Get Mystery Box with random crypto!

EBC(Ethiopian Brodcasting Corboration(EBC)

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebc_news_zena — EBC(Ethiopian Brodcasting Corboration(EBC) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebc_news_zena — EBC(Ethiopian Brodcasting Corboration(EBC)
የሰርጥ አድራሻ: @ebc_news_zena
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.01K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-10-21 13:36:40
ተማሪ ፅጌረዳ ግርማይን በስለት ወግቶ የገደለው ተማሪ ተፈረደበት

(የኢትዩትዩብ እለታዊ መረጃዎች)
የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ተማሪ ፅጌረዳ ግርማይን በስለት ወግቶ የገደለው ተማሪ በ22 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ ቤት የውሳኔ ማሻሻያ ማድረጉን ገለፀ።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ  ተማሪ ተከሳሽ ብሩክ በላይነህ ፤ " ያቀረብኩትን የፍቅር ጥያቄ አልተቀበለችም ፣ ሌላ ፍቅረኛ ይዛ ውጪ ልትወጣ ነው። " በሚል ስሜት ተነሳስቶ ተማሪ ጽጌረዳ ግርማይን አካል 9 ጊዜ በስለት ወጋግቶ የመግደል ወንጀል ፈፅሟል።

በቀድሞው አጠራር የጋሞ ዞን ዐቃቤ ህግ የመሠረተውን የወንጀል ክስ ተመልክቶ ግራና ቀኙን ሲያከራክር የቆየው የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀደም ሲል በቀን 19/10/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተከሳሽ ላይ የ17 ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት ውስኖ እንደነበር ይታወሳል።

የዞኑ ዐቃቤ ህግ በከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ቅር በመሰኘቱ  ይግባኙን ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ሲከታተል ቆይቷል።

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የበየነው የቅጣት ውሳኔ ከተፈፀመው ወንጀል  አኳያ ተገቢነት ያለው ሆኖ ባለመገኘቱ የሥር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ  አሻሽሎ ሰሞኑን በዋለው ችሎት  በተከሳሽ  ላይ የ22 ዓመት ፅኑ እሥራት የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።
583 views10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-13 19:25:46 በጅማ ዞን ቀርሳ ወረዳ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመብረቅ አደጋ እናትና አባትን ጨምሮ የሶስት ቤተሰብ አባላት ህይወት ማለፉን ፖሊስ ገለጸ፡፡

የቀርሳ ወረዳ ፖሊስ እንዳስታወቀው ÷ትናንት ሌሊት 9 ሰዓት ላይ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ በተከሰተ የመብረቅ አደጋ ሶስት የቤተሰብ አባላት ህይወት አልፏል።

በአደጋው የአራት አመት ህጻን ልጅን ጨምሮ ወላጅ እናትና አባትም ህይወታቸው ማለፉን በወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት የወንጀል ክትትል መርማሪ ኢንስፔክተር አህመድ ከማል ተናግረዋል።

አሁን እየጣለ ያለው ዝናብ ለእንደዚህ አይነት አደጋ ስለሚያጋልጥ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።
Via fm
821 viewsedited  16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 18:12:29
ተፈታኝ ተማሪዎች ተረጋግተው ወደ ግቢ እንዲመለሱ ጥሪ ቀረበ

የሲዳማ ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ በደቡብ ቴሌቪዥን ዜና 24 ላይ ቀርበው በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጠረውን ድንገተኛ አደጋ አሁናዊ ሁኔታ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል

እንደ አቶ አለማየሁ ገለጻ አደጋው የደረሰው በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ እና በቴክኖ ግቢ መካከል ያለው የተማሪዎች መሸጋገሪያ ድልድልይ በመደርመሱ ነው፡፡

415 ተማሪዎች በድልድዩ ላይ ሆነው ድልድዩ መደርመሱን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ 310 ተማሪዎች ቀላልና 110 ተማሪዎች ላይ መካከለኛና ከባድ ጉዳት ደርሷል ብለዋል፡፡

20 ተማሪዎች የአጥንት ስብራተ ያጋጠማቸው ሲሆን 85 በሚሆኑት ላይ ቀላል አካላዊ ጉዳት መድረሱንም አብራርተዋል፡፡

የአንድ ተማሪ ህይወት በአደጋው ማለፉንም ነው የተናገሩት፡፡
ተጎጂዎች በከተማው በሚገኙ የሪፌራል፣ ያኔት፣ አዳሬ እና ሞቲቴ ፉራ ሆስፒታሎች ህክምና እየተሰጣቸው ይገኛል፡፡

