Get Mystery Box with random crypto!

COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE

የቴሌግራም ቻናል አርማ computer_mobile21 — COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE C
የቴሌግራም ቻናል አርማ computer_mobile21 — COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE
የሰርጥ አድራሻ: @computer_mobile21
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.07K
የሰርጥ መግለጫ

Welcome To Computer & Mobile Maintenance Channel.
It Gives You Some Hints To Repair(Improve Performance Of) Your Computer & Mobile By Yourself. ለጠጋኞችም የሚጠቅም ምርጥ ቻናል ነው!
JOIN @Computer_Mobile21
Contact @seen311 or @seen3bot
Group👉 @Computer_Mobile3

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-10 20:36:24 #Graphics_cards #Nividia #AMD

Graphics/Display/Video Card ወይም በትክክለኛ ስሙ GPU /Graphics Process Unit/

አሁን አሁን የምንገዛቸው ላፕቶፖች Graphics card አለው ወይስ የለውም ብሎ ማጣራት የተለመደ ሆኗል። በነገራችን ላይ መጠኑ እና ጠቀሜታው ይለያይ እንጂ ኮምፒውተር የተባለ ነገር ሁሉ በኛ አጠራር ግራፊክስ ካርድ አለው።
Graphics Card ማለት ከ ፎቶ እና ቪዲዮ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ነገሮች በምንጠቀምበት ሰአት ፈጣን እና ከፍተኛ ጥራት ባለው መንገድ አቀናብሮ መስራት የሚያስችል የሒሳብ ቀመር የሚጠቀም Hardware Device ነው።

⇒በተለይም አዳዲስ ጌሞች እና ለ Rendering የሚያገለግሉ ሶፍትዌሮች ለመጠቀም( Photo Shop , Revit...) በጣም አስፈላጊ ናቸው። በተለይ ለ Architecture ተማሪዎች ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው። በአሁን ጊዜ በስፋት የሚታወቁት #Nividia እና #AMD ናቸው።

ሁለት አይነት ካርዶች ሲኖሩ የመጀመርያዎቹ ከ mother board ጋር ተጣብቆ / integrated ሆነው የሚመጡ ሲሆኑ intel በስፋት ይታወቅበታል። ሁለተኛው ደግሞ ለብቻ የሚሸጡ dedicated ናቸው።
እኛ ሀገር በስፋት ከ ላፕቶፖች ጋር integrated ሆነው የሚመጡ ሲሆኑ መጨመርም ሆነ መቀየር የማንችላቸው ናቸው።

ከ Nividia እና ከ AMD የትኛው ይሻላል?

#AMD( Advanced Micro Device) ረዘም ያለ ዕድሜ ያስቆጠረ ሲሆን ግራፊክስ ብቻ ሳይሆን CPU ም ያመርታል። በተለይም የግራፊክስ ካርዶችን በ Radeon Brand የሚወጣ ነው።
#Nividia ባንጻራዊነት በቅርቡ የተመሰረተ ሲሆን ዋና አላማውም ግራፊክስ ካርዶችን ማምረት ነው። በ Geforce Brand የሚወጣ ሲሆን በብቃትም ሆነ በፍጥነት ከ AMD እንደሚሻል ብዙዎቹ ይስማማሉ።
እስካሁን እንደ ባለሞያ እንዳየነው ብዙ ጊዜ fail እያረገ የሚመጣው AMD የተገጠመላቸው ቦርዶች ናቸው።

ኮምፒዩተራችን Graphics card እንዳለው እና እንደሌለው እንዴት ማወቅ እንችላለን?
የ window 10 ተጠቃሚ ከሆናቹ Task Manager ላይ ገብታቹ performance ላይ side bar ላይ ያለውን GPU በመጫን ማየት የምትችሉ ሲሆን
የ window 7 ተጠቃሚዎች ደግሞ Run ( window key + R ) ላይ dxdiag ብላቹ ከጻፋቹ በኋላ በሚመጣላቹ window ላይ display በመጫን ማግኘት ትችላላቹ!
ብዙ ጊዜ ካልተላጠ ደግሞ keyboard አከባቢ ተለጥፎ ይገኛል።

❖ Driver ያልተጫነበት ኮምፒዩተር በጣም ቀርፋፋ እና graphics ካርዱን ማግኘት አይችልም!

