Get Mystery Box with random crypto!

COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE

የቴሌግራም ቻናል አርማ computer_mobile21 — COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE C
የቴሌግራም ቻናል አርማ computer_mobile21 — COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE
የሰርጥ አድራሻ: @computer_mobile21
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.07K
የሰርጥ መግለጫ

Welcome To Computer & Mobile Maintenance Channel.
It Gives You Some Hints To Repair(Improve Performance Of) Your Computer & Mobile By Yourself. ለጠጋኞችም የሚጠቅም ምርጥ ቻናል ነው!
JOIN @Computer_Mobile21
Contact @seen311 or @seen3bot
Group👉 @Computer_Mobile3

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-01-21 05:23:11 አፕሊኬሽን ከGoogle Play Store ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት አፕሊኬሽኑ #ጎጂ ወይም #ጠቃሚ መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?

ከGoogle Play Store ላይ የምናወርዳቸው አፕሊኬሽኖች ጠቃሚ መሆናቸው የተረጋገጠላቸው እና ጎጂ እንዳልሆኑ የተመሰከረላቸው ናቸው፡፡

ነገር ግን አንድ አንድ ግዜ ጠቃሚ መስለው ጎጂ አፕሊኬሽኖችን Play Store ላይ ልታገኙ ትችላላችሁ፡፡

ታድያ Play Store ላይ አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ስናደርግ አፕሊኬሽኑ ጠቃሚ ወይም ጎጂ መሆኑን እንዴት መለየት እንችላለን?

#1. አፕሊኬሽኑ ምን ያህል ግዜ ዳውንሎድ እንደተደረገ መመልከት

ዳውንሎድ ማድረግ የፈለግንው አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት አፕሊኬሽኑ ምን ያህል ግዜ ዳውንሎድ (Download Count) እንደተደረገ በደንብ መመልከት

ለምሳሌ ዳውንሎድ የምታደርጉት አፕሊኬሽን አንድ ሚሊዮን ግዜ ወይም ከዚያ በላይ ዳውንሎድ እንደተደረገ ካያችሁ ወድያው አፕሊኬሽኑ የተለቀቀበት ቀን በደንብ መመልከት፡፡

ምክንያቱም አብዛኛው አፕሊኬሽን ከተለቀቀበት ግዜ ጀምሮ አንድ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የቆየ ሲሆን ነወ ከሚሊዮን በላይ ዳውንሎድ ሊኖረው የሚችለው፡፡ ስለዚህ እናንተ ማውረድ የፈለጋችሁት አፕሊኬሽን ከተለቀቀ አንድ ዓመት ካልሞላው እና ዳውንሎድ የተደረገው ከሚሊዮን በላይ ከሆነ አፕሊኬሽኑን ከማውረድ ብትቆጠቡ ይሻላል፡፡

#2. ስለ አፕሊኬሽኑ የተሰጡ የተወሰኑ አስተያየቶችን ማንበብ

ዳውንሎድ ማድረግ የምትፈልጉት አፕሊኬሽን ከማውረዳችሁ በፊት ከዚህ በፊት አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ያደረጉ ሰዎች ስለ አፕሊኬሽኑ አስተያየት (Reviews)ያስቀምጣሉ፡፡ እነዚህን አስተያቶች በጥንቃቄ ማንበብ፡፡

ስለ አፕሊኬሽኑ በጣም የሚያማርሩ አስተያየቶች ካነበባችሁ አፕሊኬሽኑ ከማውረድ እንደጥቆጠቡ እመክራለሁ፡፡

#3. የአፕሊኬሽኑ ስምምነት በጥንቃቄ ማንበብ

አፕሊኬሽኑ ከላይ የተጠቀሱትን ፍተሸዎች ካለፈ ዳውንሎድ ታደርጉታላችሁ፡፡ ከዚያ ኢንስቶል ስታደርጉት የአፕሊኬሽኑን ስምምነት በጥንቃቄ ማንበብ ያስፈልጋል፡፡

ሁላችንም ማለት ይቻላል አፕሊኬሽን ኢንስቶል ስናደርግ ስምምነቱን ሳናነብ "Accept" እንላለን፡፡ ልክ አይደለም፡፡
ምክንያቱም የሳይበር ወንጀለኞች ይህንን ባህሪያችን ስለሚያውቁ እኛን ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮችን ስምምነቱ ላይ በማስገባት ጥቃት ሊፈፁሙብን ይችላሉ፡፡

