Get Mystery Box with random crypto!

ቻይና “ለአሜሪካ ከባድ ማስጠንቀቂያ ነው” ያለችውን ወታደራዊ ልምምድ በታይዋን አቅራቢያ አደረገች | EBC(Ethiopian Brodcasting Corboration(EBC)

ቻይና “ለአሜሪካ ከባድ ማስጠንቀቂያ ነው” ያለችውን ወታደራዊ ልምምድ በታይዋን አቅራቢያ አደረገች

የቻይና ጦር ቃል አቀባይ በትናትናው እለት እንዳስታወቀው ቻይና እራሷን በራስ የምታስተዳድር ደሴት ላይ ያላትን ቁርጠኝነት ለአሜሪካ ለማሳየት በቅርቡ በታይዋን አቅራቢያ ተከታታይ ወታደራዊ ልምምዶችን አድርጋለች።

የቻይና ጦር የምስራቃዊ እዝ በታይዋን ዙሪያ የውጊያ ዝግጁነት ልምምዶችን እና ሌሎች የስልጠናዎችን በባህር እና አየር ላይ ማካሄዱንም የወታደራዊ እዙ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሺ ዪ ተናግረዋል። ልምምዱ አሜሪካ ለታይዋን እውቅና ለመስጠት እያደረገችው ላለው እንቅሰቃሴ “ከባድ ማስጠንቀቂያ” መሆኑንም ቃል አቀባዩ ገልፀዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት በእስያ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኀገራቸው ታይዋንን ለመጠበቅ ኃይል ልትጠቀም እንደምትችል መናገራቸው ይታወሳል።