Get Mystery Box with random crypto!

Commercial Bank of Ethiopia - Official

የሰርጥ አድራሻ: @combankethofficial
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 120.27K
የሰርጥ መግለጫ

Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with more than 1800 branches across the country.
@ www.facebook.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 73

2022-09-05 11:28:32
የአሸናፊዎች ዝርዝር
================

ለአሸናፊዎች ሽልማቱ የሚደርሰው በሲቢኢ ብር በመሆኑ የሲቢኢ ብር ደንበኛ ካልሆኑ ወደ *847# በመደወል ወይም የሲቢኢ ብርን መተግበሪያ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ በማውረድና ሞባይልዎ ላይ በመጫን ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግዎ ምዝገባዎን በማካሄድ ሽልማቱን ይቀበሉ፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡- https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአይፎን ስልኮች፡- https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
4.0K views08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 13:03:18
እግር ኳስን በሬዲዮ ሽልማትዎን በሲቢኢ ብር
=====================================

ዛሬ ቼልሲ ከዌስትሐም የሚያደርጉትን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሞዛይክ ስፖርት ጋር በመተባበር በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ ያቀርቡላችኋል።

በፕሮግራሙ እየተዝናኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀው የጥያቄና መልስ ውድድር በመሳተፍ ሽልማትዎን በሲቢኢ ብር መቀበል ይችላሉ።

በሬዲዮ ፕሮግራሙ ላይ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን 454 ሺ ተከታይ ባለውና በሜታ የእውቅና ባጅ በተሰጠው የፌስ ቡክ ገጻችን የውስጥ መስመር (Inbox) ብቻ በመመለስ ይሳተፉ።


ሽልማቱ በሲቢኢ ብር የሚደርስ በመሆኑ ደንበኛ ካልሆኑ ወደ *847# በመደወል ወይም የሲቢኢ ብርን መተግበሪያ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ በማውረድና ሞባይልዎ ላይ በመጫን ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግዎ ምዝገባዎን በማካሄድ ሽልማቱን ይቀበሉ፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡- https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአይፎን ስልኮች፡- https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
5.0K views10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 16:35:46
Call for Written Exam - Building Administration Engineer Applicants
==================

Dear Applicants,

Thank you for your application for the position of Building Administration Engineer for Commercial Bank of Ethiopia.

We are pleased to invite you to take a written exam on Wednesday Sep 07, 2022 at 02:00 local time (Morning) at CBE’s Zagwe Building, Lideta, Addis Ababa.

N.B. You are required to provide your ID card or Passport. Using a mobile phone is prohibited.

Please check name lists of applicants to seat for the written exam using the following link:
https://combanketh.et/cbeapi/uploads/Buil_Admin_Engineer_Telegram_a08b70b385.pdf
5.0K views13:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 12:45:16
ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ!
5.2K viewsedited  09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:56:54
ከውጭ ሀገር ገንዘብ ለማስላክ በርካታ አማራጮች......
1.4K views11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 11:34:03
ወጣቶች በቁጠባ ነገን የሚለውጡበት አቅም መፍጠር ይችላሉ!
3.6K views08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:24:50
በስህተት ወደ ሌላ ሂሳብ የገባ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ለባለቤቱ ተመለሰ።
===================

አቶ ሲሳይ ተስፋዬ በስልካቸው አንድ መልእክት ይደርሳቸዋል፡፡ በወቅቱ ሀሰተኛ መልእክት ስለመሰላቸው ብዙም ትኩረት አልሰጡትም፡፡ በጡረታ ላይ የሚገኙት አቶ ሲሳይ ዘመድም ወዳጅም ይህን ያደርጋል ብለው የሚጠብቁት ነገር ስላልሆነ በሂሳባቸው ብር 501,840.00 መግባቱን የሚናገረውን መልእክት ሀሰተኛ ነው ብለው አምነዋል፡፡

ከጥቂት ቀናት በኋላ ሂሳባቸውን በኤ.ቲ.ኤም ሲያዩ ግን እውነትም ብር 501,840.00 ወደ ሂሳባቸው ገብቷል፡፡ አቶ ሲሳይ በጡረታ ዘመኔ ያገኘሁት ሲሳይ ነው ብለው አልተደሰቱም፡፡ ይልቁንስ በስህተት የገባ ገንዘብ መሆኑ ስለገባቸው የገንዘቡን ባለቤት ማፈላለግ ጀመሩ እንጂ፡፡

