Get Mystery Box with random crypto!

ደሸት777.... (፯፯፯)

የቴሌግራም ቻናል አርማ desht777 — ደሸት777.... (፯፯፯)
የቴሌግራም ቻናል አርማ desht777 — ደሸት777.... (፯፯፯)
የሰርጥ አድራሻ: @desht777
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.55K
የሰርጥ መግለጫ

ደሸት777(፯፯፯) ድርጅታችን ቢመረመር ውጤቱ ታላቋን ኢትዮጵያን ለመገንባት እና ኃያል ሥልጡን ለማድረግ የተቋቋመ ብሎም ብዙ ሊቃውንቶችን በይፋ ጥበባቸውን የሚያስቀጥል ኃያል ድርጅት ነው።

https://www.facebook.com/ደሸት-፯፯፯-103696061536486/
ይሄ ደሞ የFacebook ፔጃችን ነው
በዚህ ቻናል ላይ ያላችሁን ሀሳብና አስተያየት በዚህ @Dessht777bot መላክ ትችላላችሁ

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-30 21:51:53
የተወርዋሪ ኮከብ(Comet) እና የትክክለኞቹ ኮከቦች(star)ልዩነት

ተወርዋሪ ኮከቦች በተለመዶ ወደ ምድር ሲመጡ የሚታዩ ነገሮች ሲሆን ካሁን አሁን ወደቁ ብለን ስናስብ ተመልሰው በቅፅበት ይጠፋሉ።


እንዚህ ተወርዋሪ ኮከቦች የሚገኙት በኛው ሶላር ሲስተም ውስጥ ሲሆን ትክክለኞቹ ከዋክብት ግን የሚገኙት ከኛ ሶላር ሲስተም ውጭ ነው።

ተወርዋሪ ኮከቦች ከክዋክብት አንፃር እጅግ ትንሽ ነገሮች ናቸው፤ ወይም የተሰባበሩ ድንጋዮች ናቸው።

እንዚህ ነገሮች ወደ ምድራች የሚወድቁ ሲሆን ምንም አይነት ጉዳት አያስከትሉም።

ተወርዋሪ ኮከቦች የሚመጡት ከማርስ አጠገብ ከሚገኘው ከድንጋዮች ጥርቅም ነው።
በዚህ ቦታ እጅግ ብዙ ድንጋዮች በመሰባሰብ ፀሐይን የሚዞሯት ሲሆን ድንገት ከእሽክርክሪታቸው እየወጡ ወደ ፕላኔቶች ይወድቃሉ።
ከፕላኔቶች አንዷም የኛዋ ምድር ስትሆን በየአመቱ እጅግ በብዙ ተወርዋሪ ኮከቦች ትመታለች ግን ምንም ጉዳት ሳያስከትሉ ታቃጥላቸዋለች!!!
349 views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 12:21:10

547 views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 23:01:57 የጠፍችው አትላንቲስ


ምድራችን እጂግ አስደናቂና ሚስጥራቸው ያልተፈታ እንዲሁም  ውስብስብ የሆኑ በርካታ ነገሮችን በውስጧ ይዛለች።

የእኒህን አስጀናቂ ነገሮችን ሚስጥር ለመረዳት አለም በመሰረታዊነት የጥንት መዛግብቶችን በመመርመርና በማጥናት የእንቆቅልሾችን  ሁሉ ጠቋሚ መንገድን ያገኛል።

ከእነዚህም በዋናነት የኢትዮጵያውያኑ የጥንት መዛግብት ተጠቃሽ ነው።

እኒህን የጥንት መዛግብትን በመ መርመርና በመፈተሽ የተገኘው የምርምር ስራ የ ጠፋችውን የአትላንቲስ ከተማ ጉዳይ ነው ።

አለም ላይ ዘመን ተሻጋሪ አነጋጋሪ ከሆኑት ዋና ነገሮች አንዱ ስለ ጠፋችው አትላንቲስ ከተማ ሁኔታ ነው።
የጠፋችው አትላንቲስ.... ማን ናት