❖አንዳንድ ላፕቶፖች ደግሞ ለመሰረታዊ አግልግሎት የሚሆኑ intel graphics እና ከዛ ለበለጡ አገልግሎቶች የሚሆኑ AMD አልያም Nividia geforce graphics ካርዶችን አንድ ላይ ሊይዝ ይችላል።

@computer_mobile21
@computer_mobile21

Read more
https://www.tomshardware.com/features/amd-vs-nvidia-gpus#:~:text=Nvidia%20wins%20for%204K%20and,it%20works%20on%20any%20GPU.

Share share
2.2K viewsSeen above, edited  17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 08:37:29 #Factory_reset
የጠፋብዎትን የሞባይል ስልክ ፓስዎርድ ለመመለስ ምን
ያደርጋሉ?

የሚከተሉትን ስምንት ስቴፖች በሚገባ በመተግበር
የጠፋብዎትን ፓስዎርድ መመለስ ይችላሉ፡፡

#1. በቅድሚያ ቀፎው ላይ ያሉ ሁሉም መረጃዎች የሚጠፉ መሆኑን መረዳት አለብዎት

#2. መጀመሪያ ስልኮን ሙሉ በሙሉ ያጥፉት

#3. ከዚያ የስልኮን የድምጽ መጨመሪያ ቁልፍ፣ የስልኮን
ማጥፊያ እና የመሰላል ቁልፍ ሶስቱንም ባንዴ ተጭነው
ለተወሰነ ጊዜ ይቆዩ

#4. የተወሰኑ ስልኮች በድምፅ መጨመሪያ እና ስልክ
ማጥፊያ ቁልፎችን በመጫን ብቻ ይሰራሉ፡፡

#5. የአንድሮይድ ምስሏ አልያም የስልኮ ብራንድ ስም
ሲመጣ ሁሉንም ቁልፎች ይልቀቁና በድምጽ መቀነሻው
ቁልፍ ወደታች ያሉትን አማራጮች (wip data/factory
reset) ይምረጡ፡፡

#6. ከዚያ ስምንተኛ ተራ ቁጥር ላይ ያለችውን አማራጭ
ይጫኑ (yes delete all user data)

#7. ይህን እንዳደረጉ ስልኮን “reboot” በሚለው
አማራጭ አጥፍተው ያስነሱ፡፡

#8. እንኳን ደስ ያለዎት፡፡ የስልክዎን ፓስወርድ በሚገባ
አጥፍተዋል ማለት ነው፡፡ next የሚለውን በመንካት መከተል ነው። wifi ከጠየቀ ኢንተርኔት ጋር ማገናኘትና email በመሙላት መጨረስ።
አሁን ስልክዎ ላይ app ጭነው እንደፈለጉ መጠቀም ይችላሉ::

@computer_mobile21
@computer_mobile21
Share
4.1K viewsSeen above, 05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 20:50:02
3.3K viewsSeen above, 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 20:49:50 #play_store #Malicious_Apps

በፕሌይ ስቶር ላይ የተጫኑ የአንድሮይድ መተግበሪያዎች ከ300 ሺ በላይ #ተንኮል_አዘል_አጥፊ መተግበሪያዎችን መያዛቸው ተገለፀ

በፕሌይ ስቶር ላይ የተጫኑ የተለያዩ የአንድሮይድ መተግበሪያዎች #ከ300 ሺ በላይ ተንኮል አዘል አጥፊ መተግበሪያዎች (Malicious Apps) በተጠቃሚዎች ስልክ ላይ መጫናቸውን ጥናት አመለከተ፡፡
በፕሌይ ስቶር የሚገኙ በሶስት ቤተሰብ የተከፈሉ አጥፊ የአንድሮይድ መተግበሪያዎች መገኘታቸውን ዘስኬለር ትሬት ላብ (Zscaler's ThreatLab) የተባለ የሳይበር ደህንነት አጥኚ ቡድን አሳውቋል፡፡

እነዚህን አጥፊ መተግበሪያዎች በተጠቃሚ ዲቫይዞች ላይ በሚጫኑበት ወቅት ከሚያደርሱት ጉዳት መካከል የዳታ ስርቆት፣ የአጭር ፅሁፍ ልውውጥ ጠለፋ፣ የማህበራዊ ሚዲያዎች አካውንት ስርቆት እና ከተጠቃሚው እውቅና ውጪ ክፍያ ማስቆረጥንb ያካትታሉ፡፡

