Get Mystery Box with random crypto!

DaniApps™

የቴሌግራም ቻናል አርማ dani_apps — DaniApps™ D
የቴሌግራም ቻናል አርማ dani_apps — DaniApps™
የሰርጥ አድራሻ: @dani_apps
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.81K
የሰርጥ መግለጫ

✅The Best Android Apps And Games Are Here.📱
✅For Any Questions ➡️ @DaniappsBot Or Group ➡️ @dani_apps_group.
✅ Apps Or Games ➡️ @daniappsstore
✅Ask Any Apps ➡️ @Daniapps2bot
✅ Website https://daniapps.epizy.com/

https://g.page/r/CYhVwdbaF335EA0/review

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 11:00:17 Telegram sticker ለመስራት የሚያስፈልገን

1-
@Stickers bot
2- ፎቶ መጠን መቀየሪያ app->photo risizer
3- የፎቶ ኋላ ማጥፊያ app -> bg eraser

( እላይ የተጠቀሱትን አፕሊኬሽኖች ከፁሁፉ ስር ያገኙታል)

እንጀምር
መጀመሪያ የተጠቀሱትን አፕሊኬሽኖች ስልካችን ላይ እንጭናለን በመቀጠል የምንፈልገውን ፎቶ እንመርጣለን ከዛ ከጫንናቸው apps ውስጥ background Eraser የሚለውን App በመክፍት ከስር "load a photo" የሚለውን በመጫን የመረጥነውን ፎቶ እናስገባለን ከዛ እላይ በኩል Done የሚለውን መጫን በመቀጠል ፎቶው ላይ ማጥፋት የምንፈልገውን ቦታ ማስተካከያዎችን በመጠቀም በመንፈለገው መጠን ካጠፋን በኋላ Done የሚለውን በመጫን ቀጥለን save ማድረግ ከዚህ በኋላ Photo Resizer app በመክፈት select photo የሚለውን በመጫን save ያደረግነውን ፎቶ መርጠን ማስገባት በመቀጠል እላይ Resi... ከሚለው ፅሁፍ ጎን ያለችውን photo resize ማድረጊያ ምልክት መጫን ከዛ select dimensions ከሚለው ስር width × height ከሚለው ፅሁፍ ስር custom የሚለውን በመጫን 512 × 512 ማድረግ
( ስቲከር ለማዘጋጀት የግድ አንዱ ጉን 512px መሆን አለበት ሌላኛው ጎን ግን 512 እና ከዛ በታች መጠቀም እንችላለን

ከ 512px ከበለጠ ስቲከር መስራት አንችልም ) ከዛ Ok የሚለውን መጫን ከዚህ በኋላ ፎቷችን በቀጥት ስልካችን ውስጥ በ png ፎርማት Save ይሆናል( ስቲከር ለመስራት ኢሜጃችን png ፎርማት መሆን አለበት) አሁን ሁሉንም በመዝጋት telegram አፕሊኬሽናችንን በመክፈት search ማድረጊያው ላይ Stickers ብለን ሰርች በማድረግ ከሚመጣው Stikers bot ላይ በመግባት

/start
የሚለውን ፅሁፍ እንጫናለን ከዛ
"Hello, I'm the Sticker Bot!…" የሚል መልስ ሲመጣልን ከዝርዝረየ ውስጥ /newpack
የሚለውን መንካት ወይም ፅፈን መላክ ከዛ
"Yay! A new stickers pack... "የሚል መልስ ሲመጣልን ለስቲከር ፓካችን የምንፈልገውን ስም በምንፈልገው ቋንቋ በመፃፍ መላክ ከዛ ስሙ ተቀባይነት ካገኘ "Alright! Now send me the sticker.…" ብሎ ስቲከር ለማድረግ የፈለግነውን ፎቱ እንድንልክ ይጠይቀናል አሁን መጀመሪያ ላይ ያዘጋጀነውን ፎቶ በፋይል መልክ እንልካለን