የዚች ከተማ ታሪክ መነሻ ግኝት በ360 ከ ቅድመ ልደተ ክርስቶች በፊት ፕልቶ በተባለ ፈላሰፋ ነበር።
ይህ ፈላስፊ ዋቢ አድርጎ  ጀምስ የተባለ የኒውዮርክ ፕሮፈሰር ሲገልጽ።
ይህ ከተማ በ ሳራ በርሃ አካባቢ  አካባቢ ሲሆን በዛን ዘመን የሚገኙ የሰውና የአማልክት ገጸ ያላቸው ፍጡራን መኖርያ እንደነበር ይገልጻል። እኒህ የተለዩ የሆኑ ፍጡራንም የ Uthiopia የተባለ ስልጣኔ ያስፋፉ ሲሆኑ በባህር ሀይል የተካኑ ጠቢባን ገናና ፍጡራን እምደነበሩ ይገልጻል። የሚኖሩትም በደሴት መካከል ከሀይቅ ስር ነበር። በዚህም አካባቢ ከፍተኛ የወርቅና የብር ክምችት ሲለሚገኝ ገናና የመሆናቸውን መንገድም እንዳጸናላቸው ይገልጻሉ ታዲያ አትላንቲስ ማን ናት ?
ፍላስፍዎ ፕሌቴ  ከ ክርስቶስ ልደት 350  አመት ቀደም ብሎ ሲጽፍ የአትላንቲስ ግዛት የኢትዮጵያ ግዛት እንደለሆነች እና በአባይ ወንዝ ተፍስስ እንደምትገኝ ገልጿሌ።
ሌላው  ጃክሰን የተባለ የተሪክ ተመራማሪ ሰላማዊቷ ዩቲዮጵያ በማለት አትላንቲሰሰ የኢትዮጵያ ግዛት እንደነበረችና እነደተሰወረች በማስረጃ ይሞግታል።
ላላው ጀርመናዊኤውገን the adventure of human kind በሚል መጻህፉ ላይ ከአትላንቲስ መጥፍት በኋላ የጀመረው ስረው መንግስት አዲሱን የጥቁር ዘር በሚወክሉ ኢትዮጵያውያን መሆኑ እስከ ደቡብ አውሮፖ ኢሲያና መካከለኛው ምስራቅ ዘልቀው የገቡ ጥቁር ነገስታት በመሆን በግርክና ሮማ እስከ መመለክ ደርሰው ነበር በማለት የ አትላንቲስ ሴልጣኔ የጥቁር ኢትዮጵያውያን ስልጣኔ ነው ይላል።

   ይህንን እና በርካታ  ማስረጃወችን በማቅረብ ይሞግታሉ ..እኔ ደግሞ የኢትዮጵያ ማንነት  እንዴውም ከዚህ በላይ ነው እላለሁ..

