Get Mystery Box with random crypto!

Monitoring በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET343 የተከሰተው ምንድን ነበር? | DaniApps™

Monitoring

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET343 የተከሰተው ምንድን ነበር?

በያዝነው ሳምንት መጀመርያ ሰኞ እለት በበረራ ቁጥር ET343 ከካርቱም ወደ አዲስ አበባ ሲበር የነበረ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ማረፊያው አዲስ አበባ ደርሶ እያለ ከበረራ ተቆጣጣሪዎች ጋር ግንኙነቱ ተቋርጦ እንደነበር በአለም አቀፍ የአቪዬሽን ሚድያዎች ሲዘገብ ነበር።

እንደ "Aviation Herald" ያሉ ሚድያዎች አውሮፕላኑ ግንኙነት ካለማድረጉ በተጨማሪም ለማረፍ ከፍታውን ሳይለቅ አዲስ አበባ መድረሱን የዘገቡ ሲሆን ጉዳዩን ከኢትዮጵያ የበረራ ቋት ማዕከል ማረጋገጣቸውን ፅፈዋል።

በዚህ ዙርያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ መግለጫ ያወጣ ሲሆን በተባለው ጉዳይ ዙርያ ሪፖርት እንደደረሰው እና የበረራው ፓይለቶች ኋላ ላይ ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር ግንኙነት ፈጥረው አውሮፕላኑ በሰላም እንዳረፈ አስታውቋል።

አክሎም በረራውን ሲያከናውኑ የነበሩ ፓይለቶች ከስራ ታግደው ምርመራ እየተካሄደ እንደሆነ አስታውቋል። በምርመራው ውጤት መሰረትም አስፈላጊው የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድ ጨምሮ አስታውቋል።

EthioCyber
DaniApps