Get Mystery Box with random crypto!

የተወርዋሪ ኮከብ(Comet) እና የትክክለኞቹ ኮከቦች(star)ልዩነት ተወርዋሪ ኮከቦች በተለመዶ | ደሸት777.... (፯፯፯)

የተወርዋሪ ኮከብ(Comet) እና የትክክለኞቹ ኮከቦች(star)ልዩነት

ተወርዋሪ ኮከቦች በተለመዶ ወደ ምድር ሲመጡ የሚታዩ ነገሮች ሲሆን ካሁን አሁን ወደቁ ብለን ስናስብ ተመልሰው በቅፅበት ይጠፋሉ።


እንዚህ ተወርዋሪ ኮከቦች የሚገኙት በኛው ሶላር ሲስተም ውስጥ ሲሆን ትክክለኞቹ ከዋክብት ግን የሚገኙት ከኛ ሶላር ሲስተም ውጭ ነው።

ተወርዋሪ ኮከቦች ከክዋክብት አንፃር እጅግ ትንሽ ነገሮች ናቸው፤ ወይም የተሰባበሩ ድንጋዮች ናቸው።

እንዚህ ነገሮች ወደ ምድራች የሚወድቁ ሲሆን ምንም አይነት ጉዳት አያስከትሉም።

ተወርዋሪ ኮከቦች የሚመጡት ከማርስ አጠገብ ከሚገኘው ከድንጋዮች ጥርቅም ነው።
በዚህ ቦታ እጅግ ብዙ ድንጋዮች በመሰባሰብ ፀሐይን የሚዞሯት ሲሆን ድንገት ከእሽክርክሪታቸው እየወጡ ወደ ፕላኔቶች ይወድቃሉ።
ከፕላኔቶች አንዷም የኛዋ ምድር ስትሆን በየአመቱ እጅግ በብዙ ተወርዋሪ ኮከቦች ትመታለች ግን ምንም ጉዳት ሳያስከትሉ ታቃጥላቸዋለች!!!