Get Mystery Box with random crypto!

#ባለጌ ሕፃን! ቴዎድሮስ መዝገቡ ባለጌ ሕፃን አጥፍቶ ሲቆጡት የበለጠ ጥፋቱን ይቀጥላል። ዕቃ | ደሸት777.... (፯፯፯)

#ባለጌ ሕፃን!

ቴዎድሮስ መዝገቡ

ባለጌ ሕፃን አጥፍቶ ሲቆጡት የበለጠ ጥፋቱን ይቀጥላል። ዕቃ ይሰብራል። እናቱን በጭቃ ይቀባል።
ብልግና የምግባር መለኪያ፥ የባህሪው መገለጫ ነዉና ምግባሩ ጥፋት ነው። ብቃቱ አዉዳሚነት ነው።

በቅርብ አመታት በኢትዮጵያ ምድር ላይ ወደ ስልጣን የመጣው መሪ ዶክተር ዓብይ አሕመድ ከባለጌ ሕፃን የወረደ ማንነትን ይዞ የሕዝብ መሪ የሆነ የመጀመሪያው ሰው ነው።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላይ የተነሳውን የሕዝብ ብሶት ከማስተካከል ይልቅ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ አዉጆ በአጣዬ ላይ ተጨማሪ ሰቆቃ እና ለአገራችን ሳንካ የሆነ ተግባር በድጋሜ ማካሔዱን መርጧል።

ይህ ስነ ምግባር የመሪነት መግለጫ ሳይሆን የቁሞቀር ፖለቲከኞች ባህሪ፣ ማገናዘብ የተሳናቸው ሰዎች ህልም ነው።