Get Mystery Box with random crypto!

#VIRUSES ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተሮች እንዴት ነው የሚገቡት? በዚህ የቴክኖሎጅ ዘመን ኮምፒው | COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE

#VIRUSES
ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተሮች እንዴት ነው የሚገቡት?

በዚህ የቴክኖሎጅ ዘመን ኮምፒውተራችን አልያም ስማርት ስልኮቻችን ሁነኛ የመረጃ ማግኛ እና መዝናኛ ከሆኑ ሰነባብተዋል።

ይሁን እንጂ የሰዎችን መረጃ አላስፈላጊ በሆነ መልኩ ለመጠቀም ብሎም መረጃ እና ንብረትን ወደ ግል ለማዞር የሚሞክሩ ሰዎች ስጋት ከሆኑም ቆይተዋል።

ቫይረሶች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ወደ ኮምፒውተራችን ሲገቡ ሙሉ በሙሉ አልያም በከፊል ከጥቅም ውጭ ሊያደርገው ይችላል፤
የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎቻችንም ለሌሎች አሳልፈው የመስጠት እድልም አላቸው።

እናም በተቻለ መጠን ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተራችን ገብተው ጉዳት እንዳያደርሱብን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነጥቦችም የኮምፒውተር ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተሮች የሚገቡበትን መንገድ ያስገነዝባሉ።

የማንቂያ መልዕክቶችን (ኖቲፊኬሽን) ሳናነብ መቀበል ቫይረስ ወደ ኮምፒውተራችን ከሚገባባቸው መንገዶች ዋነኛው የማንቂያ መልዕክቶችን ሳንረዳ መክፈት ነው።
ለምሳሌ፦
1. በኢንተርኔት መረጃዎችን ስናፈላልግ a unique plugin is necessary is required የሚል ማስታወቂያ ሲመጣ ምንም አይነት የደህንነት ስጋት ይኑረው አይኑረው ሳናውቅ እንዲከፍትልት የሚያዘንን ቅደም ተከተል መከተል፤

2. በነፃ የሚለቀቁ ፕሮግራሞችን ከጫንን በኋላ በተደጋጋሚ እንድንጭናቸው የምንጠየቀውንና እያንዳንዱን የኢንተርኔት እንቅስቃሴያችንን ለመረጃ በርባሪዎች አሳልፈው የሚሰጡ ፕሮግራሞችን ማውረድ
የተበከለ ሶፍትዌር መጫን ከኢንተርኔት የምናወርዳቸው ነገሮች ከታማኝ ምንጮች የተገኙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርብናል።

ካወረድን በኋላ ወደ ኮምፒውተራቸን ስንጭን (install ስናደርግም አንቲቫይረስ ሶስትዌር ሊኖረን ይገባል።

ላኪያቸው የማይታወቁ የኢሜል መልዕክቶችን መክፈት
ማንኛውንም ላኪያቸውን የማናውቃቸውን የኢሜል መልዕክቶች ከመክፈታችን በፊት በኦንላይን አንቲቫይረስ ሶፍትዌሮች ስካን ማድረግ ይኖርብናል።

በኢሜል መልዕክቶች አማካኝነት የተለያዩ ቫይረሶች ስለሚላኩ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው።

የተበከሉ ውጫዊ ስቶሬጅ መሳሪያዎች (ሚሞሪ፣ ፍላሽ ዲስክ፣
ሀርድ ዲስክ ወዘተ ኮምፒውተራችን ላይ መሰካትም ሌላኛው ቫይረስ ወደ ኮምፒውተራችን የሚገባበት መንገድ ነው።

የኮምፒውተር ሶፍትዌሮችን በየጊዜው አለማሳደግ አፕዴት አለማድረግ ችግር ላይ እንደሚጥል ይታመናል።

@computer_mobile21
@computer_mobile21
#share

Read more
https://support.microsoft.com/en-us/topic/how-to-prevent-and-remove-viruses-and-other-malware-53dc9904-0baf-5150-6e9a-e6a8d6fa0cb5