Get Mystery Box with random crypto!

የጠፍችው አትላንቲስ ምድራችን እጂግ አስደናቂና ሚስጥራቸው ያልተፈታ እንዲሁም  ውስብስብ የሆኑ | ደሸት777.... (፯፯፯)

የጠፍችው አትላንቲስ


ምድራችን እጂግ አስደናቂና ሚስጥራቸው ያልተፈታ እንዲሁም  ውስብስብ የሆኑ በርካታ ነገሮችን በውስጧ ይዛለች።

የእኒህን አስጀናቂ ነገሮችን ሚስጥር ለመረዳት አለም በመሰረታዊነት የጥንት መዛግብቶችን በመመርመርና በማጥናት የእንቆቅልሾችን  ሁሉ ጠቋሚ መንገድን ያገኛል።

ከእነዚህም በዋናነት የኢትዮጵያውያኑ የጥንት መዛግብት ተጠቃሽ ነው።

እኒህን የጥንት መዛግብትን በመ መርመርና በመፈተሽ የተገኘው የምርምር ስራ የ ጠፋችውን የአትላንቲስ ከተማ ጉዳይ ነው ።

አለም ላይ ዘመን ተሻጋሪ አነጋጋሪ ከሆኑት ዋና ነገሮች አንዱ ስለ ጠፋችው አትላንቲስ ከተማ ሁኔታ ነው።
የጠፋችው አትላንቲስ.... ማን ናት


የዚች ከተማ ታሪክ መነሻ ግኝት በ360 ከ ቅድመ ልደተ ክርስቶች በፊት ፕልቶ በተባለ ፈላሰፋ ነበር።
ይህ ፈላስፊ ዋቢ አድርጎ  ጀምስ የተባለ የኒውዮርክ ፕሮፈሰር ሲገልጽ።
ይህ ከተማ በ ሳራ በርሃ አካባቢ  አካባቢ ሲሆን በዛን ዘመን የሚገኙ የሰውና የአማልክት ገጸ ያላቸው ፍጡራን መኖርያ እንደነበር ይገልጻል። እኒህ የተለዩ የሆኑ ፍጡራንም የ Uthiopia የተባለ ስልጣኔ ያስፋፉ ሲሆኑ በባህር ሀይል የተካኑ ጠቢባን ገናና ፍጡራን እምደነበሩ ይገልጻል። የሚኖሩትም በደሴት መካከል ከሀይቅ ስር ነበር። በዚህም አካባቢ ከፍተኛ የወርቅና የብር ክምችት ሲለሚገኝ ገናና የመሆናቸውን መንገድም እንዳጸናላቸው ይገልጻሉ ታዲያ አትላንቲስ ማን ናት ?
ፍላስፍዎ ፕሌቴ  ከ ክርስቶስ ልደት 350  አመት ቀደም ብሎ ሲጽፍ የአትላንቲስ ግዛት የኢትዮጵያ ግዛት እንደለሆነች እና በአባይ ወንዝ ተፍስስ እንደምትገኝ ገልጿሌ።
ሌላው  ጃክሰን የተባለ የተሪክ ተመራማሪ ሰላማዊቷ ዩቲዮጵያ በማለት አትላንቲሰሰ የኢትዮጵያ ግዛት እንደነበረችና እነደተሰወረች በማስረጃ ይሞግታል።
ላላው ጀርመናዊኤውገን the adventure of human kind በሚል መጻህፉ ላይ ከአትላንቲስ መጥፍት በኋላ የጀመረው ስረው መንግስት አዲሱን የጥቁር ዘር በሚወክሉ ኢትዮጵያውያን መሆኑ እስከ ደቡብ አውሮፖ ኢሲያና መካከለኛው ምስራቅ ዘልቀው የገቡ ጥቁር ነገስታት በመሆን በግርክና ሮማ እስከ መመለክ ደርሰው ነበር በማለት የ አትላንቲስ ሴልጣኔ የጥቁር ኢትዮጵያውያን ስልጣኔ ነው ይላል።

   ይህንን እና በርካታ  ማስረጃወችን በማቅረብ ይሞግታሉ ..እኔ ደግሞ የኢትዮጵያ ማንነት  እንዴውም ከዚህ በላይ ነው እላለሁ..

