Get Mystery Box with random crypto!

Marriage Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ biblicalmarriage — Marriage Tube M
የቴሌግራም ቻናል አርማ biblicalmarriage — Marriage Tube
የሰርጥ አድራሻ: @biblicalmarriage
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.09K
የሰርጥ መግለጫ

ኢሳ 53:10
በቻናላችን
👉 🌷ጋብቻ ምንድነው?🌷
👉 ❤️ማንን ላግባ?❤️
👉 😳ፖርኖግራፊና መዘዙ😳
🚩 የፍቅር ታሪኮች
💝 የርቀት ፍቅር
አጋር ቻናል:- @Nazrawi_tube
ለአስተያየት
👉 @Biblicalmarriage_bot
0910337074
🔵ቅድስና ለእግዚአብሔር🔵

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-07-03 16:36:10
የፖርኖግራፊ ተጠቂ ኖት?
Anonymous Poll
14%
ሀ. አዎ
86%
ለ. አይደለሁም
534 voters2.1K views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 16:34:13
የፍቅር ጓደኛ ለመያዝ ትክክለኛ እድሜ የትኛው ነው?
Anonymous Poll
1%
ሀ. ከ18 አመት በታች
11%
ለ. ከ18-20
13%
ሐ. ከ20 -21
75%
መ. ከ21 በላይ
634 voters2.1K views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 07:22:44
በተለያዩ አጥቢያዎች፣ የወጣቶች ህብረትና የተማሪ ህብረቶች(ኮሌጅና ዩኒቨርስቲዎች) ባገለገልንባቸው ጊዜያት ካስተዋልናቸው ነገሮች ውስጥ የተበላሸ የተቃራኒ ፃታ ግንኙነት፣ ቅድስና የጎደለው እጮኝነት፣ ችላ የተባለ ወጣትነት፣ በትዳር ውስጥ ያሉ ከባድና ውስብስብ ጉዳዮች፣ የፖርኖግራፊ ችግር...ወዘተ አስተውለናል።

በዚህ ሁሉ ግን ቤተ ክርስቲያን ምን ያክል ዝም እንዳለችና ብዙዎች ደጋፊና መካሪ እንዲሁም አቅጣጫ ጠቋሚ ያጡ ወጣቶች መብዛታቸው ብሎም በጭንቅ ውስጥ ያለ ጋብቻ እንዳለ ግልፅ ነው።

ወጣቶች የንፅህና ጉድለት ተገኝቶባቸው ከአጥቢያና ከህብረት ከማገድ በፊት እንዲሁም ባለትዳሮች ትዳራቸው በፍቺ ከመቋጨቱ በፊት ቤተ ክርስቲያን ትኩረት ሰጥታ ስልጠዎችንና የፀሌት ጊዜዎችን ልታዘጋጅ ይገባል!

ልንረዳችሁ የምትፈልጉ ወገኖች ስልካችን ክፍት ነው።

ተባረኩ!


@Biblicalmarriage
2.2K views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 21:46:28
በድሬዳዋና ሐረር አካባቢ ለምትገኙ ቅዱሳን በሙሉ!
CJ እና የድሬዳዋ አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በመተባበር ከሐምሌ 9 እስከ 10 የሚቆይ ኮንፍራንስ የተዘጋጀ ሲሆን በዕለቱ ሳቢያን ስታዲየም በመገኘት እንድትካፈሉ እናሳውቃለን!

#ታላቅ_ደስታ_ይሆናል!
2.5K views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 00:08:40 የተቃራኒ ፆታ ጓደኝነት ፅንሰ ሐሳብ መነሻ

••• የተቃራኒ ፆታ ጓደኝነት አሁን የመጣ ሀሳብ ወይም ሰይጣን እኛን ለማጥመድ ብሎ የፈጠረው ሳይሆን በእግዚአብሔር የዘላለም ፕሮግራም ውስጥ የነበረ ደግሞም ኃጢያት ወደ ምድር ከገባ በኋላ ምንም እንኳን የዘላለም ዕቅድነቱ ቢቀርም የእግዚአብሔር መልካም ሐሳብ ሆኖ የቀጠለ ነው፡፡
••• ለአዳም እግዚአብሔር እጅግ በጣም ብዙ ነገሮችን ሰጥቶታል ለምሳሌ ምንም የማይጎድልበትን መኖሪያ (ኤድን ገነት)፣ በጣም ብዙ አይነት ዝርያ ያላቸውን እንስሳት፣ ለመብላት ደስ የሚያሰኙ ፍራፍሬዎችን፣ ወዘተ... ነገር ግን ይሄ ሁሉ ሲሆን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር :: (ዘፍ 2፤20)
ለመጀመሪያ ጊዜ አዳም የተሟላ የደስታ ኑሮ መኖር የጀመረው እንደ እርሱ ያለች ረዳት ሔዋን ስትፈጠርለት ነበር፡፡