( ቀጥታ ጋለሪ በመግባት ወይም በፎቶ መልክ ብንልክ ተቀባይነት አይኖረውም )
መጀመሪያ -->file -->internal Storage -->picture --->PhotoResizer የሚለው folder ውስጥ በመግባት ያዘጋጀነውን ፎቶ በመምረጥ መላክ ቀጥሎ "Thanks! Now send me an emoji" በማለት ለስቲከሩ የሚሆን emoji( አሻንጉሊት) እንድንክለት ይጠይቀናል እኛ የምንፈለገውን emoji(አሻንጉሊት) መላክ ከዛም "Congratulations. Stickers in the pack: 1. To add another sticker…

...When you're done, simply send the /publish
command." የሚል ስቲከራችን ተቀባይነት እንዳገኘ የሚናገር መልስ ይመጣልናል እኛም /publish የሚለውን በምንካት ወይም በመፃፍ መላክ ከዚህ ኋላ ለ ስቲከራችን የሚሆን link እንዲያዘጋጅልን
"Please provide a short name for your stickerpack.…" የሚል ጥያቄ የያዘ መልስ ሲላክልን የፈለግነውን ለሊንክ የሚሆ ስም ፅፈን መላክ ስሙ ተቀባይነት ካገኘ
"Kaboom! I've just published your sticker pack.…"በመላት ከሥር የ ስቲከራችንን ሊንክ አያይዞ ይልክልናል
ተቀባይነት ከሌለው ሌላ ስም በማስገባት እንደገና መላክ አለብን

ከዚህ በኋላ ስቲከራችን ሌላ ሰው እንዲጠቀምብት ከፈለግን ሊንካችንን ሸር ማድረግ ነው
አንዴ ስቲከር pack ከከፈትን በኋላ ሌላ እስቲክር ለመጨመር ስንፈልግ ቀጥታ በቀላሉ ያዘጋጀነውን ፎቶ ልክ እንደመጀመሪያው በፋይል መልክ በመላክ ስቴፖችን መከተል ነው።

EthioCyber
DaniApps
114 views𝗗𝗮𝗻𝗶 𝗔𝗽𝗽𝘀 , 08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 11:00:18 ስማርት ስልኮቻችን ሀይል እንዴት መሙላት አለብን…?

በርካታ ተግባራትን የሚያከናውኑበት ስማርት ስልክዎ ባትሪ በፍጥነት እያለቀ ተችገረዋል?

የተለያዩ ስልቶችን ተጠቅመው የስልክዎን ባትሪ ቢያንስ ሙሉ ቀን እንዲያስጠቅምዎትስ ጥረት አድርገዋል?

በቴክኖሎጂው መስክ የተሰማሩ ባለሙያዎች የስልካችን ባትሪ በፍጥነት እያለቀ የምንቸገረው በሶስት ምክንያቶች መሆኑን ይገልፃሉ።

የመጀመሪያው በስማርት ስልኮቻችን የጫንናቸው መተግበሪያዎች መብዛት እና እያወቅንም ይሁን ሳናውቅ ተከፍተው ባትሪ መብላታቸው
ነው።
የስማርት ስልካችን ላይ ሙጭጭ ብለን አልላቀቅ ማለትም ሌላኛው የባትሪ እድሜን የሚያሳጥር ልማድ ነው።

ሶስተኛው እና ዋነኛው የባትሪ ህይወትን የሚያሳጥረው ተብሎ በባለሙያዎች የተጠቀሰው ደግሞ የሀይል አሞላላችን (ቻርጅ አደራረጋችን መሆኑ ተገልጿል።

