Get Mystery Box with random crypto!

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵

የቴሌግራም ቻናል አርማ daily_news_ethiopian — Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵 D
የቴሌግራም ቻናል አርማ daily_news_ethiopian — Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵
የሰርጥ አድራሻ: @daily_news_ethiopian
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.94K
የሰርጥ መግለጫ

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵
🇪🇹ኢትዮጵያ
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ ቤተሰብ ይሁኑ
Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵
@Daily_News_Ethiopian
አስተያየትና መልክት ካሎት @Natty19
ምርትና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
@Natty19

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 00:25:40
ወደ ወልድያ ከተማ ለማቅናት ያሰበው የትሕነግ ወራሪ ቡድን እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ እግሩ ከሼህ ሁሴን ጅብሪል የትንቢት ሜዳ መሐልና ጠርዝ አልዘለለም።

ቡድኑ የተመኘውን የባሩድ ጸበል ከምድር በሚፈልቅ ብቻ ሳይሆን ከሰማይም በሚዘንብ እየተቸረው ይገኛል።

የትግራይ ወራሪ ሃይል ወልዲያ ከተማን ተቆጣጥሯልም እየተባለ በተለያዩ ሚዲያዎች የሚነዛው ወሬ ሀሰት ነው ሲሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ዶክተር ዳዊት መለሰ አስታውቀዋል።

ወልዲያ ከተማ በጥላት ቁጥጥር ስር አለመውደቋን እና ሰላም መሆኗን ለሁሉም ማህበረሰብ መግለፅ እወዳለሁ ነው ያሉት ከንቲባው በመግለጫቸው።

  ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን።
149 views21:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:25:09
ታዳጊዋ የ10,000.00 ዶላር ሽልማቷን ለብፁዕነታቸው አበረከተች!
ይችን ድንቅ ብላቴና ሎዛ ትባላለች። በትምህርቷ እጅግ ድንቅ ብቃት በማስመዝገቧ የ10ሺ ዶላር ሽልማት ትምህርት ቤቷ ይሸልማታል።
ልበ በርሀኗ ሎዛ በአሜሪካ በተለያዩ ከተሞች እየዞሩ ለፈረሰችው ወልድያ እና ላሊበላ ገንዘብ እየሰበሰቡ ለሚገኙት ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ቃል ገብታ ሰነበተች።

ታዲያ ዛሬ በቅዱስ ገብርኤል ዲሲ የተገኙት ብፁእነታቸው እዚህም በመሰብሰብ ላይ እያሉ ይች ትንሽዬ ብላቴና "ካለኝ ላይ ቀንሼ ሳይሆን የተሸለምኩትን ሙሉ ብር ይሄው እውቀቱን የሰጠኝ አምላክ ነው እሱ የሰጠኝን ለሱ" ብላ ሙሉውን ሰጠች።

እንዴት መባረክ መመረጥ ነው?!
የዘመኑ ሰው እንኳን ያለውን ካለው ላይ ማካፈል በማይፈልግበት በዚህ ዘመን ልበ ብርሀኑዋ ሎዛ ሙሉ የሽልማት ገንዘቧን ለግሳለች።
10,000.00$ ዶላር አሜሪካ ላይ ትልቅ ገንዘብ ነው ።ይህ ለኛ ንፉጎቹ ትልቅ ትምህርት ነው

እባካችሁ ሎዛን መርቁልኝ ከዚህ በላይ እውቀቱን ያድልሽ በሉልኝ ተባረኪ እህታችን!!

via- orthodox tewohido network
566 views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:07:09
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው፣ በአልጄሪያ ያደረጉትን የስራ ጉብኝት አጠናቅቀው ወደ #ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

Finishing the working visit to Algeria, Prime Minister Abiy Ahmed and his delegation have returned to #Ethiopia.

#PMOEthiopia
1.1K views10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:05:23 ከዳባት ከተማ አስተዳደር የፀጥታው ምክር ቤት  በወቅታዊ ዙሪያ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል!