••• እንደውም እግዚአብሔር ከአዳም የጎን አጥንቱ ላይ ወስዶ ሔዋንን በመፍጠር ወደ አዳም ሲያመጣት በሚገርም ሁኔታ ከየት እንደመጣች እንኳን ማንም ሳይነግረው በቀጥታ እንዲህ ነበር ያለው “አዳምም አለ፦ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።” (ዘፍ 2፤23-24)
ይሄ የሚያሳየን የሴትና ወንድ ጓደኝነት የሰይጣን ፈጠራ ወይም ደግሞ የሰዎች ስሜት ብቻ የፈጠረው ሳይሆን ከጅምሩ የእግዚአብሔር መልካም ሐሳብ እንደነበረ ነው፡፡
••• እንደዚህ መልካምና ደስ የሚያሰኝ ለጥቅማችንም የተፈጠረ ሆኖ እያለ ግን አዳም በሰራው ኃጢያት ምክንያት ሰው ስለወደቀ ሰይጣንም ለክፉ ስራው ማስፈፀሚያነት ይጠቀምበት ጀመር፡፡
እኛ ክርስቶስ ኢየሱስን አምነን ከመንፈስ ቅዱስ ዳግም የተወለድን ቅዱሳን በሙሉ ለየት የሚያደርጉን ነገሮች ውስጥ አንዱ በሰይጣን ተበላሽቶ ከወደቀው ዓለም የተዋጀንና በአዲሱ አዳም (ኢየሱስ) የዘር ግንድ የገባን መሆናችን ነው፡፡
••• የወደቀውና የተበላሸው ዓለም ውስጥ ያሉ ሰዎች የራሳቸው የሆነ የአኗኗር ስርአትና የሚመሩበት ሕግ (መልካምም ሆነ ክፉ) እንዳላቸው ሁሉ እኛም ደግሞ የሚገዛንና ስርአት የሚያስይዘን የህይወት መንፈስ ሕግ አለን፡፡
••• ስለ ሰው ለሚፈጠርብን ማንኛውም ጥያቄ መልስ የምናገኘው መሪያቸን ከሆነው መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ እና ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር ሴት እና ወንድ እርስ በርስ እንዲፈላለጉ እና እንዲፋቀሩ የሚያደርግ ስሜት በውስጣቸው አስቀምጧል፡፡
••• እንግዲህ የተቃራኒ ፆታ ጓደኝነትና የትዳር ዲዛይነር እግዚአብሔር ከሆነ፤ እንዴት በቅድስና እንደምንይዘው የሚያሳይ ደግሞ መንገድ አለው ማለት ነው፡፡
••• ታዲያ ፈጣሪችን የሆነው እግዚአብሔር እንተዳደርበት ዘንድ የሰጠን ማኑዋል መፅሐፍ ቅዱስ ነው እንጂ ስለኛ አፈጣጠር የማይመለከተው አካል አቅጣጫ ሊያሳየን አይችልም፡፡