ቶማስ ሙር   ዮትጵያ ያላት እንዲሁም ፕሌቶ አትላንቲስ ያላት የቃል-ኪዳን ምድር  ኢትዮጵያ ናት።

ፍራርሲክ ቤከን እኮ "ዘ ኒው አትላንቲክ" ያላት በኋላም ፕሮክለስ የተባለ 415-482 ዓ.ም የነበረ እንዲሁም የፕሌቶን አስተሳስብ የቀረፀ ሰው እንዲህ ይለናል "ፕሌቶ አትላንቲስ ፍፁማዊ አገር የሰላም አገር የፍቅር አገር :የበረከት አገር ያላት ፊክሽናል አለም ሳትሆን #የኢትዩጵያ_ግዛት ነው" ብሎ ያኔ ፅፋታል።>>
:
  በጥንት ልደተ ክርስቶስ የፐርሻዎ ንግስት እኮ ኢትዩጵያን ለመውጋት ዘምታ ጦሯን አስጨርሳ ተመለሰች ይላል ።ታላቁ እስክንድር 127 ሀገራትን ሲገዛ ኢትዩጵያን አልገዛም።ንግስት ማክዳ እኮ ጠቢቡ ሰለሞንን የጠየቀች ጠቢብ ነች።
: ኢትዮጵያ በግብፅ 18 የነገስታትን አንግሳለች። ሜምኖን የተባለዉ ኢትዮጵያዊ የግብፅ ንጉስ ከ1320 አ.አ እስከ ሴፕዩምስኬኩረስ 170 አ.ም የቆመ ሀዉልት እንደነበረዉና ሀዉልቱም ጠዋት ጠዋት ፀሀይ ሲያርፍበት የክራር ድምፅ ያሰማ እንደነበር ሄሮዱተስ በፓፒረስ ወረቀት ላይ አስፍሮት ይገኛል።
:
ከማንም አገር ያልተዳቀለ የራሳችን የሆነ ይህም ብቻ ሳይሆን ለዓለም ፊደላት መሰረት የሆነ ፊደል፣ አሀዝ፣ የቀን መቁጠርያ ለአለም የሠጠች።ከአለም መጀመሪያ እግዚያብሔርን ስታመልክ የኖረች እስከ አለም መጨረሻ የምትኖር እና የምታሳምን ኢትዮጵያ ናት ምክንያተም የቃል-ኪዳን ምድር ናት።
አሐሜኔስ የተባለ ኢትዮጵያዊ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕላኔቶች እንዳሉ የተናገረ ሰው ነው። ይህ አሐሜኔስ የተባለው ኢትዮጵያዊ 16 ፕላኔቶች እንዳሉ የተናገረ ሲሆን፤ ፀሀይን ለመዞር ስንት ግዜ እንደሚፈጅባቸው፤ በስንት ምህዋር እንደሚዞሩና በውስጣቸው ያሉትን ፍጥረታትን ጽፍል።NASA እንኳን አስካሁን እርገጠኛ የሆነው ዘጠኝ ፕላኔቶች እንዳሉ ነው ነገር ግን ገና 7 ፕላኔቶች ይቀራሉ።
:ከአራራት ተራራ ግርጌ ከግዮን መፍለቂያ ጀምረው ሜዴትራንያንን ተሻግረው እስከ የመን ድረስ ሰፊ ግዛት የነበራቸው የዛሬዎቹን የአትላንቲክና የሕንድ ውቅያኖሶችን ጨምሮ መላው አፍሪቃን በስማቸው የሰየሙ።ውቅያኖስን አቋርጠው በዛሬዎቹ አማሪካና አውሮፓ : ኢስያን ቀድመው የሰፈሩ።
:
በጥንት ስሟም ምሥር የተባለች የምትጠራዋን ግብጽን ኢትዮጵያኖች ለመጀመሪያ ጊዜ ምሥርን ስላበቀሉባት ምሥር እየተባለች እንጥትጠራ ያደረጉ። #ኢትዮጵያ ከሌሎች የዓለም ሀገራት በተለየ የምስጢራት እና የጥበባት መገኛ ነች ፡፡ ለዚህም ዋንኛው መንስኤ በምድራዊ ሰማያትና በሰማያተ ሰማያት በሚገኙት መላእክት ቅዱሳን አባቶች ብሎም የአዳም ልጆች መካከል ግንኙነት ከሚፈጠርባቸው በምድር ላይ ከሚገኙት ሰባቱ የክብር ቦታዎች መካከል አራቱን ይዛ መገኘቷ  ይህ እኔ ሌሎቹ ያልተነገር ታሪክ ያላት ናትና ወደ ፊት እንገልጣታለን!

ፈለገ ጥበባት
470 views20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 23:01:13
393 views20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 18:47:51

461 views15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 18:59:04 #ጎግ_ማጎግ ማናቸው?#ውጊያቸውስ_መቼና_ከማንጋ_ነው? ኢትዮጵያስ?

{ክፍል-፩}

(ቱካ ማቲዎስ)

የሥማቸው መጠሪያ?

አማርኛው:- ጎግ ማጎግ ፣ አረብኛው:- Ya'juj Ma'juj (እጁጅ እና ማእጁጅ)፣ እንግሊዝኛው:- Gog and Magog ይላቸዋል።

አንድም:- ጎግ- "ሠራዊት፤በዝቶ የሚሄድ፤የሚንጋጋ ማለት ነው:-ጎግ'ማጎግ የ"ብዙ ብዙ" ማለት ነው ይባላል።
አንድም:- ጎግ ግለሰብ ፣ማጎግ ደግሞ የሚመጣበት ሃገር ነውም የሚሉ አሉ።

ወይም ማጎግ ያስገኛቸው ጎጎች የሚለው ምናልባት ፅዑፉን ጠልቀን እያነበብን ስንመጣ ስለ ስያሜያቸው የምንረዳው ይሆናል።

የሆኖው ሆኖ ሥያሜያቸው ለጦርነት፣ለጥፋትና ለአመፃ ስለሚተባበሩ በዓላማና በተግባር በአንድነት የፀኑ ሕዝቦች እንደሆኑ ስማቸው ራሱ ይናገራል።

ከየት መጡ?

