Get Mystery Box with random crypto!

EBC(Ethiopian Brodcasting Corboration(EBC)

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebc_news_zena — EBC(Ethiopian Brodcasting Corboration(EBC) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebc_news_zena — EBC(Ethiopian Brodcasting Corboration(EBC)
የሰርጥ አድራሻ: @ebc_news_zena
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.01K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-13 12:58:24
አሳዛኝ ዜና

ድምፃዊ ዳዊት ነጋ በድንገተኛ ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለየ

ወዛመይ ፣ ዘዊደሮ እና በሌሎች የትግረኛ ዘፈኖች የሚታወቀው ወጣት ድምፃዊ ዳዊት ነጋ ዛሬ ማረፉ ተሰምቷል።

ድምፃዊ ዳዊት አዲስ አበባ በሚገኘው በአዲስ ሒወት ሆስፒታል ላለፉት አራት ቀን ህክምና ሲከታተል ነበር ሲሉ ከዘፋኙ ጋር ቅርበት ያላቸው ወዳጆች ገልፀዋል። ለወዳጅ ዘመዶቹ እና አድናቂዎቹ መጽናናትን እንመኛለን።
510 viewsedited  09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 12:12:11
ዶ/ር ሊያ ታደሰ የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆነው ተመረጡ

ከቀናት በፊት በተደረገው የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ምርጫ ላይ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ዳግም መመረጥ የተቃወመችው ኢትዮጵያ ከግንቦት 14 2014 ዓ.ም ጀምሮ በጄኔቭ እየተካሄደ በሚገኘው 75ኛው የአለም ጤና ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ዶ/ር ሊያ ታደሰን የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል አድርጋ አስመርጣለች።

ከመላው ዓለም የተውጣጡ 34 በጤና ዘርፍ ከፍተኛ እውቀት ያላቸው እና በአባል ሀገራት የተወከሉ ባለምያዎችን በሚይዘው ቦርድ ውስጥ ከአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሰባት ሀገራት ተወካዮቻቸውን ያስመረጡ ሲሆን እነኚህ ተመራጮች ለቀጣዮቹ 3 ዓመታት ድርጅቱን ያገለግላሉ። የቦርዱ ዋነኛ ተግባር የጠቅላላ ጉባዔውን ውሳኔ እና ፖሊሲ ማስፈጸም እንዲሁም ምክረ-ሀሳብ ማቅረብ እና ስራዎችን ማመቻቸት ነው።
709 views09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 21:33:29
በሃሰተኛ ገንዘብ ነዳጅ ቀድቶ ለማምለጥ የሞከረው አሽከርካሪ ከቆመ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

የትራፊክ አደጋው የደረሰው ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ/ም ከሌሊቱ 6፡30 ሰዓት ገደማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ሚካኤል አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ላይ ነው ተብሏል።

የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1- 30262 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ ከጀሞ 1 አቅጣጫ ወደ ሚካኤል አደባባይ እየተጓዘ 67 ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ ነዳጅ ማደያ ውስጥ ነዳጅ ሊቀዳ መግባቱን በአዲስ አበባ ፖሊስ የትራፊክ አደጋ ምርመራ ቲም ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ስጦታው ወልዴ ገልፀዋል።
569 views18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 20:45:43
ቻይና “ለአሜሪካ ከባድ ማስጠንቀቂያ ነው” ያለችውን ወታደራዊ ልምምድ በታይዋን አቅራቢያ አደረገች

የቻይና ጦር ቃል አቀባይ በትናትናው እለት እንዳስታወቀው ቻይና እራሷን በራስ የምታስተዳድር ደሴት ላይ ያላትን ቁርጠኝነት ለአሜሪካ ለማሳየት በቅርቡ በታይዋን አቅራቢያ ተከታታይ ወታደራዊ ልምምዶችን አድርጋለች።

የቻይና ጦር የምስራቃዊ እዝ በታይዋን ዙሪያ የውጊያ ዝግጁነት ልምምዶችን እና ሌሎች የስልጠናዎችን በባህር እና አየር ላይ ማካሄዱንም የወታደራዊ እዙ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሺ ዪ ተናግረዋል። ልምምዱ አሜሪካ ለታይዋን እውቅና ለመስጠት እያደረገችው ላለው እንቅሰቃሴ “ከባድ ማስጠንቀቂያ” መሆኑንም ቃል አቀባዩ ገልፀዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት በእስያ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኀገራቸው ታይዋንን ለመጠበቅ ኃይል ልትጠቀም እንደምትችል መናገራቸው ይታወሳል።
520 views17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 18:10:19 የዚምባብዌው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀገራቸው ኮ/ል መንግስቱ ሀይለማርያምን ለኢትዮጵያ አሳልፋ ልትሰጥ እንደምትችል ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ላይ ገልጸዋል:: "የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት የዚምባብዌ መንግስትን ቀርቦ ጥያቄ ካቀረበ አስፈላጊው እርምጃ ተወስዶ ተገቢው ጥያቄ መልስ ያገኛል" ነው ያሉት የዚምባብዌው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ኮረኔል መንግስቱ ሆይ የዚምባቤ መንግስት ለኢትዮጵያ አሳልፋ እስኪሰጥህ አትጠብቅ በገዛ ፍቃድህ ወደ ምትወዳት ሀገርህ ከነቤተሰብህ በመግባት ቀሪ እድሜህን በሀገርህ ላይ አሳልፍ
659 views15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 13:18:33 ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ያሉበትን ማወቅ እንዳልቻሉ ባለቤታቸው ተናገሩ