መቼ?
••• የፍቅር ጓደኝነትን ለመጀመር ትክክለኛ ጊዜውን ማወቅ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የብዙ ሰዎች ጓደኝነት ትዳር ላይ ሳይደርስ ከሚፈርስባቸው ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ያለጊዜው መጀመሩ ነው፡፡ ጓደኝነትን ያለጊዜ በመጀመር ከሚደርሱት ጉዳቶች ውስጥ ደግሞ ዋነኛው የቅድስና ችግር ነው፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ችግሮች ለመዳን የፍቅር ጓደኝነትን ከመጀመራችን በፊት አሁን ትክክለኛ ጊዜው ነውን? ብለን ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል፤ ምን መጠየቅ ብቻ እርግጠኛ የሆነ መልሱንም ማወቅ አለብን!!
••• ጊዜ አለመጠበቅ የሚያመጣውን ጉዳት በሚገባ ያስተዋልን እንደሆነ “ታዲያ እንዴት ነው ጊዜውን ማወቅ የምንችለው?” የሚል ጥያቄ ወደ አእምሮአችን ይመጣል፡፡
••• የዘጠኝ ዓመት ሕፃን ልጅ ፍቅረኛ ልያዝ ወይ ብላ ብትጠይቃችሁ በእርግጠኝነት የምትመልሱላት መልስ አንቺ እኮ ገና ሕፃን ልጅ ነሽ ፍቅረኛ ለመያዝ ትንሽ ማደግ አለብሽ የሚል ነው፡፡ ነገር ግን አንድ የሀያ አምስት አመት ኮረዳ ተመሳሳይ ጥያቄ ብትጠይቃችሁ ህፃን ነሽ እደጊ አትሏትም ወይም ደግሞ እንዴት በሀያ አምስት ዓመትሽ አትሏትም ይልቁንም ልጁ ማነው? ክርስትያን ነው ወይ? ባሕርይው ምን ዓይነት ነው? እና ሌሎችንም ጥያቄዎችን በመጠየቅ ለማጣራት ነው የምንሞክረው፡፡ ከዚህ የምንረዳው የፍቅር ጓደኝነትን መያዝ ወይም አለመያዝ የሚወሰነው በእድገታችን ነው ማለት ነው፡፡
እድገት ምንድን ነው? በእድሜና በአካለመጠን የመግዘፍ ብቻ ወይስ አርቆ የማሰብና የማስተዋል መጠን? ክፍል እየቆጠሩ መመረቅ ብቻ ወይስ በማህበራዊና ስነልቦዊ ዕውቀት መራቀቅ?፣ እድገት ምንድን ነው? ስንት ዓይነት እድገት አለ?
እድገት የሚለካው ሁሉን አቀፍ በሆነ አዎንታዊ የለውጥ መጠን ነው፡፡ አንድ ሰው ሀያ እና ሀያ አንድ አመት ስለሞላው ብቻ አድጓል ማለት አንችልም፡፡ በትምህርት ልቆ ዶክተር ኢንጂነር ቢባል ይህ ብቻውን የእድገቱ ማሳያ ሊሆን አይችልም፡፡
እድገት ዘርፈ ብዙ፣ መጠነ-ሰፊና፣ እና ሁሉን አቀፍ አዎንታዊ የለውጥ መጠን ነው፡፡ የፍቅር ጓደኝነትን ከመጀመራችን በፊት በቅድሚያ ሁለንተናዊ የሆነ እድገታችንን መመርመር መቻል አለብን፡፡ ይህን ስናደርግ ትክክለኛ ጊዜው ይሁን አይሁን መወሰን ቀላል ይሆንልናል፡፡

ወንድማችሁ ናትናኤል ቤኪ_ነኝ

ስተያየት ካለዎት በ @CbekinaT ላይ ያናግሩኝ።
@Biblicalmarriage
◈sʜᴀʀᴇ◈
ይቀላቀሉን
3.7K viewsNatinael Beki, 21:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 21:57:06 https://youtube.com/shorts/lMt595VfehY?feature=share
4.0K views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 15:21:34 እንዲሳካላችሁ ይህን ማድረግ ይጠበቅባችኋል

4.1K views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , edited  12:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 18:03:54 °°°°° የንስር ህይወት °°°°°
ንስር አሞራ እና ......አንቺ .........አንተ .

ንስር አሞራ እስከ 70 አመት የሚኖር የእድሜ ባለፀጋ ነው ካልክ ልክ ነህ ... ግና 70 አመት ሙሉ በደስታ ከመኖሩ በፊት በእድሜው አጋማሽ ማለትም በ35 - 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል ...

የመጀመሪያው :- ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል ...

ሁለተኛው :- አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው አፉ(መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል ...

ሶስተኛው:- ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል።

እነዚህ ሶስት ከባድ ነገሮች ንስር አሞራ በእድሜው አጋማሽ የሚያጋጥሙት ከባድ ችግሮች ናቸው። አሁን ንስር አሞራ ያለው ምርጫ ሁለት ነው።

1ኛ. ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ?

2ኛ. አምስት ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን 35 አመት በደስታ ማሳለፍ ?