በኃለኛው ዘመን ስለሚነሱና ጥምረት ፈጥረው ውጊያ አድርገው ምድርን እንዳልነበረች ስለሚያደርጓት ጎግ ማጎግ ለእዝቅኤል ማንነታቸው ተነግሮታል:-

ት. ሕዝ 38÷2 - "...ፊትኽን፡#በጎግ፡ላይና፡#በማጎግ፡ምድር፡ላይ፥#በሞሳሕና፡#በቶቤል፡ዋነኛ፡አለቃ፡ላይ፡
አቅናበት፥ትንቢትም፡ተናገርበት..."

እዚኽ ላይ ማጎግ የተባሉትና ከሱምጋ ወግነው ለውጊያ ሚሰለፉት የኖህ ልጅ #ያፌት የወለዳቸው ልጆች ናቸው።
ዘፍ.10÷2 "የያፌት ልጆች ጋሜር፥ #ማጎግ፥ማዴ፥ያዋን፥ይልሳ፥ #ቶቤል፥ #ሞሳሕ፥ቴራስ፡ናቸው።" ብሎ በግልፅ አስቀምጦልናል።"

አለቃ ሆኖ ጦርነቱን የሚመራው ዋናው ጎግ እንደሆነ ደግሞ እንዲኽ ይለናል ት.ሕዝ 38÷3 "የሞሳሕና፡የቶቤል፡#ዋነኛ_አለቃ_ጎግ፡ሆይ..."

የጎግ የማይቀር አለቅነትና ወደርሱም ስለሚሰበሰቡ ወገኖች ት.ሕዝ 38÷3 ይኽን ይላል። " አንተና፡ወዳንተ፡የተሰበሰቡ፡ወገኖችኽ፡ዅሉ፡ተዘጋጁ፥አንተም፡ራስኽን፡አዘጋጅተኽ፡አለቃ፡ኹናቸው።"

ከቅዱስ መጽሐፍ በተጨማሪ በታላቁ እስክንድር ጀብዱ "ዜና እስክንድር" ላይ #የእስክንድር_በር ተብሎ የሚታወቀውና በራሱ በታላቁ እስክንድር የተገነባ፣ ክፉ ጨካኝና የሰውን ሥጋ የሚበሉ የተባሉ ጎሳዎችን ወደ ሰው ልጅ መኖሪያ እንዳይቀርቡና ÷ የሰውን ዘር እንዳያጠፉ "ምድቅኤል"ና "ቅርፍትኤል" የሚባሉትን ሁለት ተራሮች እስክንድር መቄዶናዊ በፀሎት አቃርቦ አጋጥሞባቸው እንዳይወጡ የመላዕእክት ጠባቂ (ወደበሩ ሲቀርቡ የበገና ድምፅ የሚያሰማ ሮቦት፣መካኒካል ጥበብ) አቁሞባቸዋው ወደ በሩ አይጠጉም። እነዚሕም ከያፌት ማጎግ ከተባለው የዘር ግንድ የወጡና መናፍስታዊ ፍጥረታት እንደሆኑ ያስረዳል።

የታሸገባቸው ተራራም ሥፍራውም በቱርክ ሃገር በአርመኒያና አዘርባጃን አካባቢ በቱርክና ሩስያ ድንበር ካውካስ ተራራ እንደሚገኝ የሚናገሩ አሉ።

Vikings , Huns , Khazars, Mongols , Turanians እና ሌሎች ዘላን ዝርያዎች ዘሮች ናቸው የሚሉ አሉ።

የእስክንድር በርና ጎግ ማጎግ የሚገናኙባት ብዙ ታሪክ ተፅፏል። በኛም ግእዝ "ዜና እስክንድር" በሚል የተጠቀሰ አለ።

ስለነዚኽ ፍጡራን ቅዱስ ቁርዓንም Surah Kahaf
የተባለው ምዕራፍ Yajuj and Majuj ( ﻳَﺄْﺟُﻮﺝُ ﻭَﻣَﺄْﺟُﻮﺝُ ) ጎግ ማጎግን ኃላ ቀርና ግብረ ገብነት የጎደላቸው ዘሮች በማለትና በ Zu'l-Qarnayn (በባለ ሁለት ቀንዱ) የፅድቅና ትክክለኛ ነገር በሚሰራው ገዢ ) በብረት መዝጊያ እንደተነጠሉና እንደታገዱ ይገልፃል።

{{ ስለ ታላቁ እስክንድር መቄዶናዊ በርና በውስጡ ስለታገዱት አስገራሚ ፍጡራን ሌላ ቀን በሠፊው እንመለሥበታለን።}}

ቁጥራቸው ብዛታቸውስ?