ስለዚህ ስምምነቱን ስታነቡ ለምሳሌ data mining, data sharing, pop-ups ወዘተ የሚሉ ቃላት ከተመለከታችሁ የአፕሊኬሽኑን ኢንስቶሊንግ ሂደት እንድታቋርጡ እመክራለሁ፡፡፡


ስለዚህ ዳውንሎድ ማድረግ የፈለጋችሁት አፕሊኬሽን ቢያንስ እነዚህን 3 ፍተሸዎችን ካለፈ ጎጂ አይደለም ማለት ነው፡፡

Contact @seen3bot
Join
@computer_mobile21
@computer_mobile21
#share
Read more
https://beebom.com/dangerous-android-apps-you-should-not-install/
7.8K viewsOnline, edited  02:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-18 06:55:33 #computer_Printer_connection
ኮምፒውተራችን እንዴት በቀላሉ ከፕሪንተር ጋር ማስተዋወቅ እንችላለን

ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር ለማስተዋወቅ የሚጠቅሙ ብዙ ሶፍትዌሮች እንዳሉ ይታወቃል እንዲሁም ተመሳሳይ  wifi በመጠቀምም በዋየርለስ ወይም ያለ ኬብል ፕሪንተራችንን ከኮምፒውተራችን ጋርም ማስተዋወቅ እንችላለን።

ያለምንም wifi እና software ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር ማስተዋወቅ እንችላለን።

control panel ውስጥ በመግባት device printer እንመርጣለን ወይም start ን በመንካት search box ላይ device and printer ብለን እንፅፋለን።
ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር ማያያዙን እንዳንረሳ።
በመቀጠል add printerን  እንመርጣለን ።search እስኪጨርስ እንጠብቃለን።
add alocal printer የሚለውን መርጠን next እንለዋለን።
በመቀጠል ፕሪንተራችንን ያያዝነው በኬብ ስለሆነ ከሚመጣልን ምርጫ የመጀመሪያውን USB portን እንመርጣለን።next እንለዋለን
አሁን ከሚመጡልን ዝርዝሮች ውስጥ የፕሪንተራችንን ስም በመፈለግ መርጠን next ቀጥሎም next እንለዋለን።
በመጨረሻም print a test page የሚል ይመጣልናል click አርገን test እናደርግና finish ብለን እንጨርሳለን።
wasa electronics

Contact @seen3bot
Join
@computer_mobile21
@computer_mobile21
#share
Read more
https://www.google.com/amp/s/www.wikihow.com/Connect-a-Printer-to-Your-Computer%3famp=1
6.3K viewsSeen above, edited  03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-16 04:35:19 በኮምፒውተራችን አዲስ ዊንዶው ምርት ከጫንን በኋላ ደህንነቱን እንዴት አስተማማኝ እናደርጋለን?
አዲስ ዊንዶውስ ምርቶችን /Windows/ (7፣ 8፣10) ወይም ሌላ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከጫንን በኋላ ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግና ለማሻሻል ከዚህ በታች የተቀመጡትን የደህንነት እርምጃዎች መተግበር ይመከራል፡፡

#1. የዊንዶው ስርዓትን ማዘመን/up to date/ የቅርብ ጊዜ የደህንነት ማዘመኛዎች እና መጠገኛዎችን /updates and patches/ መጫን፡፡

#2. ሶፍትዌሮችን ማዘመን /Update software/ ፕሮግራሞች እና መተግበሪያዎች ሁሉም ዓይነት የቅርብ ጊዜ ማዘመኛዎች እና የደህንነት መጠገኛዎች መኖራቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ የታወቁ ሶፍትዌሮች እንደ ጃቫ ፣ አዶቤ ፍላሽ ፣ አዶቤ ሾክዌቭ ፣ አዶቤ አክሮባት ሪደር የመሳሰሉት ጊዜ ያለፈባቸው ከሆኑ በአጥፊ ተልእኮ ላይ የተሰማሩ ተዋንያን ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎች በቀላሉ ለመድረስ ያስችላቸዋል።

