2021-09-21 20:17:56
ትናንሽ እቃዎችን ለመያዝ
የኤሌክትሪክ ሽቦዎችን/ገመዶችንና ኮንዲዩቶችን ለማሰር
የኤሌክትሪክ ሽቦዎችን/ገመዶችን ለመጠምጠምና ለማጉበጥ
እንዲሁም የክብ ቅርፅ እንዲይዙ ማድረግ ወዘተ ጥቂቶቹ ናቸው።
19.ኮንዲዩት/ፓይፕ ማጠፊያ (Conduit/Pipe Bender)
በእሳትና በአሸዋ ወይም በእሳት ብቻ በመጠቀም
(አብዛኞቻችን የምንጠቀምበት) ማጠፍ እንችላለን። ነግር ግን
ጊዜ የሚያባክንና እጃችንም የሚጎዳ ስለሆን መሳሪያ መጠቀሙ
አስፈላጊ ነው።
ኮንዲዩት/ፓይፕ ማጠፊያ (Conduit/Pipe Bender)
የተለያዩ አይነት ማጠፊያዎች/Benders ሲኖሩ ከነዚህም ዋና ዋና
የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው።
1.በእጅ የሚሰራ ማጠፊያ (Hand/manual bender)
2. ሀይድሮሊክ(Hadraulic)
3.ኤሌክትሪክ(Electric)
4.ሜካኒካል(Mechanical)
ሲሆኑ በቀላሉ ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ አመች የሆነው እና ለሳይት
ስራ የሚሆነው በእጅ የሚሰራ ማጠፊያ (Hand/manual
bender) ነው። ስለዚህ በዚህ ክፍል የምናየው ይሄን ይሆናል።
በእጅ የሚሰራ ማጠፊያ (Hand/manual bender)
መጠናቸው(sizes) አነስተኛ ለሆኑ ኮንዲዩቶች እና
የኤሌክትሪክ ሀይል የሌለበት ቦታ ላይ በጣም ጠቃሚ ነው።
መጠናቸው ከፍተኛ ለሆኑ ፓይፕ/ኮንዲዩት በተለይ ለቧንቧ
ስራ ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ እንደ አስፈላጊነቱ መርጦ
መጠቀም ተገቢ ነው። ምክንያቱም ማጠፍ በፈለግን ጊዜ
መሳሪያውን የምናቀሳቅሰው በእግራችን ወይም በእጃችን ስለሆን
ከፍተኛ ሀይል/ጉልበት ስለሚጠይቅና አቅማቸውም ውስን ስለሆነ
ነው ለትላልቆችና ብዛት የምናመርት ከሆነ ከላይ ከተዘረዘሩት
ውስጥ መርጠን መግዛት አለብን።
@computer_mobile21
@computer_mobile21
6.0K viewsSeen above, 17:17