ጥናቱ አክሎም ይህንን ችግር የሚያመጡ ከ50 በላይ የሆኑ መተግበሪያዎች ከጎግል ፕሌይ ስቶር እንዲወገዱ የተደረጉ ቢሆንም ከ300ሺ በላይ ተጠቃሚዎች ቀደም ብለው በማውረድ እየተጠቀሙባቸው እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ከነዚህ አጥፊ መተግበሪያ መካከል ለዓብነት ከ5 ሺ ጊዜ በላይ ተጠቃሚዎች እንዳወረዱት የተጠቀሰው ቫኔላ ስናፕ ካሜራ (Vanilla Snap Camera) በተባለው መተግበሪያ አጥፊ ተንኮል አዘል ኮድ ይዞ መገኘቱን ተገልጿል፡፡

ከመሰል አጥፊ መተግበሪያዎች እራስን ለመከላከል ከተሰጡት ምክረ ሀሳቦች መካከል ከፕሌይ ስቶር የምናወርዳቸው መተግበሪያዎች አስፈላጊና መሰረታዊ ካልሆኑ አለማውረድ፣ መተግበሪያዎቹ የግድ አስፈላጊ ከሆኑም ከዚህ ቀደም ተጠቃሚዎች የሚሠጡትን አስተያየቶችን መገምገም እና ችግር እንደሌለባቸው ማረጋገጥ፣ እምነት ሊጣልባቸው ከሚችሉ እና ብዙ ተጠቃሚዎች ካላቸው መተግበሪያ አልሚዎች መጠቀም፣ እንዲሁም መተግበሪያዎቹ ከሚሰጡት አገልግሎት ጋር ብቻ የሚያያዙ ፍቃድ ከዲቫይዞቻችን እንዲያገኙ ማድረግ እና መተግበሪያዎችን መጠቀም ከጀመርንም በኋላ በተከታታይ የዲቫይዞቻችንን የዳታና የባትሪ አጠቃቀም መከታተል ያስፈልጋል፡፡

https://t.me/computer_mobile21
3.3K viewsSeen above, edited  17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 21:37:19 #insufficient_storage
#የሞባይል ስልካችን ሜሞሪ
#ሞልቷል የሚል መልእክት

አብዛኞቻችን በስልካችን ላይ ቪድዮ፣ ሙዚቃ፣ አፕልኬሽን.. ስንጭን ሜሞሪ ሞልቷል (Insufficient storage) የሚል መልእክት እየመጣ የፈለግነውን እንዳንጭን ይከለክለናል።እንዲህ ዓይነት ችግር ሲገጥመን እንዴት ሚሞሪያችንን ነፃ( free) ማድረግ እንደምንችል እንመልከት።
ከዚያ በፊት ግን ሜሞሪ ሞልቷል (Insufficient storage) የሚል መልእክት ለምን ይመጣል?

የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም አንዱ ስራ አፕልኬሽን install ስናደርግ አፕሊኬሽኖችና ከነሱ ጋር የተያያዙ ፋይሎችን ለማስቀመጥ ነው።አፕሊኬሽኖችና ከነሱ ጋር የተያያዙ ፋይሎችን ማስቀመጬ ቦታ ሲያጣ ሜሞሪ ሞልቷል ይለናል።
አፕልኬሽኖች የሞባይላችንን storage ይጠቀማሉ።እንዴት?
1ኛ፦ አፕሌክሽኖቹ ለራሳቸዉ የሚወስዱት ቦታ አለ።
2ኛ፦ የአፕልኬሽኖቹ data ማስቀመጫ የሚጠቀሙበት ቦታ አለ።
3ኛ፦ የአፕልኬሽኑ ካሽ(ጊዜያዊ ፋይል) ማስቀመጫ ቦታ ይፈልጋል።
እነዚህ ካሽ(ጊዜያዊ ፋይሎች) ጣም ብዙ ቦታ ሊይዙ ይችላሉ።
መፍትሄ
ከመፍትሔው በፊት መጀመራያ እስቶሬጃችሁን ምን ምን እንደሞላዉ እዩት።
@computer_mobile21

