Get Mystery Box with random crypto!

DaniApps™

የቴሌግራም ቻናል አርማ dani_apps — DaniApps™ D
የቴሌግራም ቻናል አርማ dani_apps — DaniApps™
የሰርጥ አድራሻ: @dani_apps
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.81K
የሰርጥ መግለጫ

✅The Best Android Apps And Games Are Here.📱
✅For Any Questions ➡️ @DaniappsBot Or Group ➡️ @dani_apps_group.
✅ Apps Or Games ➡️ @daniappsstore
✅Ask Any Apps ➡️ @Daniapps2bot
✅ Website https://daniapps.epizy.com/

https://g.page/r/CYhVwdbaF335EA0/review

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-10 11:01:38
ኢትዮ ቴሌኮም የፓስፖርት አገልግሎት ክፍያዎችን በቴሌ ብር መፈፀም እንደሚቻል ይፋ አደረገ፡፡


ከበርካታ የመንግስት እና የግል ተቋማት ጋር ስምምነት እየፈፀመ የሚገኘው ኢትዮ ቴሌኮም አሁንም ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ጋር ስምምነቱን ፈፅሟል።

ስምምነቱም አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት፣ እድሳት ለመፈፀም እና ሲጠፋ ሌላ ለማውጣት አገልግሎት ሲፈልጉ በቴሌ ብር ክፍያ መፈፀም እንደሚችሉ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህወት ታምሩ አስታውቀዋል።

ወደ ተግባር ከገባ አንድ አመት ያስቆጠረው ቴሌ ብር 20 ሚሊዮን ደምበኞች እየተገለገሉበት መሆኑንም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ጠቁመዋል።
20 ቢሊዮን ብር የገንዘብ ዝውውርም ተደርጎበታል ነው ያሉት።

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሙሉጌታ በበኩላቸው አገልግሎቱ በቀን ከ1500 እስከ 2000 የሚጠጉ ደምበኞች የሚስተናገዱበት መሆኑን ጠቅሰዉ አገልግሎቱን ለማግኘት የሚፈጠረውን መጨናነቅ ይቀንሰዋል የሚል እምነት እንዳላቸዉ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም
DaniApps
558 views𝗗𝗮𝗻𝗶 𝗔𝗽𝗽𝘀 , 08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 11:51:45
አስማተኛው ማንቆርቆሪያ

የጥንት ቻይና ንጉሶች ወይም ባለስልጣኖች ተቀናቃኝ ወይም መንግስቱን የሚወርስ ሲኖር እራሳቸውን ለመከላከል የሚጠቀሙበት መሳሪያ ነው።
እንደምታዩት አንድ ማንቆርቆሪያ ቢሆንም ከውስጡ 3 የተለያዩ መጠጦችን መቅዳት ይቻላል።
በመጀመሪያም መገደል የሚፈለገው ሰው ቤተ መንግስት ግብዣ ነው በሚል ይጠራ እና ምግብ ከበላ በኋላ ሻይ ነው በሚል መርዙ ይቀዳል ማለት ነው ፤ ሰውየውም እንዳይጠራጠር ጋባዡ መርዝ አይደለም ብሎ ለራሱም ሻይ ይቀዳል
ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ይህ እየተለመደ በመምጣቱ ባለስልጣኑ ሁሉ ግብዣ ተጠርቶ ሲሄድ የራሱን ማንቆርቆሪያ ይዞ መሄድ ጀምሮ ነበር

JOSIE_Technology
DaniApps
510 views𝗗𝗮𝗻𝗶 𝗔𝗽𝗽𝘀 , 08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 21:08:53
የአገልግሎት እክል ማሳወቂያ
Incident notice

EthioTelecom
DaniApps
485 views𝗗𝗮𝗻𝗶 𝗔𝗽𝗽𝘀 , edited  18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 11:01:54 ስለ 5ጂ ሰምተው ተደንቀው ይሆናል፤ የ6ጂ መንገድ መጀመሩን ቢያውቁስ?

የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ኤሌክትሪካል መሐንዲሶች እስከ 100 ጊጋኸርዝ ባለው የራዲዮን ፍሪኩዌንሲ መስራት የምትችል ገመድ አልባ ትራንሲቨር ሰርተዋል፡፡ ይህም በአሁኑ ሰዓት
በግንባታ ላይ ካለው የአምስተኛው ትውልድ ገመድ አልባ ግንኙነት (5ጂ) መስራት ከሚችለው
አራት እጥፍ የላቀ ነው፡፡ በፈጣሪዎቿ “end-to-end transmitter-receiver” የሚል ስያሜ የተሰጣት ይህች ባለ 4.4 ካሬ ሚ.ሜ ቺፕ ለተላበሰችው የተለየ የዲጂታል-አናሎግ አወቃቀር ምስጋና ይግባውና ዲጂታል ሲግናሎችን ፈጣንና ኃይል ቆጣቢ በሆነ መልኩ ማንቀሳቀስ ትችላለች፡፡

በዩኒቨርሲቲው የኤሌክትሪካል ምህንድስና እና ኮምፒውተር ሳይንስ ፕሮፌሰር የሆኑት ፓያም
ሄይዳሪ አዲሱ ፈጠራቸው የሚያቀርበው የፍጥነት እና ዳታ መጠን ከአዳዳሶቹ የገመድ አልባ
ግንኙነት ደረጃዎች እንኳን ሲነፃፀር በሁለት orders of magnitude የላቀ መሆኑን በመጥቀስ መሳሪያውን 5ጂን የተሸገረ ብለውታል፡፡ ይህ እውነት አለው፡፡ 5ጂ መስራት የሚችለው ከ28 እስከ 38 ጊጋ ኸርዝ ባለው ገደብ ውስጥ ነው፡፡ በሌላ መልኩ 6ጂ ከ100 ጊጋ ኸርዝ በላይ እንደሚሰራ ይጠበቃል፡፡
ይህች አነስተኛ ቺፕ ዳታን በከፍተኛ ፍጥነት ማዘዋወር መቻሏ የነገሮች ከበይነ-መረብ ጋራ
ያላቸው ትስስር (Internet Of Things) እየላቀ በመጣበት በዚህ ወቅት እጅጉን አስፈላጊ
ያደርጋታል፡፡ ከዚህም ባሻገር መረጃን በማዘዋወር ረገድ ያላት ፍጥነት ከገመድ ጋር ተወዳዳሪ
ስለሆነ እንደ ዳታ ሴንተር ባሉ ስፍራዎች ላይ የሚታየውን ከፍተኛ የገመድ ዝርጋታ እና እርሱን
ተከትሎት የሚመጣውን ከፍተኛ ወጪንም እንደምትቀንስ ይጠበቃል፡፡

EthioCyber
DaniApps
638 views𝗗𝗮𝗻𝗶 𝗔𝗽𝗽𝘀 , 08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 08:15:24 ጎግል ፕሌይ ስቶር ብልሽት ለማስተካከል
...........................................................
Google Play Store በአብዛኛዎቹ የAndroid ዘመናዊ ስልኮች ላይ ተጭኖ የሚመጣ ሲሆን በሆነ ምክንያት በዲቫይሱ(ስልክ ወይም ታብሌት) ላይ መሥራት ሊያቆም ሊያጋጥም ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት በዲቫይሱ ላይ የተጫኑ ሶፍትዌሮችን የቅርብ ግዜ ማድረግ፣ ሶፍትዌሮችን ዳውንሎድ አድርገን መጫን እና አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን የቅርብ ግዜ ማድረግ አንችልም፡፡