ቶማስ ሙር   ዮትጵያ ያላት እንዲሁም ፕሌቶ አትላንቲስ ያላት የቃል-ኪዳን ምድር  ኢትዮጵያ ናት።

ፍራርሲክ ቤከን እኮ "ዘ ኒው አትላንቲክ" ያላት በኋላም ፕሮክለስ የተባለ 415-482 ዓ.ም የነበረ እንዲሁም የፕሌቶን አስተሳስብ የቀረፀ ሰው እንዲህ ይለናል "ፕሌቶ አትላንቲስ ፍፁማዊ አገር የሰላም አገር የፍቅር አገር :የበረከት አገር ያላት ፊክሽናል አለም ሳትሆን #የኢትዩጵያ_ግዛት ነው" ብሎ ያኔ ፅፋታል።>>
:
  በጥንት ልደተ ክርስቶስ የፐርሻዎ ንግስት እኮ ኢትዩጵያን ለመውጋት ዘምታ ጦሯን አስጨርሳ ተመለሰች ይላል ።ታላቁ እስክንድር 127 ሀገራትን ሲገዛ ኢትዩጵያን አልገዛም።ንግስት ማክዳ እኮ ጠቢቡ ሰለሞንን የጠየቀች ጠቢብ ነች።
: ኢትዮጵያ በግብፅ 18 የነገስታትን አንግሳለች። ሜምኖን የተባለዉ ኢትዮጵያዊ የግብፅ ንጉስ ከ1320 አ.አ እስከ ሴፕዩምስኬኩረስ 170 አ.ም የቆመ ሀዉልት እንደነበረዉና ሀዉልቱም ጠዋት ጠዋት ፀሀይ ሲያርፍበት የክራር ድምፅ ያሰማ እንደነበር ሄሮዱተስ በፓፒረስ ወረቀት ላይ አስፍሮት ይገኛል።
:
ከማንም አገር ያልተዳቀለ የራሳችን የሆነ ይህም ብቻ ሳይሆን ለዓለም ፊደላት መሰረት የሆነ ፊደል፣ አሀዝ፣ የቀን መቁጠርያ ለአለም የሠጠች።ከአለም መጀመሪያ እግዚያብሔርን ስታመልክ የኖረች እስከ አለም መጨረሻ የምትኖር እና የምታሳምን ኢትዮጵያ ናት ምክንያተም የቃል-ኪዳን ምድር ናት።
አሐሜኔስ የተባለ ኢትዮጵያዊ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕላኔቶች እንዳሉ የተናገረ ሰው ነው። ይህ አሐሜኔስ የተባለው ኢትዮጵያዊ 16 ፕላኔቶች እንዳሉ የተናገረ ሲሆን፤ ፀሀይን ለመዞር ስንት ግዜ እንደሚፈጅባቸው፤ በስንት ምህዋር እንደሚዞሩና በውስጣቸው ያሉትን ፍጥረታትን ጽፍል።NASA እንኳን አስካሁን እርገጠኛ የሆነው ዘጠኝ ፕላኔቶች እንዳሉ ነው ነገር ግን ገና 7 ፕላኔቶች ይቀራሉ።
:ከአራራት ተራራ ግርጌ ከግዮን መፍለቂያ ጀምረው ሜዴትራንያንን ተሻግረው እስከ የመን ድረስ ሰፊ ግዛት የነበራቸው የዛሬዎቹን የአትላንቲክና የሕንድ ውቅያኖሶችን ጨምሮ መላው አፍሪቃን በስማቸው የሰየሙ።ውቅያኖስን አቋርጠው በዛሬዎቹ አማሪካና አውሮፓ : ኢስያን ቀድመው የሰፈሩ።
:
በጥንት ስሟም ምሥር የተባለች የምትጠራዋን ግብጽን ኢትዮጵያኖች ለመጀመሪያ ጊዜ ምሥርን ስላበቀሉባት ምሥር እየተባለች እንጥትጠራ ያደረጉ። #ኢትዮጵያ ከሌሎች የዓለም ሀገራት በተለየ የምስጢራት እና የጥበባት መገኛ ነች ፡፡ ለዚህም ዋንኛው መንስኤ በምድራዊ ሰማያትና በሰማያተ ሰማያት በሚገኙት መላእክት ቅዱሳን አባቶች ብሎም የአዳም ልጆች መካከል ግንኙነት ከሚፈጠርባቸው በምድር ላይ ከሚገኙት ሰባቱ የክብር ቦታዎች መካከል አራቱን ይዛ መገኘቷ  ይህ እኔ ሌሎቹ ያልተነገር ታሪክ ያላት ናትና ወደ ፊት እንገልጣታለን!

ፈለገ ጥበባት