ተማሪዎች ሳይደናገጡ ተረጋግተው ወደ ግቢው እንዲመለሱ ጥሪ ያቀረቡት አቶ አለማየሁ ፈተናውን አስመልክቶ የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትን መመሪያ እንዲከታተሉ አሳስበዋል፡፡ በተመሳሳይ የተማሪ ወላጆችም ሳይረበሹ ተማሪዎችን በማረጋጋት ሂደት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የክልል መንግስት በጸጥታው ረገድ የሚጠበቅበትን እየተወጣ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ ደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት
183 views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 11:22:00 የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ድልድይ ተደርምሶ በ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱንና በደረሰው ጉዳት ማዘኑን የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ

ዛሬ ጠዋት የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ዋናውን ግቢ እና የቴክኖሎጂ ካምፓስ ግቢን የሚያገኛኘው ድልድይ ተደርምሶ በ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱንና በደረሰው ጉዳት ማዘኑን የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል፡፡

የሲዳማ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እንዳስታወቁት እስከአሁን ባለው ሂደት በጉዳቱ የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ፣ ሁለት ከባድ ጉዳት እና ሌሎች መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸዉ ይገኛል፡፡

እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲከሰቱ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጆችና ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ ከሚመለከተው አካል ብቻ በማግኘት እንዲያረጋግጡና እንዲረጋጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን
via FM
106 views08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 22:19:49
የ12ኛ ክፍል ተፈታኟ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ወንድ ልጅ ተገላገለች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመፈተን ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደበች ተማሪ ወንድ ልጅ በሠላም መገላገሏ ተገለፀ።

ከቡርቃ ዲምቱ መሰናዶ ትምህርት ቤት ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደበችው ተማሪ ጽጌረዳ አበራ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን ዩኒቨርሲቲ ከደረሰች በኋላ ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላለች።

ተማሪ ጽጌረዳ አበራ በዛሬው ዕለት ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ወንድ ልጅ በሰላም መገላገሏን ነው የዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን እና የሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ኮማንድ ፖስት ዘርፍ የህክምና ግብረ ሀይል አስተባባሪ ዶክተር ሁሴን መሀመድ የገለጹት፡፡

በአሁኑ ሰዓት እናትና የተወለደው ህፃን በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡

Via FB
228 views19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-30 09:07:05
243 views06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-30 09:05:37
በአዲስ በፋብሪካ ላይ በደረሰ ቃጠሎ 60 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ።

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ስሙ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ ፋብሪካ ላይ በደረሰ ከፍተኛ የእሳት አደጋ 60 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽንን ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ቃጠሎውን መቆጣጠር መቻሉን ለኢቢሲ የተናገሩት የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ የአደጋው መንስኤ አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡ ከቀኑ 9 ሰዓት ከ45 በተነሳው የእሳት አደጋ 1 የእሳት አደጋ ሰራተኛ ከባድ ጉዳት ሲደርስበት 3 የአካባቢው ነዋሪዎች ደግሞ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል፡፡

የእሳት አደጋው የደረሰበት ፋብሪካ በመንደር ውስጥ የሚገኝ መሆኑ እንዲሁም የተቃጠለ ዘይት ያለበቂ ጥንቃቄ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ተከማችቶ መገኘቱ ለአደጋው መባባስ ምክንያት ሆኗል ብለዋል። 2 ሰዓት የቆየውን አደጋ ለመቆጣጠር 10 የእሳት አደጋ መኪናዎች፣ 2 አምቡላንሶች፣ 80 የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች እና የአካባቢው ማኅበረሰብ የጋራ ርብርብ ማድረጋቸውንም አስታውቀዋል።

በዚህም 350 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ማትረፍ መቻሉን ገልፀዋል፡፡
250 views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 15:41:41
ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ አረፈ።
ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ባደረበት ህመም ምክንያት ማረፉን የቅርብ ወዳጆቹ ለኢፕድ ገልጸዋል።

ድምፆዊ ማዲንጎ አፈወርቅ እንደማንኛውም ድምፆዊ ዘመን የሚሻገር ስራ ባለቤት ነው።

ኢትዮጵያ በተፈተነችበት ወቅት እያመመው ግንባር ድረስ በመሔድና ማሰልጠኛም ምልምሎችን በማነቃቃት የራሱ የሆነ ታሪክ የሰራ አርቲስት ነበር።