ብዙዎቻችን የስማርት ስልካችን ባትሪ ሙሉ በሙሉ ሲያልቅ ቻርጅ ማድረግ እንዳለብን እናምናለን።

በአንዳንዶቻችን ዘንድ ደግሞ ቻርጅ እንደሰካን ሞባይላችንን መጠቀም የባትሪውን አገልግሎት ያራዝማል የሚል አመለካከት አለ።

ይሁን እንጂ የሞባይል ባትሪ እንደ ሰው ልጅ ሁሉ “መጨናነቅን” አይወድም ነው የሚለው ባትሪ ዩኒቨርሲቲ የተሰኘ ኩባንያ።

ስልካችንን ቻርጅ እያደረግን መጠቀም የባትሪውን እድሜ ያሳጥራልም ይላል።

ስለ ስማርት ስልክዎ ባትሪ ከመጨነቅ የሚገላግሉ ናቸው ያላቸውን ነጥቦችም ባትሪ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች አስቀምጧል።

የስልክዎ ባትሪ ሙሉ ቻርጅ ከተደረገ በኋላ ሞባይሉን ከቻርጀሩ ይንቀሉት፡

ኩባንያው እንደሚለው የስማርት ስልካችን ባትሪ ከአቅሙ በላይ ቻርጅ ሲደረግ የረጅም ጊዜ አገልግሎቱ እየወረደ ይመጣል።

ስልካችን 100 ፐርሰንት ቻርጅ ከሆነ በኋላ እንደተሰካ መተው ለከፍተኛ መጨናነቅ በመዳረግ የባትሪውን ሀይል የመያዝ አቅም ይቀንሰዋል።

(እስከ 100 ፐርሰንት ቻርግ ማድረግም ለመጀመሪያ ጊዜ ካልሆነ አስፈላጊ አይደለም፡

ከአድካሚ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በኋላ ጡንቻዎችን ማፍታታት እንደሚገባ ሁሉ ስልካችንም ሙሉ በሙሉ በሀይል ከተሞላ በኋላ ከቻርጀሩ መንቀል ይገባል።

ባትሪውን ከሙቀት ይጠብቁት
የስማርት ስልክ ባትሪዎች በቀላሉ በሙቀት ይግላሉ።

ለዚህም ነው አፕል ራሱ የአይፎን ስልኮችን ቻርጅ ስታደርጉ መሸፈኛ (ኬዞቹን ብታወጡት በማለት የሚመክረው።

ስለሆነም ስልካችን ቻርጅ ስናደርግ መሞቁን ካስተዋልን ሽፋኑን ማውጣት ይኖርብናል።

የባትሪያችን ጤና ለመጠበቅ ስማርት ስልካችን ቻርጅ የምናደርግበት አካባቢ የፀሀይ ሙቀት የሌለበት ቢሆንም ጥሩ ነው።

100 ፐርሰንት ላይ እስከሚደርስ መጠበቅ የለብንም፡

እንደ ባትሪ ዩኒቨርሲቲ ገለፃ ከሆነ ከፍተኛ ቮልቴጅ ባትሪውን ስለሚያጨናንቀው ባትሪን መቶ በመቶ ሀይል መሙላት አያስፈልግም።

ስማርት ስልካችን ቀኑን ሙሉ ቻርጅ ማድረግም በባትሪው እድሜ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ብሏል።

ቻርጅ ለማድረግ የባትሪውን ማለቅ አይጠብቁ።

ስልካችን ቻርጅ ለማድረግ ባትሪው ተሟጦ እስኪያልቅ መጠበቅ የለብንም።

ባገኘነው አጋጣሚ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን ሀይል ይዞ የመቆየት አቅም ያሳድገዋል።

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ስልቶች የስማርት ስልካችን ባትሪ ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግል እና ቀኑን ሙሉ ከስጋት ነፃ እንድንሆን ይረዳናል ።


EthioCyber
DaniApps
170 views𝗗𝗮𝗻𝗶 𝗔𝗽𝗽𝘀 , 08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:01:43
የአልትራሳውንድ መሣሪያን ለመተካት ያለመው ፈጠራ

የማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች በታማሚዎች ሰውነት ላይ በቀላሉ የሚለጠፍ እና የሰውነትን የውስጥ አካላት ምስል በጥራት ማሳየት የሚችል መሣሪያ ማበልፀጋቸው ተነገረ፡፡