ዮሐ.ራዕ 20÷8 "በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ..."

ይኽ ማለት #ከሰሜን_ከደቡብ_ከምሥራቅና_ምዕራብ የምድራችን ክፍል፣ ጎግ አለቃ ሆኗቸው ለጦርነት እንደሚያሰልፋቸውና፣

"ቍጥራቸውም፡እንደ፡ባሕር፡አሸዋ፡የሚያኽል፡ነው።" ይለናል።#ይቀጥላል
634 views15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 19:14:06

609 views16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 10:29:14
#ባለጌ ሕፃን!

ቴዎድሮስ መዝገቡ

ባለጌ ሕፃን አጥፍቶ ሲቆጡት የበለጠ ጥፋቱን ይቀጥላል። ዕቃ ይሰብራል። እናቱን በጭቃ ይቀባል።
ብልግና የምግባር መለኪያ፥ የባህሪው መገለጫ ነዉና ምግባሩ ጥፋት ነው። ብቃቱ አዉዳሚነት ነው።

በቅርብ አመታት በኢትዮጵያ ምድር ላይ ወደ ስልጣን የመጣው መሪ ዶክተር ዓብይ አሕመድ ከባለጌ ሕፃን የወረደ ማንነትን ይዞ የሕዝብ መሪ የሆነ የመጀመሪያው ሰው ነው።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላይ የተነሳውን የሕዝብ ብሶት ከማስተካከል ይልቅ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ አዉጆ በአጣዬ ላይ ተጨማሪ ሰቆቃ እና ለአገራችን ሳንካ የሆነ ተግባር በድጋሜ ማካሔዱን መርጧል።

ይህ ስነ ምግባር የመሪነት መግለጫ ሳይሆን የቁሞቀር ፖለቲከኞች ባህሪ፣ ማገናዘብ የተሳናቸው ሰዎች ህልም ነው።
952 views07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 19:21:49 Watch "በፊት ዝንጀሮ ያሉኝ ሰዎች ዛሬ ሰገዱልኝ!!!" on YouTube


764 views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 21:37:40 #ደሸት ወደ ፊት....777

የሚረዳን ይከተለናል፤ የማይረዳን እና ጠማማ የሆነው ግን አብሮን መራመድም ሆነ መሻገር አይችልም።

ይህ አዲስ ታሪክ አይደለም፤ ነገ ደሸት እና ነገደ ተርሴስ ለጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ስጦታን እንቁዮጵን ሲቀርቡ፤ በተቃራኒው ደግሞ ንጉሥ ሄሮርስ እእልፍ አዕላፍ ሕፃናትን በመግደል ለተንኮል የተሰለፉት ለቁጥር የሚታክቱት ናቸው።

ተሻጋሪ ለመሆን እውነትን እና ፍትሕን መመርመር እና ስለ እውነት ስንል እራሳችንን አሳልፈን ስንሰጥ ነው።

እኛን የሚከተል ትውልድ ከዚህ በታች ባለው እሳቤ አዕምሮው (mind) በላቀ እሰቤ ማሰብ ሲችል።

ነገን በመልካም #እሳቤ ስሎ ለቀጣዩ ትውልድ እና ለታሪክ አሻራ መጣል የሚፈልግ እና ማድረግ የሚችለው ሁሉ ከእኛ ጋር ይጣመራል፤ ሲፈጥንም ይቀድመናል።

እኛ ደሸቶች #በ፯ ኃይል እናምናለን፤ በዓለም ላይ ፀያፍ ተግባር እንዲጠፋ፥ የ666 ተንኮል እንዲወድም፥ ዘረፋ፥ ሙስና፥ ዝሙት፥ ታሪክ አውዳሚነትን በፅኑ ይቃወማል።

ይህን አፀያፊ ተግባር #ለመደምሰስም ወጣቱን ትውልድ እያስተባበረ እና ያልነቃውን ትውልድ እና ታላቅ አገር፥ ስልጡን ወጣት፥ የተማረ የሰው ኃይል፥ ሥነ ምግባር ያለው ትውልድ እንገነባለን።

መነሻችንም ሆነ መዳረሻችን እውነትን እና ጥበብን ብሎም ታሪካዊ አሻራን ማሳረፍ እና ማስቀጠል ነው።

@desht777
@desht777

ደሸት ወደ ፊት..፯፯፯
906 viewsedited  18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