አሚኮ በድምጻዊው ህልፈት የተሰማውን ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹ፡ ለአድናቂዎቹና ወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ይመኛል።

Via አሜኮ
223 views12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 10:40:34
አዲስ አበባ የሚዘጉ መንገዶች

ሰኞ መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ የሚካሄደውን የደመራ የመለኮስ ስነ-ስርአት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ፦

•  ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም  ከኤድናሞል በአትላሳ ወደ ካዛንቺስ የሚወስደው መንገድ  ኡራኤል አደባባይ

• ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አጎና ሲኒማ

• ከጎፋ በአዲሱ መንገድ ወደ  ለገሃር  ለሚመጡ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛ ላይ

• ከቡልጋሪያ በሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር የሚሄዱ ጠማማ ፎቅ አካባቢ

•  ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ እንዲሁም ከጦር ኃይሎች በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ለገሃር  የሚወስደው ሚክሲኮ አደባባይ

• ከተከለ ሃይማኖት በጎማ ቁጠባ  ወደ ለገሃር ሰንጋተራ 40/60 ኮንደሚኒዬም አካባቢ

• ከጌጃ ሰፈር ፣ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎማ ቁጠባ

• ከመርካቶ በተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሜትሮሎጂ በር ላይ

• ከራስ ቴአትር በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ

• ከተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ ሼል

• ከፒያሳ በቸርችር ጎዳና ለገሃር ቴዎድሮስ አደባባይ

• በአሮጌው ቄራ ፍል ውሃ ንግድ ማተሚያ ቤት

• ከካዛቺስ ወደ ሂልተን ካዛንቺስ ቶታል

• ከአዋሬ በካዛንቺስ ወደ ፍል ውሃ የሚወስደው መንገድ የቀድሞ 6ኛ ፖሊስ መታጠፊያ ላይ ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

ህብረተሰቡ ይህን አውቆ አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም መልዕክት አስተላልፏል።

በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም ክልክል ነው ተብሏል።
188 views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 19:26:16 ሩሲያ ማዳበሪያ በነጻ ለአፍሪካ ልታቀርብ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ታዳጊ ለሆኑ የአፍሪካ ሀገራት በሺህ ቶኖች የሚቆጠር ማዳበሪያ በነጻ ልታቀርብ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

የሩሲያ የማዕድንና የፖታሽ ማዳበሪያዎች አምራች ዩራልቼም ፥ ምርቶቹን ለአፍሪካ በነጻ ለማቅረብ መወሰኑን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ዲሚትሪ ኮኒያዬቭ አስታውቀዋል፡፡

በዚህም የመጀመሪያውን 25 ሺህ ቶን ማዳበሪያ ወደ ቶጎ እንደሚላክም ነው የተገለጸው፡፡

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ፥ ሀገሪቱ ማዳበሪያ መስጠቷና ወደ ውጭ መላኳ በምግብ ዋስትናዋ ላይ አንዳች ችግር አይፈጥርም ሲሉ ነው የገለጹት፡፡

በዚህ ወር መጀመሪያ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሻንጋይ የትብብር ድርጅት የመሪዎች ስብሰባ ላይ፥ በምዕራቡ ዓለም በተጣለባት ማዕቀብ ሳቢያ በወደቦች የተጠራቀመ 300 ሺህ ቶን ማዳበሪያን ለታዳጊ ሀገራት በነፃ ታቀርባለች ማለታቸው ይታወሳል።

ፑቲን ሩሲያ የማዳበሪያ ምርቷን ወደ አውሮፓ ህብረት ለመላክ የሚያስችለውን ውሳኔ በደስታ ቢቀበሉም፥ የህብረቱ አባል ሀገራት ብቻ እንዲገዙ የቀረበውን ሀሳብ መተቸታቸውን የዘገበው አር ቲ ነው፡፡

በሐምሌ ወር መጨረሻ ሞስኮና ኪየቭ በኢስታንቡል በተመድ አደራዳሪነት ባደረጉት ውይይት በጥቁር ባህር በኩል ዩክሬን የእህል ምርቶቿን ለዓለም ገበያ እንድታቀርብ መስማማታቸው የሚታወስ ነው።

ስምምነቱ ሩሲያ የማዳበሪያና የምግብ ሸቀጦችን ለዓለም አቀፉ ገበያ እንድታቀርብ የሚፈቅድ ቢሆንም ሞስኮ ግን ይህ ተፈጻሚ አለመሆኑን ገልጻለች።
280 views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