Get Mystery Box with random crypto!

#play_store #Malicious_Apps በፕሌይ ስቶር ላይ የተጫኑ የአንድሮይድ መተግበሪያዎች | COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE

#play_store #Malicious_Apps

በፕሌይ ስቶር ላይ የተጫኑ የአንድሮይድ መተግበሪያዎች ከ300 ሺ በላይ #ተንኮል_አዘል_አጥፊ መተግበሪያዎችን መያዛቸው ተገለፀ

በፕሌይ ስቶር ላይ የተጫኑ የተለያዩ የአንድሮይድ መተግበሪያዎች #ከ300 ሺ በላይ ተንኮል አዘል አጥፊ መተግበሪያዎች (Malicious Apps) በተጠቃሚዎች ስልክ ላይ መጫናቸውን ጥናት አመለከተ፡፡
በፕሌይ ስቶር የሚገኙ በሶስት ቤተሰብ የተከፈሉ አጥፊ የአንድሮይድ መተግበሪያዎች መገኘታቸውን ዘስኬለር ትሬት ላብ (Zscaler's ThreatLab) የተባለ የሳይበር ደህንነት አጥኚ ቡድን አሳውቋል፡፡

እነዚህን አጥፊ መተግበሪያዎች በተጠቃሚ ዲቫይዞች ላይ በሚጫኑበት ወቅት ከሚያደርሱት ጉዳት መካከል የዳታ ስርቆት፣ የአጭር ፅሁፍ ልውውጥ ጠለፋ፣ የማህበራዊ ሚዲያዎች አካውንት ስርቆት እና ከተጠቃሚው እውቅና ውጪ ክፍያ ማስቆረጥንb ያካትታሉ፡፡

ጥናቱ አክሎም ይህንን ችግር የሚያመጡ ከ50 በላይ የሆኑ መተግበሪያዎች ከጎግል ፕሌይ ስቶር እንዲወገዱ የተደረጉ ቢሆንም ከ300ሺ በላይ ተጠቃሚዎች ቀደም ብለው በማውረድ እየተጠቀሙባቸው እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ከነዚህ አጥፊ መተግበሪያ መካከል ለዓብነት ከ5 ሺ ጊዜ በላይ ተጠቃሚዎች እንዳወረዱት የተጠቀሰው ቫኔላ ስናፕ ካሜራ (Vanilla Snap Camera) በተባለው መተግበሪያ አጥፊ ተንኮል አዘል ኮድ ይዞ መገኘቱን ተገልጿል፡፡

ከመሰል አጥፊ መተግበሪያዎች እራስን ለመከላከል ከተሰጡት ምክረ ሀሳቦች መካከል ከፕሌይ ስቶር የምናወርዳቸው መተግበሪያዎች አስፈላጊና መሰረታዊ ካልሆኑ አለማውረድ፣ መተግበሪያዎቹ የግድ አስፈላጊ ከሆኑም ከዚህ ቀደም ተጠቃሚዎች የሚሠጡትን አስተያየቶችን መገምገም እና ችግር እንደሌለባቸው ማረጋገጥ፣ እምነት ሊጣልባቸው ከሚችሉ እና ብዙ ተጠቃሚዎች ካላቸው መተግበሪያ አልሚዎች መጠቀም፣ እንዲሁም መተግበሪያዎቹ ከሚሰጡት አገልግሎት ጋር ብቻ የሚያያዙ ፍቃድ ከዲቫይዞቻችን እንዲያገኙ ማድረግ እና መተግበሪያዎችን መጠቀም ከጀመርንም በኋላ በተከታታይ የዲቫይዞቻችንን የዳታና የባትሪ አጠቃቀም መከታተል ያስፈልጋል፡፡

https://t.me/computer_mobile21