1ኛ. በከተማዉ ዉስጥ ማንኛዉም ሰዉ ከምሽቱ 2:00 ስዓት በኃላ እንቅስቃሴ የተገደበ ነው።

2ኛ. ማንኛዉም መጠጥ ቤቶችና ምግብ ቤቶች ከምሽቱ 2:00 በኃላ አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው

3ኛ. በከተማችን ማንኛውም ተሽከርካሪ ባጃጅን ጨምሮ ከምሽቱ 12:00በ በኋላ እና ጧት ከ12:00 ስዓት በፊት ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ተከልክሏል።

4ኛ. የከተማችን ማህበረሰብ በአደረጃጀቶቹ አካባቢውን የመጠበቅና ከፀጉረ ልውጦች እና ስርጓ ገቦች በንቃት እንዲጠብቅ ።ይህ ሁኔታ ሲያጋጥም ለህግ አካል ጥቆማ መስጠትና በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል የመተባበር ግዴታዎች አስቀምጧል።

5ኛ. በከተማችን የምትገኙ አልጋ ቤቶች ፣ቤት አከራዮች እና ሆቴሎች ማንነቱ ያልታወቀ ማንነቱን በመለየት በመረጃ ፎርም ሞልቷ ማከራየት እና አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም ለህግ አካላት እንድታሳውቁ።

6ኛ. የባጃጅ አሽከርካሪዎች ከዳባት ዳራ እና ከዳባት ወቅን ብቻ እንድታሽከረክሩ የተወሰነ ሲሆን ከዳባት ወደ አጅሬ መስመርና ከዳራ ገደብየ ማሽከርከር የተከለከለ ነው።

7ኛ. የዳባት ከተማ ፈቃድ የሌለዉ ባጃጅ ከዳባት ወደ ሌላና ከሌላ ቦታ ወደ ዳባት ማሽከርከር ተከልክሏል።

8ኛ. ለፀጥታ ስራ ከተሰማሩት ዉጭ ማንኛዉም ግለሰብ የጦር መሳሪያ ይዞ በከተማ መንቀሳቀስና በመጠጥ ቤትም ሆነ ምግብ ቤቶች ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

9ኛ. ወራሪና አሸባሪዉ የህዉሓት ቡድን ከሚያሰራጨው የሀሰት ፕሮፖጋንዳና ለህዝባችን ስነ ልቦና የማይነጥኑና ለጠላት ጉልበት የሚሆኑ ወሬዎችን ከማሰራጨት ሁሉም ህዝብ እንዲቆጠብ

10ኛ. በከተማችን ተከራይተዉ የሚኖሩ ኤርትራዊያን ስደተኞች ጋር ተያይዞ ወደ ካፕ የሚመለሱበት ምቹ ሁኔታ እንዲመቻች ከሚመለከታቸዉ አካለት ጋር ስራ እየተሰራ መሆኑን የከተማችን ህዝብ እንዲገነዘብ እያሳሰብን ከዚህ ጎን ለጎን ስራዎች ስለሚያስፈልጉ

ሰርጎ ገቦች  ሊኖሩ ስለሚችሉ ጉዳዩ በጥንቃቄ በፀጥታ ሀይሉ እየተገመገመ የሚመራና የሚከወን ይሆናል ይህ ተግባር በጥንቃቄ  ካልተመራ ለከተማችን የሚኖረዉ አሉታዊ ተጽኖ ከፍ ያለ በመሆኑ ህዝባችን ጉዳዩን በእያለበት ክትትል እንዲያደርግ።
  
ሁሉም አከራይ ተክክለኛ ኤርትራዊ ስደተኛ መሆኑን ማረጋገጥና እንቅስቃሴዉን መከታተል የተለየ ነገር ሲመለከት ለፀጥታ መዋቅሩ እንዲጠቁም።
1.1K views10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 12:53:55
ወልዲያ አደርን ጠላት በከበባ ውስጥ አድርጎ ሊበትነን ቢመኝም እስከ ቀኑ 5: :00 ሠዓት   ድረስ በጀኔራል ሀሠን ከረሙ  በአዋጊው ሻለቃ ሞገስ ከበደ,  በደምሌ አራጋው ,  በወርቄ ጀግኖች እየተመራ  በአማራ የወሎ ፋኖ ጦር ከመከላከያ  ከልዩሀይል ጋር በመሆን  ወልዲያን አላሥደፈራትም  ።

በአሁኑ ሠአት በወርቄ ቂልጡ ,በአላ ውሀ, በጎብየ , በሶስት ግንባሮች ተሠልፎ እየተፋለመ ይገኛል ።
ህዝባችን በተረጋጋ መንፈስ ይጠብቅ ጦርነት የብዙ ነገሮች ውጤት ነውና !!!