ፈጠራው በጤና ተቋማት የሚገኘውን የአልትራሳውንድ መመርመሪያ መሣሪያ የፖስታ ቴምብር በሚያክል ተለጣፊ ቁስ በመተካት የታማሚዎችን ልብ፣ ሳምባ እና ሌሎች ውስጣዊ አካላትን አሁናዊ ምስል በተሻለ ጥራት ለመመልከት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

በኢንስቲትዩቱ ድረ-ገጽ በወጣው መረጃ መሠረት ይህ ቆዳ ላይ የሚለጠፍ ቁስ የአልትራሳውንድ መሣሪያዎች ስራቸውን በሚከውኑበት መንገድ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ለአርባ ስምንት ሰዓት ያለማቋረጥ ምስሎችን ማቅረብ እንደሚችል ተመላክቷል፡፡

መሣሪያው በበጎ ፈቃደኞች ላይ በተደረገ ሙከራ የግለሰቦቹን ዋና ዋና የደም ቧንቧዎች፣ ልብ፣ ሳንባ እና ሌሎች ውስጣዊ የሰውነት አካላትን አሁናዊ ምስል ጥራት ባለው መልኩ ማቅረብ መቻሉ ተገልጿል፡፡

አሁን ላይ ባለው የተመራማሪዎቹ ንድፍ ከመሣሪያው የተንፀባረቁ የድምፅ ሞገዶችን ለመተርጎም ከሌላ መሣሪያ ጋር ማገናኘት ያስፈልጋል፡፡ ሆኖም ፈጠራውን ገመድ አልባ በማድረግ ለማንኛውም ሰው ተደራሽ ይደረጋል ተብሏል፡፡


EthioCyber
DaniApps
125 views𝗗𝗮𝗻𝗶 𝗔𝗽𝗽𝘀 , 08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 17:52:06

170 views𝗗𝗮𝗻𝗶 𝗔𝗽𝗽𝘀 , 14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 17:52:06 Check It Out
152 views𝗗𝗮𝗻𝗶 𝗔𝗽𝗽𝘀 , 14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:00:52 ማህበራዊ ሚዲያ

1. ከጎልማሶችና በዕድሜ ከገፉ ሰዎች አንጻር ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ የሚጋሩ ሀሠተኛ መረጃዎችን በመለየት ረገድ ከፍ ያለ በራስ መተማመን ማሳየታቸውን በትናትናው ዕለት ይፋ የሆነ የዳሰሳ ጥናት ጠቁሟል። በሚዲያ አጠቃቀም ንቃት ላይ የሚሰራው ሚዲያ ዋይዝ (MediaWise) እና በዳታ ዙሪያ የሚሰራው ዩጎቭ (YouGov) ከጎግል ጋር በመተባበር የሰሩት የዳሰሳ ጥናት በናይጄሪያ፣ በህንድ፣ በዩናይትድ ስቴትስ፣ በጃፓን፣ በጀርመን፣ በብራዚልና በዩናይትድ ኪንግደም ነዋሪ የሆኑ 8,500 ሰዎችን ያካተተ ነበር። የጥናቱ ውጤት ከ26 ዓመት በታች የሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ሀሠተኛ መረጃን በመለየት ረገድ የተሻለ በራስ መተማመን ያሳዩ ሲሆን ይልቁንም ወላጆቻቸውና በዕድሜ የገፉ ሰዎች ለሀሠተኛ መረጃ ይጋለጣሉ ብለው እንደሚጨነቁ አሳይቷል። ወጣቶቹ ሀሠተኛ መረጃን ለመለየት የመረጃ ምንጩና በመረጃው በተካተቱ ሃቆች ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ እንዲሁም እንደ ሪቨርስ ኢሜጅ ሰርች ያሉ መገልገያዎችን በተሻለ ሁኔታ እንደሚጠቀሙ ጥናቱ አስነብቧል።