#3. መልሶ ማግኛ ስርዓት መፍጠር/Create a restore point/ ለዊንዶው ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች(OS) የደህንነት ማዘመኛዎች ከተጫነ ቀጣዩ እርምጃ በዊንዶውስ ውስጥ ወደ ነበረበት የመመለሻ ቦታ መፍጠር ነው። በኮምፒተር ላይ ችግርን ሊያስከትሉ የሚችሉ ወይም ስርዓቱ ላይ ማንኛቸውም ለውጦች ከማድረግዎ በፊት የመልሶ ማግኛ አማራጭን ተግባራዊ ማድረግ ይመከራል።

#4. ፀረ-ቫይረስ መጫን Install antivirus product - አስተማማኝ የደህንነት መፍትሔ የሚሰጥ ማለትም ሪልታይም ቅኝት ፣ ራስ-ሰር ዝመና (Automatic update) እና ፋየርዎል ማካተት አለበት

#5. ለባለብዙ ደረጃ የጥቃት መከላከያ ንቁ የደህንነት መፍትሄን መጫን/Install a proactive security solution for multi-layered protection

#6. የምትክ ስርዓት መፍጠር /Back up your system/

#7. መደበኛ አካውንት መጠቀም/ Use a standard user account/

#8. የተጠቃሚ መለያ ቁጥጥርዎን ንቁ ማድረግ/Keep your User Account Control enabled/ - የተጠቃሚ መለያ ቁጥጥር በኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ ያልተፈቀዱ ለውጦችን እንዳይኖሩ ያግዛል።

Contact @seen3bot
Join
@computer_mobile21
@computer_mobile21
#share
Read more
https://www.google.com/amp/s/heimdalsecurity.com/blog/fresh-windows-installation-security-guide/amp/
5.9K viewsTAYE, edited  01:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-10 15:32:35 #software_speedup
#የኮምፒዩተራቹ_operating_system_window_10 ነው?

በምትከፍቱት እና በምትጠቀሙበት ሰአት #እየተንቀራፈፈ_አማሯችዋል? እንግዲያውስ #ፍጥነቱን ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮችን እናያለን።

#1_Power_option
Start menu ላይ power option ብላቹ ፈልጉ ከሚመጣላቹ window ውስጥ high performance የሚለውን ምረጡ

#2_Disable_unwanted_start_up_programs
ይሄ ኮምፒዩተራችንን በምንከፍትበት ጊዜ ያለ እኛ ፍቃድ ፕሮግራሞችን እየከፈተ
ፍጥነቱን ከሚቀንሱ ነገሮች አንዱ ነው። ይሄን ለመከላከል Task manager ላይ መግባት (ይሄን ለማግኘት start menu ላይ right
click አድርጎ ማግኘት ይቻላል አልያም Ctrl Alt እና delete
የሚለውን አንድ ላይ መጫን)
ከሚመጣው window ውስጥ start up ላይ በማድረግ የማትፈልጉትን ፕሮግራሞች disable ማድረግ። እዚህ ጋር impact የሚለው high ከሆነ
disable ባታረጉ ይመረጣል።

#3_Defragment_and_optimize_drive
Start menu search bar ላይ defragment ብሎ መፈለግ Window ሲመጣላቹ የምትፈልጉትን driver መርጣቹ
optimize ማድረግ

#4_Delete_unnecessary_temporary_file
Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን
መምረጥ አልያም
window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን
የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን
ሁሉንም ሲመርጥልን
ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ
folder ውስጥ
ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት
አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ
የሚመጣላቹ
folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።
እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ
ፋይሎች ስለሆኑ
ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።

#5_Clean_up_Memory
This pc ውስጥ ገብታቹ የምፈልጉት local ዲስክ ላይ right click በማድረግ property መምረጥ Disk clean up የምትለውን icon click ማድረግ የሚመጣውን የ warning box ok ማድረግ
እዚህ ጋ recycle bin ውስጥ ያሉ ፋይሎች ሳይቀሩ ነው የሚጠፉ ት

#6_Reduce_run_time_service
Run box ከፍታቹ msconfig ብሎ መጻፍ ቀጥሎ ከሚመጣው window service የሚለውን መጫን በመቀጠል hide all microsoft service የሚለውን tickvማድረግ
በመቀጠል disable የምትለዋን icon click ማድረግ

#7_Registry_tweaks
Run box መክፈት(window key + R) regedit ብሎ መጻፍ
Hkey -current user
Control panel Mouse
Mouse hover time
valueን ወደ 10 መቀየር
እዛው folder ላይ desktop መምረጥ Menu show delay
Valueን ወደ 10 መቀየር