የመጀመሪያውን ከመረጠ በእድሜው አጋማሽ ይሞታልና ታሪኩ እዛ ጋር ያበቃል።

ሁለተኛውን ምርጫ ከመረጠ ግን እነዚህን አምስት መስዋዕትነቶች ማለፍ ይኖርበታል።

፩ኛ. ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል።

፪ኛ. ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ ይጥላል።

፫ኛ. ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር ይወጣለታል፡፡ መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል፡፡

፬ኛ. አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል።

፭ኛ. አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል። በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል።

ይህን 5 ወር በዚህ መልኩ በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡



ወዳጄ ሆይ:-

ችግር ገጠመኝ ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ አትበል ፣ ችግሬ ... ችግሬ ... እያልክም ነጠላ ዜማ አትልቀቅ ፣ ፊትህንም ችግር ፊት አታስመስል ፣ ጥቅም ላይ እያፈጠጠ የሚከተል ሰው በበዛበት አለም ላይ መውደቅህን መጥሪያ ካርድ አታሰራበት ፣ መራብ መጠማትህን ፖስት ለማድረግ አትቸኩል ፣ መገፋትህን እንደ ትልቅ ነገር ቆጥረህ ኡኡኡ አትበል ፣ ስንት ነገር መስራት የምትችልበትን አዕምሮ ለሃሜትና "አሉ ... አለች" መሳሪያ በመጠቀም "የውሸት እየኖርክ - የእውነት አትሙት" ...

በቃ! ... ልክ እንደ ንስር አሞራ በህይወትህ አጋማሽ ላይ ምርጫ መቶልሃል ...

፩ኛ. ችግሩን ታቅፎ መሞት ...

፪ኛ. ለችግሩ መስዋትነት ከፍሎ ማለፍ ...

••• አስተውል ... •••

ሁለተኛውን ከመረጥክ ልክ እንደ ንስሩ አምስት ዋጋዎችን መክፈል አለብህና ዝግጁ ሁን ...

፩ኛ. ራስህን ከነገሮች አርቀህ በፅሞና ሃሳብህን መግራት ጀምር ... እዚህ ጋር ከወዳጅም ከጠላትም መራቅ ፍቱን መድሃኒት ነው ... ንስር አሞራው ከፍተኛ ተራራ ላይ የሚወጣው ከሁሉም ንስሮች እርቆ ለህይወቱ ዋጋ ለመክፈል ነው ... ይህን አይነት መላ ምሁራኑ "የስኬት ሱባኤ" ይሉታል።

፪ኛ. አንገብጋቢ ችግርህን ለመፍታት ቁርጥ ያለ አቋም ይዘህ እስከ ሞት የሚያደርስ መስዋትነት መክፈል። ንስሩ አፉ ላይ ያለውን ምግብ ማምጫ መንቁሩን እንደሚያስወግደው ሁሉ።

፫ኛ. መስዋት የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትዕግስት መጠበቅ ... ይህ ደግሞ ንስሩ መንቁሩ እስኪያድግለት ድረስ ምግብ ሳይበላ እንደሚኖረው ሁሉ አንተም ዋጋ የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትእግስት እና እምነት መጠበቅ።

፬ኛ. በትእግስት ጠብቀህ ያሰብከው ነገር ከመጣ በዋላ ህይወትህን ጠፍንገው የያዙህን ነገሮች መፍታት ... ልክ ንስሩ መንቁሩ እንዳደገለት የእግሩን ጥፍሮች በመንቁሩ እየወጋ እንደሚያስወግዳቸው ሁሉ።

፭ኛ. ሁሉን ካሳካህ በዋላ ወደ ህልምህ መብረር ... ይህ ማለት ንስሩ የእግሮቹን ጥፍር አስወግዶ እና አሮጌ ክንፎቹን አስወግዶ ከጠበቀ በዋላ አዲስ ክንፍ ፣ አዲስ መንቁር እና አዲስ ጥፍር ካበቀለ በዋላ እንደ አዲስ ጉልበታም ንስር ቀሪ ዘመኑን ይኖራል።

ሲጠቃለል ...

አንተም ፣ አንቺም ፣ እኔም በዚህ ሁሉ መንገድ አልፈን ከባዱን ጊዜ ካለፍን በዋላ በአዲስ የህይወት መንቁር ፣ የተስፋ ጥፍር እና የስኬት ክንፍ ከፍ ብለን እንበር ዘንድ ..... ኑ ንስር አሞራን እንምሰል።

ናትናኤል ቤኪ @CbekinaT
እባክዎን ለወዳጅዎ ያካፍሉ
@Biblicalmarriage
JOIN ሼር ማድረግ እንዳይረሱ

✦•• @Biblicalmarriage
✦•• @Biblicalmarriage
ƒσɾ αηy ɕσʍʍεηt... @Biblicalmarriage_bot
4.5K views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 14:58:19 ትላንት የተጎዳሽው/ኸው በራስህ ጥፋት ነው