Google Play መደብር በእርስዎ ዲቫይስ ላይ የማይሰራ ከሆነ ችግሩን ለመፍታት አንዳንድ መንገዶችን እጠቁማለሁ

1. የዲቫይሱን ቀን እና ሰዓት ቅንብር(ሴቲንግ) ያስተካክሉ
የተሳሳተ ቀን እና የጊዜ ገደብ ሲኖርዎት የGoogle አገልጋዮች ከአሳሽዎ ጋር ማመሳሰል ችግሮች ያጋጥማቸዋል ለማሰተካከል ወደ ሲስተም ሴቲንግ በመሄድ «ቀን እና ሰዓት» ማስተካከል ይጠበቅብዎታል፡፡
“Automatic date & time” and “Automatic time zone” እንዲሰራ ክፍት ያድርጉ ወይም ማኑዋሊ ቀን እና ሰዓት ያስተካክሉ፡፡
2. ጎግል ፕሌይ ስቶር ከዚህ በፊት ይዞት የነበረውን ዳታ ማጽዳት
በጎግል ፕሌይ ስቶር ላይ ከዚህ በፊት ተጠቅመናቸው የነበረው ሶፍትዌሮች ዝርዝ ይዞ ይቀመጣል(Cached data) ይሄ በምንፈልገው ጊዜ በፍጥነት ለመክፈት ኢንተርኔት ግንኙነቱ ፍጥነት ባይኖረውም ይረዳናል ነገር ግን Cached data አንዳንድ ጊዜ በPlay Store ላይ ችግር ይፈጥራል፡፡ በGoogle Play ላይ Cached data ለማጽዳት እነዚህን ደረጃዎች ይከተሉ:
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: ስቶሬጂ በመክፈት “CLEAR CACHE“.
3. የቅርብ ግዜ የሆነ ጎግል ፕሌይ ስቶር መጫን
በየጊዜው ሶፍትዌሮችን የሚሰሩ ዴቨሎፐሮች ለሰሩት ሶፍትዌር የቅርብ ግዜ ማድረጊያ አብዴተር የሚለቁ ሲሆን በዚህ የቅር ማድረጊያ ላይ የተለያዩ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል ይካተታል፡፡.
በተመሳሳይ መልኩ Google የ Play ስቶር አብዴተር በየጊዜው የሚያወጣ ሲሆን እንደሚኖሩበት አገር የሚለቀቀው አብዴት ሊዘገይ ይችላል በቀጥታ የቅርብ ማድረጊያውን(APK ፋይል) ማግኘት ከቸኮሉ APKMirror በማለት ኢንተርኔት መጠቀሚያ ብሮውዘር ላይ ፈልገው ማውረድ ይችላሉ፡፡
4. ጎግል ፕሌይ ስቶር ወደነበረበት የመጀመሪያው ቨርዥን መመለስ
አንዳንዴ የቅርብ ጊዜየተደረገ የጎግል ፕሌይ ስቶር ስሪት በርካታ ችግሮችን ሊያመጣ ይችላል ስለሆንም አብዴት የተደረገው በማጥፋት ዲቫይሱን ስንገዛ የነበረውን(factory version ) ጊዜ መመለስ፡፡ እነዚህን ደረጃዎች በመከተል እናጥፋ:
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: "Uninstall Updates"
5. ጎግል ፕሌይ ሰርቪስ መስራቱን ማረጋገጥ
Google Play Services ዋናው ተግባራት የGoogle አገልግሎቶች የሆኑትን Google Play ስቶር፣ ጎግል ማፕ፣ ጎግል ፕላስ ወዘተ አገልግሎቶች አውቶማቲካሊ ግንኙነት እንዲያደርጉ እና አብዴት የሚያደርግ የሚረዳ በመሆኑ እንደ ተጨማሪ መፍትሄ በመውሰድ Google Play Services መስራቱን ያረጋግጡ፡፡
6. ጎግል ፕሌይ ስቶርን ዘግቶ መክፈት
ይህ በአብዛኛው ተጠቃሚዎች የሚተገበሩበት የተለመደ ዘዴ ነው፡፡ ማድረግ ያለብዎት ነገር Google Play Storeን በመዝጋት እንደገና ማስጀመር( ለሌሎች አፕ ይሰራል) ችግሩን ሊፈታው ይችላል
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: “Force Stop” የሚለውን በመጠቀም መዝጋት እና እንደገና ይክፈቱ
7. ዲቫይሱን አጥፍቶ ማብራት
ዲቫይሱን አጥፍቶ ማብራት ተመራጭ መፍትሄ ሲሆን ብዙውን ግዜ ይሰራል ምክንያቱም ስማርትፎን ስልኮች አጥፍተን ዳግም ማስጀመር በዲቫይሱ ላይ ያሉትን አፕ ያረጋጋል፡፡ በተቻለ መጠን አንድ አፕ ከወትሮው የተለየ ተግባር ካመጣ ዳግም አጥፍተን ስናስጀምር የተሻለ አፈጻጸም እና ችግሩን መፍታት ይችላል፡፡
8. ዲቫይሱን አንድሮድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ዳግም ማስጀመር
ከላይ በጠቀስኩት መፍትሄ ምንም የማይሰራ ከሆነ ዲቫይሱን ፋብሪካ ዳግም ማስጀመር (hard reset) ማድረግ በዚህ ሂደት በዲቫይሱ ላይ ያሉትን ዳታ፣ የተጫኑ አፕሊኬሽን ሶፍትዌር እንደዚሁም የተጠቃሚውን አካውንት የመሳሰሉትን ሁሉ ያጠፋል፡፡

በርካታ ችግሮች በዲቫይሱ ላይ ካልገጠመዎት በስተቀር የፋብሪካ ዳግም ማስጀመር (hard reset) ባትጠቀሙ እመርጣለሁ ዳግም ለማስጀመር ከወሰኑ ሚሞሪው ያውጡ መጠባበቂያ መውሰድዎን አይርሱ፡፡

Ethiocyber
DaniApps
572 views𝗗𝗮𝗻𝗶 𝗔𝗽𝗽𝘀 , 05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