#8_visual_effects
Start menu ላይ System ብሎ መፈለግ Advanced system setting መምረጥ
Advance ውስጥ በመግባት setting መምረጥ Adjust for best performance መምረጥ ቀጥሎ የምትፈልጉት ነገር ካለ ቲክ በማድረግ መምረጥ
በመጨረሻም ከላይ ያሉትን ከጨረስን በኋላ ኮምፒዩተራችንን
Restart ማድረግ::

Contact @seen3bot

@computer_mobile21
6.1K viewsTAYE, edited  12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-31 08:54:33 #mobile_problems
ተደጋጋሚ የሞባይል ስልክ ችግሮች እና መፍትሔዎች
@computer_mobile21

#1.ለሌላ ሰዉ ድምጽ ይሰማል፡፡ ነገር ግን በጣም አነስተኛ ሲሆን ወይም የራቀ ድምጽ ሲሆን 909 ወይም 904 መደወል ጥሪዉ ሲጀምር የድምፅ መጨመሪያ ቁልፍን በመጫን ድምጹን መጨመር ችግሩ ካልተፈታ ስፒከር ቀዳዳን ማፅዳት ከላይ በተገለጡት መንገዶች ካልተፈታ ስፒከሩን መቀየር ይኖርብናል፡፡

#2.የስልካችን ጥሪ ከተወሰኑ ሰከንዶች ወይም ደቂቃዎች በኋላ ይቋረጣል፡፡ የስልካችን የጥሪ መቼት ላይ የጥሪ ገደብ /ኮል ታይም ሊሚት/Call time limit/ የሚለውን ማጥፍት በተለይ ቻይና ስልክ ላይ auto quick end የሚል መቼትን ማጥፍት፡፡
call record
General call setting
More
Auto quick -end
Off
@computer_mobile21

#3.የቻይና ስልኮች ላይ ኪፓዱ ላይ ያለዉ ብርሀን ይታያል፣ በተጨማሪም ስክሪኑ ላይ ምስሎች ይታያሉ፡፡ ነገር ግን የስክሪኑ ብርሀን የማይታይ ከሆነ
ሁሉም የቻይና ስልኮች ስክሪናቸዉ ላይ ሶስት፣ አራት ወይም አምስት የስክሪን ዳዩድ መስመሮች ይገኛሉ፡፡ እነኝህ መስመሮች ከስክሪኑ ጋር የተበየዱበት ሊድ ሊለቅ ወይም ስክሪኑ ከቦርዱ ጋር የተበየደበት ቦታ ላይ የስክሪን ብርሀን መስመሮች ተላቀዉ ከሆነ በድጋሜ ፔስትና ሊድ በመጠቀም እያንዳንዱን እግር በአግባቡ መበየድ፡፡

#4.Insert SIM የሚል ጥሁፍ የሚያሳይ ከሆነ ሲም ካርዱ የሚሰራ መሆን አለመሆኑን የሚሰራ ስልክ በመጠቀም ማየት የሲም መርገጫ ብረቱን በእጃችን መጫን ሲም ኮኔክተሩን በቲነር ማጠብ እንደ 1110,6030,2600,2610,2310,1600 ያሉ ኖኪያ ስልኮች ላይ የሚሰራ ሲም ተጠቅመን Insert
Sim የሚል ጥሁፍ የሚያሳይ ከሆነ ቻርጅ ኮኔክተሩን ማፅዳት ወይም መቀየር ቻርጅ ኢንተርፌስ አካባቢ በቲነር ማፅዳት

#5.ባትሪ ሲገባበት ቫይብሬተር የሚያደርግ ከሆነ / ስልኩን ሳናበራዉ ልክ ባትሪ እንደገባበት በራሱ ቫይብሬት የሚያደርግ ከሆነ/ DCT3 ስልክ ከሆነ ዩአይ አይሲን መቀየር ሌሎች ስልኮች ላይ ፓወር አይሲ መቀየር

#6.ኔት ወርክ የሌለው ስልክ አንቴና ኢንተርፌስ ወይም ከቦርዱ ጋር በአግባቡ መግጠሙን ማረጋገጥ ቦርዱን በቲነር ማጠብ አንቴና ስዊቹን ማሞቅ ኔትወርኩ አሁንም ካልተስተካከለ ደግሞ አንቴና ስዊች መቀየር