አዎ! ትላንት ፍቅረኛዬን ከሚከፋት/ፋው እሱ/ሷ ብቻ ደስ ይበላት/ለው እንጂ ለእኔ ችግር የለውም ብለህ/ሽ ለራስህ/ሽ ክብር ሳይኖርህ/ሽ ፍቅረኛህ/ሽ እንደ ፍላጎት/ቱ ሆነህላት/ ሆነሽለት ዛሬ ስትርቅህ/ ሲርቅሽ "እሷ/ሱ ጎዳችኝ/ ጎዳኝ" ለማለትህ/ለማለትሽ ተጠያቂው/ቂዋ አንተ/ቺ ራስህ/ሽ ነህ/ሽ።


ከፍቅረኛ ጋር እስከ መጨረሻው ለመዝለቅ አስፈላጊው ነገር በቅድሚያ ለራስ ክብር መስጠትና ራስን መውደድ ነው።


@Biblicalmarriage
3.9K views11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 15:38:13 ጥያቄ፦ ባሌ ከመጋባታችን በፊት በተለያዩ የፍቅር ቃላት ፍቅሩን ይገልፅልኝ ነበር። አሁን ግን ቃላቱም የሉም።ጭራሽ ሲያወራኝ እንኳን የስራ ጉዳይ ብቻ ነው የሚያወራኝ። እየሳቀ ካወራኝም አመታት አልፈዋል። እኔ ሳቁን የፍቅር ቃላቱን እፈልገዋለሁ። ያንን ግን አሳጣኝ። ሌሎች ጓደኞቼ ሲያወሩኝ በፍቅር ስለሆነ ደስ ይለኛል። እሱ ባሌ ሆኖ ፍቅሩን ካልገለፀልኝ ሌሎች ግን ፍቅራቸውን ከገለፁልኝ እሱ ምን ያደርግልኛል? ብፈታው ደግሞ ኃጢአት ነው። ግን ለእሱ ያለኝ ፍቅር ጠፍቷል። ምን ትመክሩኛላችሁ??

እህታችን በቅድሚያ ስለጥያቄሽ አመሰግናለሁ።

እንደሚታወቀው ትዳር መግቢያ እንጂ መውጫ የሌለው እስከሞት የሚቀጥል በእግዚአብሔር የተመሰረተ ተቋም ነው። በዚህ ተቋም ውስጥ ሁለት ሃላፊነት ያላቸው ሰዎች ሃላፊነታቸውን በተገቢው መልኩ መወጣት ይኖርባቸዋል። የባልዬው ሃላፊነት ሚስቱን ከልቡ መውደድ ሲሆን ሚስትዬዋ ደግሞ ባሏ ራሷ እንደሆና በማመን መገዛት ነው። ባለትዳሮች እነዚህን ሃላፊነቶች በአግባቡ መወጣት ሳይችሉ ሲቀር ትዳራቸው አስጊ ሁኔታ ላይ ይወድቃል።

በባል የመውደድ ሃላፊነት ውስጥ ሚስቱን የመንከባከብ፣ ደስታዋንና ስኬቷን የመፈለግ፣በተቻለ መጠን እንዳታዝን የማድረግ ነገሮች አሉ። እነዚህን ከተወጣ ከሚስቱ በኩል የሚፈልገውን ማግኘት ይችላል።

@AbrishEl @Biblicalmarriage

እህታችን! የአንቺ ቅራኔና ጥያቄ ባሌ የፍቅር ቃላትን አይገልፅልኝም የሚል እንድምታ ያለው ነው። ፍቅር በቃላት ሊገለፅ ይገባል። እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ የሚሉ ቃላትን ለትዳር አጋር መጠቀም ያውም ለሚስት እነዚህን ቃላት መጠቀም በልቧ ውስጥ ደስታን ይፈጥራል። አንቺም እንደነገርሽን ከመጋባታችሁ በፊት እነዛን ቃላት ይጠቀም እንደነበር አሁን ግን እንደሌለ ነው። ይህም ስጋትና ወደ ሌላ አካል መሳብን ፈጥሮብሻል!

ሦስት ነገር ማድረግ አለብሽ!

1. ትዳርሽን በጌታ ፊት ይዘሽ መቅረብ
2. በትዳር ውስጥ የሚስት ሃላፊነት የሆነውን ሃላፊነትሽን መወጣት
3. ከትዳር አጋርሽ ውጭ የፍቅር ቃላትን አለመጠቀም!
=======================
@Biblicalmarriage

1. ትