Get Mystery Box with random crypto!

ማህበራዊ ሚዲያ 1. ከጎልማሶችና በዕድሜ ከገፉ ሰዎች አንጻር ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ የሚጋሩ ሀ | DaniApps™

ማህበራዊ ሚዲያ

1. ከጎልማሶችና በዕድሜ ከገፉ ሰዎች አንጻር ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ የሚጋሩ ሀሠተኛ መረጃዎችን በመለየት ረገድ ከፍ ያለ በራስ መተማመን ማሳየታቸውን በትናትናው ዕለት ይፋ የሆነ የዳሰሳ ጥናት ጠቁሟል። በሚዲያ አጠቃቀም ንቃት ላይ የሚሰራው ሚዲያ ዋይዝ (MediaWise) እና በዳታ ዙሪያ የሚሰራው ዩጎቭ (YouGov) ከጎግል ጋር በመተባበር የሰሩት የዳሰሳ ጥናት በናይጄሪያ፣ በህንድ፣ በዩናይትድ ስቴትስ፣ በጃፓን፣ በጀርመን፣ በብራዚልና በዩናይትድ ኪንግደም ነዋሪ የሆኑ 8,500 ሰዎችን ያካተተ ነበር። የጥናቱ ውጤት ከ26 ዓመት በታች የሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ሀሠተኛ መረጃን በመለየት ረገድ የተሻለ በራስ መተማመን ያሳዩ ሲሆን ይልቁንም ወላጆቻቸውና በዕድሜ የገፉ ሰዎች ለሀሠተኛ መረጃ ይጋለጣሉ ብለው እንደሚጨነቁ አሳይቷል። ወጣቶቹ ሀሠተኛ መረጃን ለመለየት የመረጃ ምንጩና በመረጃው በተካተቱ ሃቆች ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ እንዲሁም እንደ ሪቨርስ ኢሜጅ ሰርች ያሉ መገልገያዎችን በተሻለ ሁኔታ እንደሚጠቀሙ ጥናቱ አስነብቧል።

2. ዋትስአፕ የተላኩ መልዕክቶች ስክሪ ቅጅ (screenshot) እንዳይደረጉ የሚያደርግ አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀምር አስታውቋል። አገልግሎቱ ዋትስአፕ ከአመት በፊት ከመጀመሩ የአንድ ጊዜ እይታ (View Once) ጋር የሚጣመር ሲሆን ይህም የተላኩ መልዕክቶችን በስክሪን ቅጅ ማስቀረትን ይከለክላል።

3. ሜታ በፕላትፎርሞቹ የሚጋሩ ይዘቶች ከፖሊሲዎቹ ጋር የማይጣረሱ መሆናቸውን የሚከታተሉ ሰራተኞቹን ቁጥር 40,000 እንዲሁም ለስራው የሚያወጣው ወጭ 5 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ዛሬ ይፋ አድርጓል። በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚያደርገውን ክትትልም ማሳደጉን በዚህም ከሚያስወግዳቸው ፌክ አካውንቶች 99.7%ቱ ካለሰው ንክኪ በቴክኖሎጅ መሆኑን ገልጿል። ሜታ ይህን ያስታወቀው በመጭው ጥቅምት ወር በብራዚል በሚደረገው ምርጫ የሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን እንዲሁም የጥላቻ ንግግሮችን ለመቆጣጣር እያደረገ ያለውን ዝግጅት ባስነበበት መጣጥፍ ነው።

4. ቴሌግራም በፕላትፎርሙ የሚደረጉ የመልዕክት ልውውጦችን የበለጠ ያዘምናቸዋል ያላቸውን አፕዴቶች (updates) ወደ ስራ ለማስገባት አፕስቶር (Appstore) እንቅፋት እንደሆነበት አስታውቋል። የቴሌግራም መስራች የሆነው ፓቬል ዱሮቭ በግል ቻናሉ ባስነበበው ጽሁፍ አፕዴቶቹ ለአፕስቶር ከሁለት ሳምንት በፊት ቢላኩም ምላሽ እንደተነፈጉ ገልጿል።

EthioCyber
DaniApps