2. ዋትስአፕ የተላኩ መልዕክቶች ስክሪ ቅጅ (screenshot) እንዳይደረጉ የሚያደርግ አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀምር አስታውቋል። አገልግሎቱ ዋትስአፕ ከአመት በፊት ከመጀመሩ የአንድ ጊዜ እይታ (View Once) ጋር የሚጣመር ሲሆን ይህም የተላኩ መልዕክቶችን በስክሪን ቅጅ ማስቀረትን ይከለክላል።

3. ሜታ በፕላትፎርሞቹ የሚጋሩ ይዘቶች ከፖሊሲዎቹ ጋር የማይጣረሱ መሆናቸውን የሚከታተሉ ሰራተኞቹን ቁጥር 40,000 እንዲሁም ለስራው የሚያወጣው ወጭ 5 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ዛሬ ይፋ አድርጓል። በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚያደርገውን ክትትልም ማሳደጉን በዚህም ከሚያስወግዳቸው ፌክ አካውንቶች 99.7%ቱ ካለሰው ንክኪ በቴክኖሎጅ መሆኑን ገልጿል። ሜታ ይህን ያስታወቀው በመጭው ጥቅምት ወር በብራዚል በሚደረገው ምርጫ የሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን እንዲሁም የጥላቻ ንግግሮችን ለመቆጣጣር እያደረገ ያለውን ዝግጅት ባስነበበት መጣጥፍ ነው።

4. ቴሌግራም በፕላትፎርሙ የሚደረጉ የመልዕክት ልውውጦችን የበለጠ ያዘምናቸዋል ያላቸውን አፕዴቶች (updates) ወደ ስራ ለማስገባት አፕስቶር (Appstore) እንቅፋት እንደሆነበት አስታውቋል። የቴሌግራም መስራች የሆነው ፓቬል ዱሮቭ በግል ቻናሉ ባስነበበው ጽሁፍ አፕዴቶቹ ለአፕስቶር ከሁለት ሳምንት በፊት ቢላኩም ምላሽ እንደተነፈጉ ገልጿል።

EthioCyber
DaniApps
198 views𝗗𝗮𝗻𝗶 𝗔𝗽𝗽𝘀 , 08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 11:01:14
Monitoring

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET343 የተከሰተው ምንድን ነበር?

በያዝነው ሳምንት መጀመርያ ሰኞ እለት በበረራ ቁጥር ET343 ከካርቱም ወደ አዲስ አበባ ሲበር የነበረ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ማረፊያው አዲስ አበባ ደርሶ እያለ ከበረራ ተቆጣጣሪዎች ጋር ግንኙነቱ ተቋርጦ እንደነበር በአለም አቀፍ የአቪዬሽን ሚድያዎች ሲዘገብ ነበር።

እንደ "Aviation Herald" ያሉ ሚድያዎች አውሮፕላኑ ግንኙነት ካለማድረጉ በተጨማሪም ለማረፍ ከፍታውን ሳይለቅ አዲስ አበባ መድረሱን የዘገቡ ሲሆን ጉዳዩን ከኢትዮጵያ የበረራ ቋት ማዕከል ማረጋገጣቸውን ፅፈዋል።

በዚህ ዙርያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ መግለጫ ያወጣ ሲሆን በተባለው ጉዳይ ዙርያ ሪፖርት እንደደረሰው እና የበረራው ፓይለቶች ኋላ ላይ ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር ግንኙነት ፈጥረው አውሮፕላኑ በሰላም እንዳረፈ አስታውቋል።

አክሎም በረራውን ሲያከናውኑ የነበሩ ፓይለቶች ከስራ ታግደው ምርመራ እየተካሄደ እንደሆነ አስታውቋል። በምርመራው ውጤት መሰረትም አስፈላጊው የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድ ጨምሮ አስታውቋል።

