Get Mystery Box with random crypto!

Commercial Bank of Ethiopia - Official

የሰርጥ አድራሻ: @combankethofficial
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 120.27K
የሰርጥ መግለጫ

Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with more than 1800 branches across the country.
@ www.facebook.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 74

2022-08-27 18:11:14
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የደረጃ ጨዋታውን አሸነፈ፡፡
=================

በታንዛኒያ አስተናጋጅነት ሲካሄድ በቆየው እና ዛሬ ፍፃሜውን በሚያገኘው የሴካፋ ክለቦች ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የደረጃ ጨዋታውን በማሸነፍ በ3ኛ ደረጃ አጠናቋል፡፡

ለዋንጫ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶት የነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን በግማሽ ፍጻሜው ከዩጋንዳው ሺ ኮርፖሬት ጋር ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 1 ተሸንፎ ዛሬ ባደረገው የደረጃ ጨዋታ የሩዋንዳውን ኤኤስ ኪጋሊ 3 ለ 1 በመርታት ነው በ3ኛ ደረጃ ያጠናቀቀው፡፡

በጨዋታው የቡድኑ አምበል ሎዛ አበራ፣ አረጋሽ ካልሳ እና ሀሳቤ ሙሶ ጎል ማስቆጠር የቻሉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ሎዛ በ11 ጎሎች የሻምፒዮናው ኮኮብ ጎል አስቆጣሪ ሆና የመጨረስ ሰፊ እድል አላት፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻምፒዮናውን በ3ኛ ደረጃ በማጠናቀቁ የነሀስ ሜዳሊያ እና የ10 ሺ ዶላር ተሸላሚ ሆኗል።
8.1K views15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:19:26
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባዘጋጃቸው 10ኛው ዙር “ይቆጥቡ፣ ይሸለሙ” እንዲሁም 21ኛ፣ 22ኛ እና 23ኛ ዙሮች “ይቀበሉ፤ ይመንዝሩ፤ ይሸለሙ!” መርሃ-ግብሮች ተሳታፊ በመሆን እደለኛ መሆን የቻሉ ደንበኞች ዛሬ ነሀሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም የብሄራዊ ባንክ ገዢ የተከበሩ ዶ/ር ይናገር ደሴ፣ የብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ፍቃዱ ድጋፌ፣ የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ገረመው ጋርጄ፣ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ሥነ-ስርዓት ሽልማታቸውን ተረክበዋል፡፡
7.6K views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 09:13:52
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ነሀሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም በ10ኛ ዙር “ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” እንዲሁም በ21ኛ፣ 22ኛ እና 23ኛ ዙሮች “ይቀበሉ፤ ይመንዝሩ፤ ይሸለሙ!” መርሃ-ግብር ተሳትፈው ተሸላሚ መሆን ለቻሉ ደንበኞች ሽልማታቸውን ያስረክባል ፡፡

2 ባለ ሦስት መኝታ አፓርትመንቶች፣ 13 አውቶሞቢሎች፣ 36 ስድስት ሰዎችን የማሳፈር አቅም ያላቸው ባለ 3 እግር ተሸከርካሪዎች እና 90 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ለእድለኞች የሚተላለፉ ሽልማቶች ናቸው
8.2K views06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:33:14
ነገ ነሀሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም ለ10ኛ ዙር “ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” እንዲሁም ለ21ኛ፣ 22ኛ እና 23ኛ ዙሮች የ “ይቀበሉ፤ ይመንዝሩ፤ ይሸለሙ!” መርሃ-ግብር ተሸላሚዎች ሽልማት የሚተላለፍበት መርሃ-ግብር በባንካችን አዲሱ የዋና መ/ቤት ህንፃ ይከናወናል፡፡
9.6K views07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 14:21:26
አደይ እንቁጣጣሽ 2015 የአዲስ ዓመት የንግድ ትርኢት እና ባዛር
በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እስከ ጷጉሜ 5 ቀን 2014 ዓ.ም
የመግቢያ ትኬቱን በሲቢኢ ብር መተግበሪያ ‘Market Place’ ባሉበት ይቁረጡ!
===================================
የሲቢኢ ብርን መተግበሪያ ሞባይሎ ላይ ለመጫን፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡- https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአይፎን ስልኮች፡- https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
10.4K views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 18:30:55
ለዋንጫ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ለፍፃሜ ሳይደርስ ቀረ፡፡
==========================

በታንዛኒያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የሴካፋ ክለቦች ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ከዩጋንዳውን ሺ ኮርፖሬት ጋር ባደረገው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ  2  ለ 1    ተሸንፎ  ለፍፃሜ ሳይደርስ ቀርቷል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደረጃ ጨዋታውን ከታንዛኒያው ሲምባ ኩዊንስ እና ከሩዋንዳው ኤኤስ ኪጋሊ ተሸናፊ ጋር የፊታችን ቅዳሜ ነሀሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም በአዛም ኮምፕሌክስ ስታዲየም የሚያደርግ ይሆናል፡፡
10.7K views15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 09:33:21
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል፡፡
============================

በታንዛኒያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የሴካፋ ክለቦች ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታውን ዛሬ ከዩጋንዳው ሺ ኮርፖሬት ጋር ያደርጋል፡፡

ቡድኑ በአሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው እየተመራ ምድቡን በአንደኝነት ማጠናቀቁ ይታወቃል፡፡

አምና በመጀመሪያ የሴካፋ ክለቦች ሻምፒዮና ተሳትፎው በሁለተኛ ደረጃ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዘንድሮ የዞኑ ሻምፒዮን በመሆን እ.ኤ.አ በ2022 ማብቂያ በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ለመብቃት ጠንክሮ እየሰራ ነው።
10.6K viewsedited  06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 17:52:24
10.4K views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 17:52:22 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ከ149.8 ቢሊዮን ብር በላይ የፋይናንስ አቅርቦት ማድረጉ ተገለፀ።
===============

ይህ የተገለፀው ዛሬ ነሀሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባብሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን የሚያካሂደው የህዝብ ንቅናቄ እና የሀብት ማሰባሰብ መርሃ ግብር ማስጀመሪያ ዝግጅት ላይ ነው፡፡

በዝግጀቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የግድቡ ሁለተኛ ተርባይን ሃይል ማመንጨት በመጀመሩና የሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌትም በስኬት በመጠናቀቁ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ የግድቡን ግንባታ ለዚህ ስኬት ላበቁ አካላት ሁሉም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ባንኩ የተጠናከረ የሀብት ማሰባሰብ ስራ በማከናወን መልሶ ለሃገራችን ልማትና ወሳኝ ለሆኑ ኘሮጀክቶች በማዋል ላይ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ አቤ፣ እ.ኤ.አ እስከ ሃምሌ 31 ቀን 2022 ድረስ ባንኩ ከሀይል ማመንጫ ስራዎች ጋር ለተያያዙ ጉዳዮች ካቀረበው ከ425.2 ቢሊዮን ብር በላይ ፋይናንስ ከ149.8 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆነው ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የዋለ መሆኑን ተናግረዋል።

ባንኩ ከሚያደርገው የፋይናንስ አቅርቦት በተጨማሪ በአገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ከተከናወነ የቦንድ ሽያጭ እና በልገሳ በርካታ ገንዘብ በማሰባሰብ ለግድቡ ግንባታ እንዲውል ማድረጉንም ነው አቶ አቤ የገለፁት፡፡

ባንኩ በቅርቡ የ200 ሚሊዮን ብር ቦንድ በስሙ መግዛቱን ያስታወሱት አቶ አቤ፣ የባንኩ ሠራተኞችም ከ19.7 ሚሊዮን ብር በላይ ቦንድ በመግዛት ግንባታው እንዲፋጠን ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡

አቶ አቤ ባንኩ ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ ከሀብት ማሰባሰብ ጀመሮ በሚጠበቅበት ሁሉ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠው፣ ባለድርሻ አካላት በሙሉ በጋራ እንዲሰሩ እና ታላቁን የህዳሴ ግድብ በየትኛውም መንገድ እንዲደግፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ የግድቡ ግንባታ 87 ነጥብ 3 በመቶ መጠናቀቁን ገልፀው፣ ቀሪ ስራዎችን በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በእስካሁኑ የግንባታ ሂደት ከ175 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል ያሉት ኢንጂነር ክፍሌ፣ቀሪ ግባታውን ለማጠናቀቅም ከ55-60 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀብት በማሰባሰብ ሂደት ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ እየተወጡ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት መካከል አንዱ እና ዋነኛው መሆኑ ተገልጿል፡፡
9.7K viewsedited  14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 15:31:58
Vacancy
=======
The Commercial Bank of Ethiopia would like to invite qualified and interested job seekers to apply for the following positions:
1. Collateral Valuation Expert- Mechanical Engineer
2. Engineer
3. Legal Advisor
4. IS Auditor - IS Network and Infrastructure Audit
5. IS Auditor - Application System Audit
6. Senior Sanitary Engineer
7. Sanitary Engineer
8. Senior Electrical Engineer
9. Electrical Engineer
10. Mechanical Engineer
11. Architect

Interested and qualified job seekers should apply through CBE career website
(https://vacancy.cbe.com.et ) from August 24 – September 03, 2022.

For requirements and other detail information, please use the following link:
https://combanketh.et/cbeapi/uploads/EXTERNAL_VACANCY_4d7209e01c.pdf
10.3K views12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