የስልካችሁ ስቶሬጅ መረጃ ለማየት ከታች ያሉትን ስፔፖች ይከተሉ
Setting ዉስጥ ይግቡ
ከዛ Storage የሚለዉ ዉስጥ ይግቡ ።
ከዚያ የ RAM ፤ Internal Storage ፤ SD Card የያዙትን መጠን በ% ያሳያችሗል።
Internal Storage የሚለዉን ይጫኑት ።
# Avaliable ፦ የሚለው ላይ አሁን ያላችሁ ነፃ የሆነ የሚሞሪ መጠን ነው። System ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ለራሱ እና ከስልኩ ገር ለሚመጡ ለአንዳንድ አፕልኬሽኖች(እንደ Setting ፤ Chrome ፤ Phone ፤GMail ፤Google ፣Contacts ፤ Photo. ..) ለማስቀመጥ የተጠቀመበት memory ያሳየናል።
# Owners የሚለው ላይ እኛ የጫንናቸዉን አፕሌኬሽኖች፣ፎቶዎች፣ ወዘተ በዝርዝር ያሳየናል።
አሁ ከላይ ካያችኋቸው ፋይሎች ዉስጥ ብዙ ቦታ ይዞ ሚሞራያችሁን የሞላዉን ትመርጣላችሁ።
አፕልኬሽን ከሆነ ብዙ ጊዜ የማትጠቀሙበትን uninstall ማድረግ።
@computer_mobile21

# Uninstall ለማድረግ Setting->Apps ከዛ uninstall ለማድረግ የፈለጋችሁትን አፕልኬሽን መርጣችሁ ስትጫኑት uninstall የሚል ሲመጣ አሱን ይጫኑት።
ፎቶ ከሆነ የማትፈልጉትን ፎቶ አየመረረጣችሁ ማጥፋት አለባችሁ።Video ከሆነ የማትፈልጉትን Video እየመረጣችሁ ማጥፋት።Audio ከሆነም ምረጡና ያጥፉ።
ከዚያም Clear data የሚለዉን በመጫን ሚሞሪ ላይ ያሉትን ፋይሎችያጥፉ

SD Card የስልኩ default ማስቀመጫ ለማድረግ ከፈለጋችሁ፦Setting-> Storage->default write disk የሚለዉጋ Phone Storage የሚለዉን ተመርጦ ታገኙታላችሁ አናንተ ግን SD card የሚለዉን ምረጡ።

Join
@computer_mobile21
@computer_mobile21
SHARE SHARE

Read more
https://www.wikihow.com/Fix-Insufficient-Storage-Available-Error-in-Android
1.5K viewsSeen above, 18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 22:06:43 #VIRUSES
ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተሮች እንዴት ነው የሚገቡት?

በዚህ የቴክኖሎጅ ዘመን ኮምፒውተራችን አልያም ስማርት ስልኮቻችን ሁነኛ የመረጃ ማግኛ እና መዝናኛ ከሆኑ ሰነባብተዋል።

ይሁን እንጂ የሰዎችን መረጃ አላስፈላጊ በሆነ መልኩ ለመጠቀም ብሎም መረጃ እና ንብረትን ወደ ግል ለማዞር የሚሞክሩ ሰዎች ስጋት ከሆኑም ቆይተዋል።

ቫይረሶች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ወደ ኮምፒውተራችን ሲገቡ ሙሉ በሙሉ አልያም በከፊል ከጥቅም ውጭ ሊያደርገው ይችላል፤
የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎቻችንም ለሌሎች አሳልፈው የመስጠት እድልም አላቸው።

እናም በተቻለ መጠን ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተራችን ገብተው ጉዳት እንዳያደርሱብን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነጥቦችም የኮምፒውተር ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተሮች የሚገቡበትን መንገድ ያስገነዝባሉ።

የማንቂያ መልዕክቶችን (ኖቲፊኬሽን) ሳናነብ መቀበል ቫይረስ ወደ ኮምፒውተራችን ከሚገባባቸው መንገዶች ዋነኛው የማንቂያ መልዕክቶችን ሳንረዳ መክፈት ነው።
ለምሳሌ፦
1. በኢንተርኔት መረጃዎችን ስናፈላልግ a unique plugin is necessary is required የሚል ማስታወቂያ ሲመጣ ምንም አይነት የደህንነት ስጋት ይኑረው አይኑረው ሳናውቅ እንዲከፍትልት የሚያዘንን ቅደም ተከተል መከተል፤

2. በነፃ የሚለቀቁ ፕሮግራሞችን ከጫንን በኋላ በተደጋጋሚ እንድንጭናቸው የምንጠየቀውንና እያንዳንዱን የኢንተርኔት እንቅስቃሴያችንን ለመረጃ በርባሪዎች አሳልፈው የሚሰጡ ፕሮግራሞችን ማውረድ
የተበከለ ሶፍትዌር መጫን ከኢንተርኔት የምናወርዳቸው ነገሮች ከታማኝ ምንጮች የተገኙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርብናል።