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ አዲስ አበባ ውስጥ ከቤታቸው እንደወጡ አለመመለሳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ለቢቢሲ ገለፁ።

ወ/ሮ መነን ስለ ባለቤታቸው ሲናገሩ ትናንት ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ.ም. ከቤታቸው 5፡15 አካባቢ የወጡት ከጓደኛቸው ጋር ቀጠሮ እንደነበራቸው ገልፀው መሆኑን ያስረዳሉ።

ከዚያ በኋላ ግን ወደ ቤታቸው ባለመመለሳቸው ደጋግመው ወደ ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ቢደውሉም ምላሽ አለማግኘታቸውን ይናገራሉ።

ጄኔራል ተፈራ ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ ያገለገሉ ሲሆን እንዲሁም በቅርቡ የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ ሆነው መስራታቸው ይታወሳል ።

እንደ ወ/ሮ መነን ገለፃ ከሆነ ጄኔራል ተፈራ ያገኟቸው ሰዎች በዕለቱ አስከ 10 ሰዓት ድረስ አብረው መቆየታቸውን እና ከዚያ በኋላ እንደተለያዩ ነግረዋቸዋል።

ከዚያ በኋላ ግን የደረሱበትን ለማወቅ እንዳልቻሉ ባለቤታቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

ጄኔራል ተፈራ ሞሞ ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥነት ከተነሱ በኋላ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ላይ በመቅረብ አስተያየታቸውን ይሰጡ ነበር።

ወ/ሮ መነን የባለቤታቸውን መጥፋት አስመልክቶ ወደ ፌደራል ወንጀል ምርመራ እንዲሁም አዲስ አበባ ፖሊስ በመሄድ ቢጠይቁም ግለሰቡ "በቁጥጥራቸው ስር እንደማይገኝ" እንደገለፁላቸው ይናገራሉ።

በአሁኑ ሰዓትም ባለቤታቸውን ለማግኘት ሊኖሩበት ይችላሉ ወደተባሉ የተለያዩ የደኅንነትና የፀጥታ ተቋማት በመሄድ ፍለጋቸውን መቀጠላቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

ጄኔራል ተፈራ ማሞ ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ናቸው።

ጄኔራል ተፈራ የስኳር ሕመምተኛ መሆናቸውን የገለፁት ባለቤታቸው የታዘዘላቸውን መድኃኒት እየወሰዱ አንደነበር አመልክተው፣ መድኃኒታቸውን ካልወሰዱ አንደሚታመሙ በመጥቀስ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከሚኖሩበት ባሕርዳር ወደ አዲስ አበባ የመጡት በእግራቸው ውስጥ የሚገኙትን ጥይቶች በተመለከተ የሕክምና ክትትል ለማድረግ እንደነበረም ጨምረው አስረድተዋል።

"እስሩን ለምዶታል ያለፈበትም ነው፤ የሚያሳስበን የጤናው ሁኔታ ነው" ብለዋል።

የጄነራሉን መሰወር በተመለከተ የፌደራልም ሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስካሁን ያሉት ነገር የለም።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባል ሆነው ለዓመታት በከፍተኛ መኮንንነት ያገለገሉት ብርጋዲዬር ጄነራል ተፈራ ማሞ ከአስር ዓመት በፊት መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ አሲረዋል በሚል ከሌሎች ጋር ተከሰው ለዓመታት በእስር ላይ ቆይተዋል።
667 views10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 10:16:46
ሃናን ትባላለች የ25 አመት ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነች፣ ከእጮኛዋ ጋር ኒካ ለማሰር ስላሰቡ አዲስ አበባ በመምጣት ለሰርጋቸው የሚያስፈልጋቸው እቃዎች ለመግዛት በአንድ ሆቴል 8ኛ ፎቅ ማረፊያቸውን አደረጉ ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ከታዲያስ አዲስ ጋር በነበረው ቆይታ።
በሆቴሉ እንዳሉ በመካከላቸው አለመግባባት ተፈጥሮ ይጨቃጨቃሉ እሱ ክፍሉን ጥሎ ወጣ ከቆይታ በኋላ የሆቴሉን ባልደረባ "እስቲ ሂድና ቼክ አድርጋት ቅድም ተበሳጭታ ነበር" ብሎ ይልከዋል፣ እሱም ሄዶ ሲመለከት ከ8ኛ ፎቅ ራሷን ወደ 3ኛ ፎቅ ወርውራ ህይወቷ እንዳለፈ ታውቋል ሲል ፖሊስ ተናግሯል።
558 views07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 17:50:56 በፍሎሪዳ ምንም የማብረር ልምድ የሌለው መንገደኛ በህመም ከወደቀው ፓይለት አውሮፕላኑን ተረክቦ በሰላም ማሳረፍ ቻለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የበረራ ልምድ የሌለው መንገደኛ አውሮፕላኑን በአሜሪካ ፍሎሪዳ አውሮፕላን ማረፊያ አሳረፈ፡፡

የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪው ሮበርት ሞርጋን ግለሰቡ ከሚያበረው አውሮፕላን መልዕክት ሰማ ከበሃማስ በኩል፡፡

"አውሮፕላኑን እንዴት እንደማበር ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም" የሚለው የአብራሪነት ልምድ ያልነበረው የአውሮፕላኑ ተጓዥ አውሮፕላኑ ውስጥ እንደማንኛውም ተጓዥ በሰላም እየተጓዘ ነበር ይህ ክስተት እስከሚፈጠር፡፡

ሁኔታው ያልተለመደና አስደንጋጭ ቢሆንም የህይወት ጉዳይ ነውና ፓይለቱ ያጋጠመው የጤና እክል በአብራሪነት የሚያስቀጥለው ባለመሆኑ የአብራሪነት ልምድ ያልነበረው ተጓዥ አብራሪ ሊሆን ግድ ሆነ፡፡

አውሮፕላኑን እንዴት መቆጣጠርና አደጋ ሳይደርስ ማሳረፍ እንደሚችል ምንም የማያውቀው ተሳፋሪ ወደአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጥሪ አደረገ፡፡

ባደረገው የእገዛ እፈልጋለሁ ጥሪውም ሁኔታውን ለአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አስረዳ፡፡

በወቅቱ በቦታው ያልነበረው የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪው ሞርጋን ከባልደረቦቹ መልዕክት ደረሰው፡፡

"ፓይለቱ አውሮፕላኑን የማብረር አቅም የለውም … ተሳፋሪዎች አውሮፕላኑን እያበረሩ ነው… ምንም የማብረር ልምድ የላቸውም" ሲል ባልደረባው እንደነገረው ይገልጻል የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪው ሞርጋን፡፡

ልምድ የሌለው ተጓዥ አብራሪው በወቅቱ የተረጋጋ እንደነበር ገልጾ ፥ "አውሮፕላኑን እንዴት እንደማበረው አላውቅም ... እንዴት ማሳረፍ እንዳለብኝም አላውቅም" ሲልም ለአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪው ይነግረዋል፡፡

ሞርጋን ይህን ተከትሎም ልምድ የሌለው መንገደኛ አብራሪውን ደረጃ በደረጃ ይነግረው ጀመር ምን ማድረግ እንዳለበት።

ሞርጋን አውሮፕላኑን በአካባቢው ወደሚገኝ አውሮፕላን ማረፊያ ለመምራት ቁልፍ ውሳኔ ላይ ደረሰ ፤ ውሳኔው የግድ በመሆኑ ተሳፋሪው የአውሮፕላን አብራሪ በአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪው እገዛ ወደታቀደለት አካባቢ መገስገስ ጀመረ።

በመጨረሻም አውሮፕላኑ ምድር ነካ ፤ ይህን በረራም ሞርጋን ልምድ የሌለው አውሮፕላን አብራሪው አውሮፕላኑን ያሳረፈበት መንገድ ፍጹም ስኬታማ ነው ሲል አድናቆቱን ገልጿል፡፡

ሞርጋን አክሎም ይህ በመሳካቱ እና ማንም ሰው ስላልተጎዳ በጣም ደስተኛ ነኝ ሲልም ስሜቱን ለሲ ኤን ኤን አጋርቷል፡፡

ፓይለቱ የጤና ችግር ገጥሞት እንደሆነ የተጠቀሰ ሲሆን ፥ ዝርዝር ጉዳዩን ግን ማወቅ እንዳልተቻለ ነው የፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር በመግለጫው የተናገረው።

ከሁነቱ በኋላ ሞርጋን አዲሱን የበረራ ተማሪውን አግኝቶ እንዳመሰገነው ገልጾ ፥ እኔ ስራዬን ነው የሰራሁት እሱ ግን ጀግና ነው ሲልም አሞግሶታል፡፡
619 views14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 17:50:16
478 views14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 23:26:11
የኒኩሌር ጦርነትን የሚቋቋመው የሩሲያ “የምጽአት ቀን” አውሮፕላን አውሮፕኑ ማንኛውንም አይነት የኒኩሌር ጥቃተን መቋቋም የሚችል ነው “የዓለም ፍጻሜ ይሆናል” በሚባለው የኒኩሌር ጦርነት ወቅት አውሮፕላኑ የፕሬዝዳንት ፑቲን ማዘዣ ሆኖ ያገለግላል የኒኩሌር የጦር መሳሪያን መቋቋም የሚችለው እና “የምጽአት ቀን” (ዶምስዴይ) የሚል መጠሪያ የተሰጠው የሩሲያ አውሮፕላን። በሩሲያ “ኢሊዩሺን አይ.ኤል-80”…
536 views20:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