ወደ ባንክ በመሄድ የሂሳብ ዝርዝር አስወጥተው ገንዘቡን ወደ ሂሳባቸው ያስገባውን ሰው ስም አገኙ፣ የውጭ ሀገር ዜጋ ነው፡፡ ስልኩን ከባንኩ ተቀብለው ደወሉለት፡፡ እውነትም በስህተት የገባ ገንዘብ መሆኑን አረጋገጡ፡፡ አስፈላጊውን ማጣራት አድርገው የገንዘቡ ትክክለኛ ባለቤት መሆኑን ሲያረጋግጡም ገንዘቡን በታማኝነት መለሱ፡፡

ገንዘቡ ህይወታቸውን ሊለውጥ ቢችልም ህሊናቸውን ግን ሊለውጥ እንደማይችል የተናገሩት አቶ ሲሳይ፣ ገንዘቡን ሲመልሱ የተሰማቸው ደስታ ወደር የለውም፡፡ የሰው ገንዘብ በፍፁም እንደማይፈልጉ እምነታቸው አድርገው የኖሩት አቶ ሲሳይ፣ አጋጣሚው የሚሉትን በተግባር ሆነው ያገኙበት ሆኖ ማለፉን ተናግረዋል፡፡

ገንዘቡ በስህተት ገቢ የተደረገበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን ቅርንጫፍም ለአቶ ሲሳይ ተስፋዬ ታማኝነት እና አራያነት ያለው ተግባር የምስጋና እና የአድናቆት ደብዳቤ ሰጥቷቸዋል፡፡
7.3K views10:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 16:43:45
በታንዛኒያ አስተናጋጅነት ሲካሄድ በቆየውና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በ3ኛ ደረጃ ባጠናቀቀበት የሴካፋ ክለቦች ሻምፒዮና የቡድኑ አምበል ሎዛ አበራ በ11 ጎሎች የኮኮብ ጎል አስቆጣሪ ሽልማትን ወስዳለች፡፡

ሎዛ አምና ኬኒያ ላይ በተካሄደው ሻምፒዮና እንዲሁ በ13 ጎሎች ኮኮብ ጎል አስቆጣሪ እንደነበረች ይታወሳል፡፡
2.7K views13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 15:34:55
እንኳን ደስ አለን!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲቲ ትሬዠሪ እና ትሬድ ሶሉሽንስ ግሩፕ (Citi Treasury and Trade Solutions Group) ተሸለመ!
3.8K views12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:13:56
ደንበኞች ከአጭበርባሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ፡፡
==========================

ደንበኞች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያዘጋጃቸውን የሽልማት ፕሮግራሞች በመንተራስ የሌብነት ተግባር ከሚፈፅሙ አጭበርባሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ አሳሰቡ፡፡

ወደ ደንበኞች ስልክ ደውለው ሽልማት እንደደረሳቸው በመንገርና ገንዘብ እንዲያስገቡ በመጠየቅ ሌብነት የሚፈጽሙ አጭበርባሪዎች መበራከታቸውን አቶ አቤ ገልፀዋል፡፡

ባንኩ ወደ ደንበኞች ስልክ የሚደውልበት አጋጣሚ መኖሩን የተናገሩት አቶ አቤ፣ ነገር ግን ደንበኞቹ ወደ ባንኩ በአካል እንዲቀርቡ ወይም ሰነድ እንዲያቀርቡ እንጂ በስልክ ይህን አስገቡ ያን አስወጡ የሚለው ነገር እንደሌለ አስረድተዋል፡፡

ደንበኞች ከባንክ ነው በሚል ስልክ ሲደወልላቸው ከሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ምንም አይነት እርምጃ መውሰድ እንደሌለባቸው እና በስልክ መረጃ እንዳይሰጡ ያሳሰቡት አቶ አቤ፣ ይልቁንስ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም 951 ላይ በመደወል የመረጃውን ትክክለኛነት ማጣራት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሚሰጠው አገልግሎት ስልክ ደውሎ ምንም አይነት ክፍያ እንደማይጠይቅም ነው አቶ አቤ ያስገነዘቡት፡፡

በተጨማሪም ደንበኞች ሞባይላቸው ሲጠፋባቸው ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎታቸው እንዲቋረጥ ማስደረግ እንዳለባቸው አቶ አቤ አሳስበዋል፡፡
5.0K viewsedited  08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