#7.እኔ የምናገረው ይሰማል ሌላ ሰዉ የሚናገረዉ አይሰማኝም ስፒከሩን መቀየር
@computer_mobile21

#8.ሰዉ የሚያወራው የሚሰማ ከሆነ ነገር ግን እኛ የምናወራው የማይሰማ ከሆነ ማይኩን መቀየር

#9.ወጭ ጥሪ ያደርጋል ነገር ግን አይቀበልም ኮል ዳይቨርት በርቶ ከሆነ ማጥፍት

#10.ከቁጥሮቹ መካከል አንዱ ብቻ ተነጥሎ የማይሰራ ከሆነ ቁጥሩ ላይ የሚያርፈዉን አልሙኒየም ማፅዳት

#11.ተንሸራታች ስልክ ላይ ያሉት ቁልፎች አይሰሩም ፣ከታች ያሉት ቁጥሮች በሙሉ ይሰራሉ
ኬብል መቀየር

#12.የምን ሰማዉ ድምጽ ይንጫጫል/ ከሌላ ሰዉ ጋር ስንነጋገር/ ስፒከር መቀየር

#13.ቁጥሮች መደዳ የማይሰሩ ከሆነ ኪፓድ አይሲን ማሞቅ ወይም መቀየር

#14.ስልኩ ክፍለሃገር ሲሄድ ኔትወርኩ አይሰራም ኔትወርክ ፊልተሩን መቀየር

#15.ስልክ ስናወራ የቁልፍ መጫን ድምፅ ይሰማናል/ ሳንነካዉ በራሱ ቁጥር ይደረድራል/ ኪፓድ አይሲን መቀየር

#16. ኔትወርክ ሙሉ ሁኖ ልክ ስንደዉል ኔትወርኩ ዜሮ ይሆናል ፓወር አምፕሊፋየሩን ማሞቅ ወይም መቀር

JOIN
@computer_mobile21
@computer_mobile21
Share share
6.5K viewsSeen above, 05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-20 20:16:43 #insufficient_storage
#የሞባይል ስልካችን ሜሞሪ
#ሞልቷል የሚል መልእክት

አብዛኞቻችን በስልካችን ላይ ቪድዮ፣ ሙዚቃ፣ አፕልኬሽን.. ስንጭን ሜሞሪ ሞልቷል (Insufficient storage) የሚል መልእክት እየመጣ የፈለግነውን እንዳንጭን ይከለክለናል።እንዲህ ዓይነት ችግር ሲገጥመን እንዴት ሚሞሪያችንን ነፃ( free) ማድረግ እንደምንችል እንመልከት።
ከዚያ በፊት ግን ሜሞሪ ሞልቷል (Insufficient storage) የሚል መልእክት ለምን ይመጣል?

የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም አንዱ ስራ አፕልኬሽን install ስናደርግ አፕሊኬሽኖችና ከነሱ ጋር የተያያዙ ፋይሎችን ለማስቀመጥ ነው።አፕሊኬሽኖችና ከነሱ ጋር የተያያዙ ፋይሎችን ማስቀመጬ ቦታ ሲያጣ ሜሞሪ ሞልቷል ይለናል።
አፕልኬሽኖች የሞባይላችንን storage ይጠቀማሉ።እንዴት?
1ኛ፦ አፕሌክሽኖቹ ለራሳቸዉ የሚወስዱት ቦታ አለ።
2ኛ፦ የአፕልኬሽኖቹ data ማስቀመጫ የሚጠቀሙበት ቦታ አለ።
3ኛ፦ የአፕልኬሽኑ ካሽ(ጊዜያዊ ፋይል) ማስቀመጫ ቦታ ይፈልጋል።
እነዚህ ካሽ(ጊዜያዊ ፋይሎች) ጣም ብዙ ቦታ ሊይዙ ይችላሉ።
መፍትሄ
ከመፍትሔው በፊት መጀመራያ እስቶሬጃችሁን ምን ምን እንደሞላዉ እዩት።
@computer_mobile21