ካወረድን በኋላ ወደ ኮምፒውተራቸን ስንጭን (install ስናደርግም አንቲቫይረስ ሶስትዌር ሊኖረን ይገባል።

ላኪያቸው የማይታወቁ የኢሜል መልዕክቶችን መክፈት
ማንኛውንም ላኪያቸውን የማናውቃቸውን የኢሜል መልዕክቶች ከመክፈታችን በፊት በኦንላይን አንቲቫይረስ ሶፍትዌሮች ስካን ማድረግ ይኖርብናል።

በኢሜል መልዕክቶች አማካኝነት የተለያዩ ቫይረሶች ስለሚላኩ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው።

የተበከሉ ውጫዊ ስቶሬጅ መሳሪያዎች (ሚሞሪ፣ ፍላሽ ዲስክ፣
ሀርድ ዲስክ ወዘተ ኮምፒውተራችን ላይ መሰካትም ሌላኛው ቫይረስ ወደ ኮምፒውተራችን የሚገባበት መንገድ ነው።

የኮምፒውተር ሶፍትዌሮችን በየጊዜው አለማሳደግ አፕዴት አለማድረግ ችግር ላይ እንደሚጥል ይታመናል።

@computer_mobile21
@computer_mobile21
#share

Read more
https://support.microsoft.com/en-us/topic/how-to-prevent-and-remove-viruses-and-other-malware-53dc9904-0baf-5150-6e9a-e6a8d6fa0cb5
1.9K viewsSeen above, edited  19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-11 22:45:55 #D-Link 4G Connect - Apps on Google Play

Mobile application for the easy management of D-Link Personal WiFi Router.
Installs: 10,000+
Updated: April 22, 2021
Size: 23M

@computer_mobile21

Check out "D-Link 4G Connect"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.mifi.connection
6.5K viewsSeen above, edited  19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 05:54:35 ስልካቹን #Factory_rest ከማድረጋቹ በፊት ማድረግ ያለባችሁ ነገር

ስልኩ የራሳቹ ከሆነ እና የራሳቹን Email አድሬስ ያስገባቹበት ከሆነ rest ካደረጋቹት በሁዋላ ስትጠቀሙበት የነበረውን email እንድታስገቡ ስለሚጠይቃቹ password እና email መርሳት የለባቹም ::


ነገር ግን ከሰው ላይ ገዝታቹት ከሆነ እና የገባበትን email ካላወቃቹት ግን ፓተርኑን ወይም የስልኩን ፓስወርድ የምታውቁት ከሆነ ይህንን ነገር ማጥፋት አለባቹ

መጀመሪያ ላይ Setting

About Phone

Software information

Build Number የሚለውን ሶስት ግዜ ስትነኩት

Developer Option ON ይሆናል

ከዛ ወደ setting ትመለሱና developer option ገብታቹ
OME Unlock የሚለውን ታበሩትና ከዛ FactoryRest ማድረግ ትችላላቹ ምንም Email አይጠይቃቹም ማለት ነው።

ወይም factory reset ከማድረጋችሁ በፊት
Setting account remove Google acount

@computer_mobile21
@computer_mobile21

Read more
https://www.google.com/amp/s/wethegeek.com/5-things-to-remember-before-factory-resetting-your-android/amp/
6.0K viewsOnline, edited  02:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-09 05:56:47 #pc_manufacturing_date

የኮምፒውተራችን እድሜ ስንት እንደሆነ ለማወቅ

1. System information በመጠቀም
Search bar ላይ System information ብላችሁ ጻፉ

ክሊክ ስትሉት ከሚመጡት ዝርዝር አማራጮች BIOS Version/date ላይ ኮምፒተሩ የተገጣጠመበትን ቀን ታገኛላችሁ

2. CMD በመጠቀም

አሁንም Search bar ላይ CMD ብላችሁ ጻፉ

open CMD

CMD ሲከፍት systeminfo.exe ብላችሁ ጻፉና ENTER በሉት ከሚመጡት ዝርዝር አማራጮች BIOS Version ላይ ኮምፒተሩ የተገጣጠመበትን ቀን ታገኛላችሁ::

@computer_mobile21
7.3K viewsOnline, 02:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-09 05:55:29 #insufficient_storage
#የሞባይል ስልካችን ሜሞሪ
#ሞልቷል የሚል መልእክት

አብዛኞቻችን በስልካችን ላይ ቪድዮ፣ ሙዚቃ፣ አፕልኬሽን.. ስንጭን ሜሞሪ ሞልቷል (Insufficient storage) የሚል መልእክት እየመጣ የፈለግነውን እንዳንጭን ይከለክለናል።እንዲህ ዓይነት ችግር ሲገጥመን እንዴት ሚሞሪያችንን ነፃ( free) ማድረግ እንደምንችል እንመልከት።
ከዚያ በፊት ግን ሜሞሪ ሞልቷል (Insufficient storage) የሚል መልእክት ለምን ይመጣል?

የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም አንዱ ስራ አፕልኬሽን install ስናደርግ አፕሊኬሽኖችና ከነሱ ጋር የተያያዙ ፋይሎችን ለማስቀመጥ ነው።አፕሊኬሽኖችና ከነሱ ጋር የተያያዙ ፋይሎችን ማስቀመጬ ቦታ ሲያጣ ሜሞሪ ሞልቷል ይለናል።
አፕልኬሽኖች የሞባይላችንን storage ይጠቀማሉ።እንዴት?
1ኛ፦ አፕሌክሽኖቹ ለራሳቸዉ የሚወስዱት ቦታ አለ።
2ኛ፦ የአፕልኬሽኖቹ data ማስቀመጫ የሚጠቀሙበት ቦታ አለ።
3ኛ፦ የአፕልኬሽኑ ካሽ(ጊዜያዊ ፋይል) ማስቀመጫ ቦታ ይፈልጋል።
እነዚህ ካሽ(ጊዜያዊ ፋይሎች) ጣም ብዙ ቦታ ሊይዙ ይችላሉ።
መፍትሄ
ከመፍትሔው በፊት መጀመራያ እስቶሬጃችሁን ምን ምን እንደሞላዉ እዩት።
@computer_mobile21

የስልካችሁ ስቶሬጅ መረጃ ለማየት ከታች ያሉትን ስፔፖች ይከተሉ
Setting ዉስጥ ይግቡ
ከዛ Storage የሚለዉ ዉስጥ ይግቡ ።
ከዚያ የ RAM ፤ Internal Storage ፤ SD Card የያዙትን መጠን በ% ያሳያችሗል።
Internal Storage የሚለዉን ይጫኑት ።
# Avaliable ፦ የሚለው ላይ አሁን ያላችሁ ነፃ የሆነ የሚሞሪ መጠን ነው። System ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ለራሱ እና ከስልኩ ገር ለሚመጡ ለአንዳንድ አፕልኬሽኖች(እንደ Setting ፤ Chrome ፤ Phone ፤GMail ፤Google ፣Contacts ፤ Photo. ..) ለማስቀመጥ የተጠቀመበት memory ያሳየናል።
# Owners የሚለው ላይ እኛ የጫንናቸዉን አፕሌኬሽኖች፣ፎቶዎች፣ ወዘተ በዝርዝር ያሳየናል።
አሁ ከላይ ካያችኋቸው ፋይሎች ዉስጥ ብዙ ቦታ ይዞ ሚሞራያችሁን የሞላዉን ትመርጣላችሁ።
አፕልኬሽን ከሆነ ብዙ ጊዜ የማትጠቀሙበትን uninstall ማድረግ።
@computer_mobile21

# Uninstall ለማድረግ Setting->Apps ከዛ uninstall ለማድረግ የፈለጋችሁትን አፕልኬሽን መርጣችሁ ስትጫኑት uninstall የሚል ሲመጣ አሱን ይጫኑት።
ፎቶ ከሆነ የማትፈልጉትን ፎቶ አየመረረጣችሁ ማጥፋት አለባችሁ።Video ከሆነ የማትፈልጉትን Video እየመረጣችሁ ማጥፋት።Audio ከሆነም ምረጡና ያጥፉ።
ከዚያም Clear data የሚለዉን በመጫን ሚሞሪ ላይ ያሉትን ፋይሎችያጥፉ

SD Card የስልኩ default ማስቀመጫ ለማድረግ ከፈለጋችሁ፦Setting-> Storage->default write disk የሚለዉጋ Phone Storage የሚለዉን ተመርጦ ታገኙታላችሁ አናንተ ግን SD card የሚለዉን ምረጡ።

Join
@computer_mobile21
@computer_mobile21
SHARE SHARE

Read more
https://www.wikihow.com/Fix-Insufficient-Storage-Available-Error-in-Android
6.1K viewsOnline, 02:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