አማራነት ይለምልም በምስጋን ደስዬ ከስፍራው የተጻፈ
1.0K views09:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:44:43
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አልጀርስ ፕሬዝዳንታዊ ቤተ መንግሥት ሲደርሱ በአልጄሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት አብደልመጂድ ታቡን አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያ እና አልጄሪያ ግንኙነት ላይ መክረዋል።

Prime Minister Abiy Ahmed is welcomed by H.E. Abdelmadjid Tebboune, President of the Republic of Algeria, at the Presidential Palace in Algiers, where the two leaders discussed Ethiopia-Algeria relations.

#PMOEthiopia
1.4K views11:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 13:57:50
የህወሓት ታጣቂዎች በቆቦ ከተማ ንጹሃንን መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ!

ቆቦ ከተማን የተቆጣጠሩት የህወሓት ታጣቂዎች ንጹሃንን መግደላቸውን የራያ ቆቦ ወረዳ ነዋሪዎች ለአል ዐይን አማርኛ ገለጹ።መንግስት የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ ሲባል የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን መልቀቁን መግለጹን ተከትሎ የህወሃት ታጣቂዎች በራያ ቆቦ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮችንና ወጣቶችን መገደላቸውን ነዋሪዎቹ ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸዋል።

ለደህንነታቸውን ሲባል ድምጻቸውን ቀንሰው በስልክ ያነጋገሩን ግለሰብ፤ በከተማዋ ወጣቶች መገደላቸውን ተናግረዋል።በቆቦ ከተማ ስልክ ይዞ መገኘት እንደሚስገድል የተናገሩት አስተያየት ሰጭዋ፤ የተገደሉ ወጣቶች አስክሬን አሁንም አለመነሳቱን ተናግረዋል።አሁን ላይ በቆቦ ከተማ በተለያዩ መንገዶች ላይ የተገደሉ ወጣቶች አስክሬን እንዳለ የተናገሩት ደግሞ ሌላ አስተያየት ሰጭ ናቸው። አሁን ባለው ሁኔታ አስክሬን ማንሳት እንዳልተቻለ የተገለጸ ሲሆን አሁንም ውጊያ እንዳለ ተናግረዋል።

ወጣቶቹ እና አርሶ አደሮቹ “ፋኖ ናችሁ፤ የብልጽግና አባል ናችሁ፤ ሚሊሻ ናችሁ” በሚል ግድያ እየተፈጸመ እንደሆነ ገልጸዋል።በሮቢት ከተማ ብቻ ሁለት ወጣቶች መገደላቸውን ከስፍራው ወደ ወልዲያ የመጣ አንድ አስተያየት ሰጭ ለአል ዐይን አማርኛ ተናግሯል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://am.al-ain.com/article/eye-witnesses-say-tplf-fighters-kills-civilian-in-kobo-town
1.3K views10:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 12:55:03
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአልጄሪያ ዋና ከተማ በሚገኘው የሰማዕታት ሀውልት የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ ስርዓት አከናውነዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአልጄሪያ ዋና ከተማ በሚገኘው የሰማዕታት ሀውልት የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ ስርዓት አከናውነዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአልጀሪያ እያደረጉት ባለው ይፋዊ የስራ ጉብኝት በርዕሰ መዲናዋ አልጀርስ የሚገኘውን የሰማዓታት መታሰቢያ ሙዚየም ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስፍራው የአበባ ጉንጉንም አኑረዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አሕመድ በትናነትናው እለት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አልጀሪያ መግባታቸው ይታወሳል።
1.2K views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 19:57:47
632 views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 19:56:46
569 views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