የስልካችሁ ስቶሬጅ መረጃ ለማየት ከታች ያሉትን ስፔፖች ይከተሉ
Setting ዉስጥ ይግቡ
ከዛ Storage የሚለዉ ዉስጥ ይግቡ ።
ከዚያ የ RAM ፤ Internal Storage ፤ SD Card የያዙትን መጠን በ% ያሳያችሗል።
Internal Storage የሚለዉን ይጫኑት ።
# Avaliable ፦ የሚለው ላይ አሁን ያላችሁ ነፃ የሆነ የሚሞሪ መጠን ነው። System ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ለራሱ እና ከስልኩ ገር ለሚመጡ ለአንዳንድ አፕልኬሽኖች(እንደ Setting ፤ Chrome ፤ Phone ፤GMail ፤Google ፣Contacts ፤ Photo. ..) ለማስቀመጥ የተጠቀመበት memory ያሳየናል።
# Owners የሚለው ላይ እኛ የጫንናቸዉን አፕሌኬሽኖች፣ፎቶዎች፣ ወዘተ በዝርዝር ያሳየናል።
አሁ ከላይ ካያችኋቸው ፋይሎች ዉስጥ ብዙ ቦታ ይዞ ሚሞራያችሁን የሞላዉን ትመርጣላችሁ።
አፕልኬሽን ከሆነ ብዙ ጊዜ የማትጠቀሙበትን uninstall ማድረግ።
@computer_mobile21

# Uninstall ለማድረግ Setting->Apps ከዛ uninstall ለማድረግ የፈለጋችሁትን አፕልኬሽን መርጣችሁ ስትጫኑት uninstall የሚል ሲመጣ አሱን ይጫኑት።
ፎቶ ከሆነ የማትፈልጉትን ፎቶ አየመረረጣችሁ ማጥፋት አለባችሁ።Video ከሆነ የማትፈልጉትን Video እየመረጣችሁ ማጥፋት።Audio ከሆነም ምረጡና ያጥፉ።
ከዚያም Clear data የሚለዉን በመጫን ሚሞሪ ላይ ያሉትን ፋይሎችያጥፉ

SD Card የስልኩ default ማስቀመጫ ለማድረግ ከፈለጋችሁ፦Setting-> Storage->default write disk የሚለዉጋ Phone Storage የሚለዉን ተመርጦ ታገኙታላችሁ አናንተ ግን SD card የሚለዉን ምረጡ።

Join
@computer_mobile21
@computer_mobile21
SHARE SHARE

Read more
https://www.wikihow.com/Fix-Insufficient-Storage-Available-Error-in-Android
8.8K viewsOnline, edited  17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-14 12:44:53 ሰላም ሰላም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች
ደሴ ፣ባህር ዳር ፣ ጎንደር፣ አዲስ አበባ፣....አካባቢ በደንብ የሚያሰለጥን የኮምፒዩተርና የሞባይል ጥገና ማሰልጠኛ ተቋም ጠቁሙን

@seen3bot ወይም @Seen311 ላይ አድርሱን

group @Computer_Mobile3

@computer_mobile21
@computer_mobile21
7.3K viewsSeen above, edited  09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-09 19:44:39 WINDOWS 10x

ዊንዶውስ 10X ወንጀልን ለመከላከል የሚያግዝ #የፀረ_ሌብነት ጥበቃ ሊጨመርበት ነው።

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ #ማይክሮሶፍት የተሰረቁ ኮምፒውተሮች እንደገና ተስተካክለው ወይም (resetting) ተደርገው ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የሚያስችል አዲስ የፀረ-ሌብነት ጥበቃ (anti-theft protection) በዊንዶውስ 10X ላይ እያዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል፡፡
@computer_mobile21

ይህ ዊንዶውስ የተጫነባቸው ኮምፒውተሮች የፀረ-ሌብነት ጥበቃ ሞድ ከተጨመረላቸው በኋላ የግድ በተሰጣቸው የማይክሮሶፍት አካውንት የይለፍ ቃል የሚገለገሉ ሲሆን ይህን ኮምፒውተር ዳግም ለማስጀመር የሚፈልግ ሰውም ይህን የይለፍ ቃል የግድ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
ይህ ደግሞ ማንኛውም የተሰረቀ ኮምፒውተር እንደገና ተስተካክሎ ወይም (reset) ተደርጎ ጥቅም ላይ እንዳይውል በማድረግ የሌብነት ወንጀልን ለመቀነስ ሊያግዝ ይችላል፡፡
በዚህ ዊንዶውስ የሚገለጉ ሰዎች ንብረታቸው ቢሰረቅ እንኳን በአዲሱ ጥበቃ አማካኝነት ኮምፒውተራቸውን በማንኛውም ቦታ ሆነው መቆለፍ የሚያስችላቸው ሲሆን፤ ጎግል ባቀረበው ‘Find my device’ በተባለው የመፈለጊያ አማራጭ ደግሞ የኮምፒውተሩን መገኛ ሊረዱ ይችላሉ፡፡
የማይክሮሶፍት ባለሙያዎች እንደጠቀሱት አዲሱ የፀረ-ሌብነት ጥበቃ አሁን ላይ ሊሰራበት የታሰበው የዊንዶውስ አይነት መደበኛው ዊንዶውስ 10 ሳይሆን በሱ ቨርዥን በቀረበው ዊንዶውስ 10X ላይ የሚሰራ ሲሆን ወደፊት በሌሎች የዊንዶውስ አይነቶች ላይ የመተግበር እቅድ እንዳለም አስረድተዋል፡፡