EthioCyber
DaniApps
239 views𝗗𝗮𝗻𝗶 𝗔𝗽𝗽𝘀 , 08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 12:41:21

241 views𝗗𝗮𝗻𝗶 𝗔𝗽𝗽𝘀 , 09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 11:00:24 ከYoutube ቪድዮ እና ኦድዮ ማውረጃ

እንዴት ከዩቱብ ቪዲዮ(video)እና ኦድዮ(audio) ያለ ሶፍትዌር እናወርዳለን( download ) እናደርጋለን ቀላል ዘዴ ተከታተሉኝ መልካም ቆይታ።

1.ከስልክ ውይም ከኮምፕውተር ብሮውሰር( browser) ላይ y2mate ብላችሁ ጽፋችሁ search ታደርጋላችሁ
2.download video and audio from youtube የሚልና ከስር በቀይ ሳጥን search or paste link here የሚል ይመጣል
3.እዛ ቦታ ላይ የቪድዮውን ሊንኩን paste ታደርጋላችሁ
4.ከዛ በተላያየ መጠን(size) አማራጭ ይመጣል ከጎን download የሚለውን እንጫናለን
5.ከዛ ዳውንሎድ (downlod) የሚል ያመጣል ከዛ ቀጥታ ይወርዳል
6. ኦድዮውንም ቪድዮ ከሚለው ጎን mp3 የሚልለውን ተጭናችሁ ልክ እንደዛው mp3 ይሚለውን ስንጫን ይመጣል።
ሊንኩን በቀጥታ ከፈለጉ ከስር ያለውን ይጠቀሙ
https://www.y2mate.com/en19

EthioCyber
DaniApps
319 views𝗗𝗮𝗻𝗶 𝗔𝗽𝗽𝘀 , 08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 11:01:14 List Of Highly Compressed PC Games

Drive Links

1. Terrorist Takedown
Size:- 144MB (
https://goo.gl/FzEvL5 )

2. Ridge Racer Unbounded
Size:- 1.6GB (
https://goo.gl/kSYLsc )

3. IGI 4 The Mark
Size:- 294MB (
https://goo.gl/6ms7Gz )

4. Sky Force Reloaded
Size:- 237MB (
https://goo.gl/FhbcLg )

5. Hitman 2 Silent Assassin
Size:- 481MB (
https://goo.gl/FTxnyt )

6. Terrorist Takedown 2 US Navy Seals
Password :
www.pcgamefreetop.net
SIze:- 454MB ( https://goo.gl/GPw93A )

7. Terrorist Takedown Covert Operations
Password=
www.fullypcgames.net
Size:- 432MB ( https://goo.gl/bxcsTM )

8. IGI 3 The Plan
Size:- 105MB (
https://goo.gl/vFfG1u )

9. Stronghold Crusader
Password:-
www.fullypcgames.net
Size:- 148MB ( https://goo.gl/27rZU2 )

10. Medal of Honor Allied Assault Spearhead
Size :- 636 MB (
https://goo.gl/adAwkr )

11. Max Payne 2 Highly Compressed
Size:- 1 GB (
https://goo.gl/62qfcy)

12. Prototype 2
Password of ZIp file is:-
games.torrentsnack.com
Size:- 3 GB ( https://goo.gl/PcWqxB )

13. Counter Strike Global Offensive ( CS GO )
Size:- 2.9 GB + 503 MB Patch Included
Direct Link:- (
https://goo.gl/v7YinS )

14. Commandos Strike Force
Size:- 1.9GB (
https://goo.gl/dXDkNn )

15. Constantine
Size:- 300 MB (
https://goo.gl/PKEDg1 )



SUBSCRIBE US ON YOUTUBE

YouTube
https://www.youtube.com/channel/UCksMp0FnUAPLNkTdsBHzG9g

Linkedin Profile
https://www.linkedin.com/in/daniapps/
EthioCyber
DaniApps
310 views𝗗𝗮𝗻𝗶 𝗔𝗽𝗽𝘀 , 08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