12ኛ ክፍል የማለፊያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በዚህ አመት ይፈተናሉ - ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በጦርነት እና በግጭት ውስጥ ሆነው ተፈትነዋል ተብለው የተለዩ እና የ12ኛ ክፍል የማለፊያ ውጤት ያላመጡ በዚህ ዓመት በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እንደ መደበኛ ተማሪ ሆነው መፈተን እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር፣ ሁሉም ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በጋራ መግለጫ እየሰጡ ነው።
846 views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 17:56:09 ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተሳካ ሮኬት አስወነጨፈ።

ደብረ ታቦር: ሚያዝያ 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከሦስተኛው ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደበው የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የአፄ ቴዎድሮስን የዕውቀት ጥያቄ የመመለስ ራዕይ አንግቦ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው የአፄ ቴዎድሮስን 154ኛ ዝክረ ሰማእት ምክንያት በማድረግ አሞራ ገደል በተባለ ሥፍራ የተሳካ የሮኬት ማስወንጨፍ
ሙከራ አካሂዷል።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ያደረገው ሙከራ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ባለፉት ዓመታት የተለያዩ የቴክኖሎጅ ምርምሮችን ሲያካሂድ መቆየቱን የዩኒቨርሰቲው ፕሬዚደንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው ተናግረዋል።

ይህ ምርምር አድጎ ለሀገሪቷ የሕዋ ሳይንስ ምርምር አጋዥ እንዲሆን ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ሌላው በዝክረ ሰማእት መታሰቢያ ዕለቱ የአፄ ቴዎድሮስን የመድፍ ሥራ የሚያስታውስ ምስለ ሴባስቶፖል መድፍ ተሰርቶ በደብረ ታቦር ከተማ የመተኮስ ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል።
815 views14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-14 20:48:41 የመብረቅ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አጠፋ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመብረቅ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የሆብቻ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ህዝቅኤል ኦይዳ እንደገለጸት፥ በትናንትናው ዕለት በአካባቢው ከጣለው ከባድ ዝናብ ጋር ተቀላቅሎ የወረደው መብረቅ ሁለት ሰዎችን ገድሏል።

እንዲሁም በሌሎች ሶስት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ምክትል ኢንስፔክተር ህዝቅኤል ተናግረዋል።

በመብረቅ አደጋው ህይወታቸው ያለፈው የ30 እና 35 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሰዎች ናቸው ብለዋል።

በአካባቢው የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የወረደው መብረቅ በመኖሪያ ቤቶችና አጥር ላይ ጉዳት ማድረሱንም የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።

በአካባቢው የዝናብ ወቅት እየደረሰ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከመሰል የተፈጥሮ አደጋዎች ራሱን እንዲጠብቅ ምክትል ኢንስፔክተር ህዝቅኤል አሳስበዋል
702 views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