ዊንዶውስ 10X አሁን ላይ ባለሁለት ስክሪን ባላቸው የኮምፒውተር አይነቶች ላይ እየተሞከረ ያለ ቢሆንም ወደፊት በሌሎች መደበኛ የላፕቶፕ አይነቶች እና የኮምፒውተር ዝርያዎች ላይ የመጠቀም እድል ሊኖር ይችላል፡፡

Join
@computer_mobile21
@computer_mobile21
Share share

Read more
https://www.google.com/amp/s/www.windowslatest.com/2020/12/23/windows-10x-here-are-the-best-new-features-and-improvements/amp/
8.5K viewsOnline, edited  16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-30 14:32:14
7.9K viewsOnline, 11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-30 14:20:02 #iPhone_13
#አፕል የረቀቁ የተባሉትን አይፎን 13 ስልኮችን አስተዋወቀ

ታዋቂው የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል ከዚህ ቀደም ከነበሩት የላቁ ናቸው
የተባሉትን አይፎን 13 ስልኮችንና አዲስ አይፓድ አስተዋወቀ።
በዚህም አፕል አራት ስልኮችን ያስተዋወቀ ሲሆን እነሱም አይፎን 13 ሚኒ፣
አይፎን 13፣ አይፎን 13 ፕሮ እና አይፎን 13 ፕሮ ማክስ የተባሉ ናቸው።
አይፎን 13 ፕሮ እና አይፎን 13 ፕሮ ማክስ ከጀርባቸው ሦስት ካሜራዎች
ተገጥመውላቸዋል። አፕል ካሜራዎቹ "እጅጉን የረቀቁ የካሜራ ሥርዓት ናቸው"
13 ስልኮች ከተለመዱት በተጨማሪ በሮዝ፣ ሰማያዊ እና ቀይ ቀለማት
አሸብረቀው መጥተዋል።
@computer_mobile21

አዳዲሶቹ አይፎኖች ሚሞሪ መጠንም ወደ 500 ጊጋ ባይት ከፍ ብሏል።
በአይፎን-12 ምርቶች ውስጥ ዝቀተኛ ሚሞሪ 64 ጊጋ ባይነት ነበር። አይፎን-13
ግን ዝቅተኛ የመያዝ አቅሙ ወደ 128 ጊጋ ባይት ከፍ እንዲል ሆኗል።
አፕል ብዙ ደክሞ የተለያየ 'ፊቸር' ያላቸውን ስልኮች ይፋ ከሚያደርግባቸው
ምክንያቶች መካከል ዋነኛው የቀደመውን አይፎን ስልክ የያዙ ደንበኞቹ በአዳዲስ
ሞዴሎች እንዲተኳቸው ለማበረታታት እንደሆነ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች
ይናገራሉ።
ይሁን እንጂ የኢንቨስትመንት ተቋሙ ዌብቡሽ እንደሚለው በመላው ዓለም
የሚገኙ የአፕል ምርት የሆኑ ስልኮችን የያዙ 250 ሚሊዮን ሰዎች ባለፉት 3.5
ዓመታት ስልካቸውን በአዲስ አይፎን ሞዴል አልቀየሩም።
ዋጋ
አይፎን 13 ሚኒ ከ938 ዶላር ጀምሮ፣ አይፎን 13 ከ1076 ዶላር ጀምሮ፣ አይፎን
13 ፕሮ ከ1312 ዶላር ጀምሮ እንዲሁም አይፎን 13 ፕሮ ማክስ 1450
የአሜሪካ ዶላር ጀምሮ ለገበያ ቀርበዋል።
እያንዳንዱ አይፎን 13 ስልክ እንደ ሚሞሪ መጠኑ ዋጋው ይለያያል።
አፕል ዎች 7 እና አይፓድ
አፕል ከስልክ በተጨማሪ ተሻሽሎ የቀረበውን አዲሱን አፕል ዎች
አስተዋውቋል።
አዲሱ አፕል ዎች 7 የገዘፈ ስክሪኑ ላይ ኪቦርድ ተግጥሞለታል። አቧራ መቋቋም
ይችላልም ተብሏል።
@computer_mobile21

የአፕል ኩባንያ አለቃ ቲም ኩክ አዲሶቹን የአፕል አይፓዶች ሲያስተዋውቁ፤
የአይፓድ ሽያጫቸው ባለፈው ዓመት 40 በመቶ ማደጉን ተናግረዋል።
በኮቪድ-19 ምክንያት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን በኢንተርኔት አማካኝነት
ለማስተማር መገደዳቸው የአይፓድ ተፈላጊነትን ጨምሮታል።
አዲሶቹ አይፓዶች ከዚህ ቀደም ከነበሩት የአፕል አይፓዶች 20 በመቶ የፈጠኑ
ይሆናሉ ብለዋል።
የአፕል አይፓዶች ከ329 የአሜሪካ ዶላር ጀምሮ ለገበያ ቀርበዋል።
በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም በርካታ ስማርት ስልኮችን ለገበያ በማቅረብ
የደቡብ ኮሪያው ሳምንስንግ መሪነቱን እንደያዛ ነው። አፕል ደግሞ ሦስተኛ
ደረጃን ይዟል።
የቻይና ኩባንያ የሚያመርታቸው ዢዮሚ ስልኮች በገበያ ደርሻ ሁለተኛ ደረጃ ላይ
ተቀምጠዋል። ኦፖ እና ቪቮ የተሰኙት ስልኮች ደግሞ አራተኛ እና አምስተኛ
ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ብሏል
አፕል ያስተዋወቃቸው አዲሶቹ አይፎን 13 ስልኮች ይዘው ከመጡት ገጽታዎች
[ፊቸሮች] መካከል የበርካቶችን ቀልብ የሳበው፤ 'በፖርትሬይት ሞድ' ቪዲዮ
መቅረጻቸው ነው።
ከዚህ ቀደም ከአይፎን 7 ወዲህ ያሉ የአፕል ስልኮች በፖርትሬይት ሞድ ፎቶ
ማንሳት እንጂ ቪዲዮ መቅረጽ አያስችሉም ነበር።
ፖርትሬይት ሞድ ለምሳሌ አንድን ሰው ከጀርባው ያለውን ዳራ በማደብዘዝ ፎቶ
በሚነሳው ሰው ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ ቀልብ መሳብ የሚችል ምስል
ማንሳት ያስችላል።
አይፎን 13 ደግሞ ይህን ወደ ቪዲዮ ከፍ አድርጎታል። የአፕል ኩባንያ አለቃ ቲም
ኩክ እንደሚሉት ከሆነ ተጠቃሚዎች በፕሮትሬይት ሞድ ቪዲዮ ከቀረጹ በኋላ
ኤዲት ማድረግ የሚያስችለው አይፎን-13 ስልክ ብቻ ነው ይላሉ።
ከዚህ በተጨማሪ አዳዲሶቹ አይፎን ስልኮች ተግባራትን በፍጥነት መከወን
የሚያስችል ሥርዓት ተዘርግቶላቸዋል።
የስክሪን ግጽታቸው የተሻለ ብርሃን አለው። የባትሪ አገልግሎት ከዚህ ቀደም
ከነበሩት አይፎን ስልኮች በ2.5 ሰዓት ከፍ እንዲል ተደርጓል። ከዚህ
በተጨማሪም አይፎን 13 ስልኮች በሮዝ፣ በሰማያዊ እና በቀይ ቀለማት
አሸብረቀው መጥተዋል።

@computer_mobile21
@computer_mobile21

Read more
https://www.apple.com/newsroom/2021/09/apple-unveils-iphone-13-pro-and-iphone-13-pro-max-more-pro-than-ever-before/
7.8K viewsOnline, edited  11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