Get Mystery Box with random crypto!

#ጎግ_ማጎግ ማናቸው?#ውጊያቸውስ_መቼና_ከማንጋ_ነው? ኢትዮጵያስ? {ክፍል-፩} (ቱካ ማቲዎስ) | ደሸት777.... (፯፯፯)

#ጎግ_ማጎግ ማናቸው?#ውጊያቸውስ_መቼና_ከማንጋ_ነው? ኢትዮጵያስ?

{ክፍል-፩}

(ቱካ ማቲዎስ)

የሥማቸው መጠሪያ?

አማርኛው:- ጎግ ማጎግ ፣ አረብኛው:- Ya'juj Ma'juj (እጁጅ እና ማእጁጅ)፣ እንግሊዝኛው:- Gog and Magog ይላቸዋል።

አንድም:- ጎግ- "ሠራዊት፤በዝቶ የሚሄድ፤የሚንጋጋ ማለት ነው:-ጎግ'ማጎግ የ"ብዙ ብዙ" ማለት ነው ይባላል።
አንድም:- ጎግ ግለሰብ ፣ማጎግ ደግሞ የሚመጣበት ሃገር ነውም የሚሉ አሉ።

ወይም ማጎግ ያስገኛቸው ጎጎች የሚለው ምናልባት ፅዑፉን ጠልቀን እያነበብን ስንመጣ ስለ ስያሜያቸው የምንረዳው ይሆናል።

የሆኖው ሆኖ ሥያሜያቸው ለጦርነት፣ለጥፋትና ለአመፃ ስለሚተባበሩ በዓላማና በተግባር በአንድነት የፀኑ ሕዝቦች እንደሆኑ ስማቸው ራሱ ይናገራል።

ከየት መጡ?

በኃለኛው ዘመን ስለሚነሱና ጥምረት ፈጥረው ውጊያ አድርገው ምድርን እንዳልነበረች ስለሚያደርጓት ጎግ ማጎግ ለእዝቅኤል ማንነታቸው ተነግሮታል:-

ት. ሕዝ 38÷2 - "...ፊትኽን፡#በጎግ፡ላይና፡#በማጎግ፡ምድር፡ላይ፥#በሞሳሕና፡#በቶቤል፡ዋነኛ፡አለቃ፡ላይ፡
አቅናበት፥ትንቢትም፡ተናገርበት..."

እዚኽ ላይ ማጎግ የተባሉትና ከሱምጋ ወግነው ለውጊያ ሚሰለፉት የኖህ ልጅ #ያፌት የወለዳቸው ልጆች ናቸው።
ዘፍ.10÷2 "የያፌት ልጆች ጋሜር፥ #ማጎግ፥ማዴ፥ያዋን፥ይልሳ፥ #ቶቤል፥ #ሞሳሕ፥ቴራስ፡ናቸው።" ብሎ በግልፅ አስቀምጦልናል።"

አለቃ ሆኖ ጦርነቱን የሚመራው ዋናው ጎግ እንደሆነ ደግሞ እንዲኽ ይለናል ት.ሕዝ 38÷3 "የሞሳሕና፡የቶቤል፡#ዋነኛ_አለቃ_ጎግ፡ሆይ..."

የጎግ የማይቀር አለቅነትና ወደርሱም ስለሚሰበሰቡ ወገኖች ት.ሕዝ 38÷3 ይኽን ይላል። " አንተና፡ወዳንተ፡የተሰበሰቡ፡ወገኖችኽ፡ዅሉ፡ተዘጋጁ፥አንተም፡ራስኽን፡አዘጋጅተኽ፡አለቃ፡ኹናቸው።"

ከቅዱስ መጽሐፍ በተጨማሪ በታላቁ እስክንድር ጀብዱ "ዜና እስክንድር" ላይ #የእስክንድር_በር ተብሎ የሚታወቀውና በራሱ በታላቁ እስክንድር የተገነባ፣ ክፉ ጨካኝና የሰውን ሥጋ የሚበሉ የተባሉ ጎሳዎችን ወደ ሰው ልጅ መኖሪያ እንዳይቀርቡና ÷ የሰውን ዘር እንዳያጠፉ "ምድቅኤል"ና "ቅርፍትኤል" የሚባሉትን ሁለት ተራሮች እስክንድር መቄዶናዊ በፀሎት አቃርቦ አጋጥሞባቸው እንዳይወጡ የመላዕእክት ጠባቂ (ወደበሩ ሲቀርቡ የበገና ድምፅ የሚያሰማ ሮቦት፣መካኒካል ጥበብ) አቁሞባቸዋው ወደ በሩ አይጠጉም። እነዚሕም ከያፌት ማጎግ ከተባለው የዘር ግንድ የወጡና መናፍስታዊ ፍጥረታት እንደሆኑ ያስረዳል።

የታሸገባቸው ተራራም ሥፍራውም በቱርክ ሃገር በአርመኒያና አዘርባጃን አካባቢ በቱርክና ሩስያ ድንበር ካውካስ ተራራ እንደሚገኝ የሚናገሩ አሉ።

Vikings , Huns , Khazars, Mongols , Turanians እና ሌሎች ዘላን ዝርያዎች ዘሮች ናቸው የሚሉ አሉ።

የእስክንድር በርና ጎግ ማጎግ የሚገናኙባት ብዙ ታሪክ ተፅፏል። በኛም ግእዝ "ዜና እስክንድር" በሚል የተጠቀሰ አለ።

ስለነዚኽ ፍጡራን ቅዱስ ቁርዓንም Surah Kahaf
የተባለው ምዕራፍ Yajuj and Majuj ( ﻳَﺄْﺟُﻮﺝُ ﻭَﻣَﺄْﺟُﻮﺝُ ) ጎግ ማጎግን ኃላ ቀርና ግብረ ገብነት የጎደላቸው ዘሮች በማለትና በ Zu'l-Qarnayn (በባለ ሁለት ቀንዱ) የፅድቅና ትክክለኛ ነገር በሚሰራው ገዢ ) በብረት መዝጊያ እንደተነጠሉና እንደታገዱ ይገልፃል።

{{ ስለ ታላቁ እስክንድር መቄዶናዊ በርና በውስጡ ስለታገዱት አስገራሚ ፍጡራን ሌላ ቀን በሠፊው እንመለሥበታለን።}}

ቁጥራቸው ብዛታቸውስ?

ዮሐ.ራዕ 20÷8 "በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ..."

ይኽ ማለት #ከሰሜን_ከደቡብ_ከምሥራቅና_ምዕራብ የምድራችን ክፍል፣ ጎግ አለቃ ሆኗቸው ለጦርነት እንደሚያሰልፋቸውና፣

"ቍጥራቸውም፡እንደ፡ባሕር፡አሸዋ፡የሚያኽል፡ነው።" ይለናል።#ይቀጥላል