Get Mystery Box with random crypto!

ከዳባት ከተማ አስተዳደር የፀጥታው ምክር ቤት  በወቅታዊ ዙሪያ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል! | Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵

ከዳባት ከተማ አስተዳደር የፀጥታው ምክር ቤት  በወቅታዊ ዙሪያ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል!

1ኛ. በከተማዉ ዉስጥ ማንኛዉም ሰዉ ከምሽቱ 2:00 ስዓት በኃላ እንቅስቃሴ የተገደበ ነው።

2ኛ. ማንኛዉም መጠጥ ቤቶችና ምግብ ቤቶች ከምሽቱ 2:00 በኃላ አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው

3ኛ. በከተማችን ማንኛውም ተሽከርካሪ ባጃጅን ጨምሮ ከምሽቱ 12:00በ በኋላ እና ጧት ከ12:00 ስዓት በፊት ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ተከልክሏል።

4ኛ. የከተማችን ማህበረሰብ በአደረጃጀቶቹ አካባቢውን የመጠበቅና ከፀጉረ ልውጦች እና ስርጓ ገቦች በንቃት እንዲጠብቅ ።ይህ ሁኔታ ሲያጋጥም ለህግ አካል ጥቆማ መስጠትና በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል የመተባበር ግዴታዎች አስቀምጧል።

5ኛ. በከተማችን የምትገኙ አልጋ ቤቶች ፣ቤት አከራዮች እና ሆቴሎች ማንነቱ ያልታወቀ ማንነቱን በመለየት በመረጃ ፎርም ሞልቷ ማከራየት እና አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም ለህግ አካላት እንድታሳውቁ።

6ኛ. የባጃጅ አሽከርካሪዎች ከዳባት ዳራ እና ከዳባት ወቅን ብቻ እንድታሽከረክሩ የተወሰነ ሲሆን ከዳባት ወደ አጅሬ መስመርና ከዳራ ገደብየ ማሽከርከር የተከለከለ ነው።

7ኛ. የዳባት ከተማ ፈቃድ የሌለዉ ባጃጅ ከዳባት ወደ ሌላና ከሌላ ቦታ ወደ ዳባት ማሽከርከር ተከልክሏል።

8ኛ. ለፀጥታ ስራ ከተሰማሩት ዉጭ ማንኛዉም ግለሰብ የጦር መሳሪያ ይዞ በከተማ መንቀሳቀስና በመጠጥ ቤትም ሆነ ምግብ ቤቶች ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

9ኛ. ወራሪና አሸባሪዉ የህዉሓት ቡድን ከሚያሰራጨው የሀሰት ፕሮፖጋንዳና ለህዝባችን ስነ ልቦና የማይነጥኑና ለጠላት ጉልበት የሚሆኑ ወሬዎችን ከማሰራጨት ሁሉም ህዝብ እንዲቆጠብ

10ኛ. በከተማችን ተከራይተዉ የሚኖሩ ኤርትራዊያን ስደተኞች ጋር ተያይዞ ወደ ካፕ የሚመለሱበት ምቹ ሁኔታ እንዲመቻች ከሚመለከታቸዉ አካለት ጋር ስራ እየተሰራ መሆኑን የከተማችን ህዝብ እንዲገነዘብ እያሳሰብን ከዚህ ጎን ለጎን ስራዎች ስለሚያስፈልጉ

ሰርጎ ገቦች  ሊኖሩ ስለሚችሉ ጉዳዩ በጥንቃቄ በፀጥታ ሀይሉ እየተገመገመ የሚመራና የሚከወን ይሆናል ይህ ተግባር በጥንቃቄ  ካልተመራ ለከተማችን የሚኖረዉ አሉታዊ ተጽኖ ከፍ ያለ በመሆኑ ህዝባችን ጉዳዩን በእያለበት ክትትል እንዲያደርግ።
  
ሁሉም አከራይ ተክክለኛ ኤርትራዊ ስደተኛ መሆኑን ማረጋገጥና እንቅስቃሴዉን መከታተል የተለየ ነገር ሲመለከት ለፀጥታ መዋቅሩ እንዲጠቁም።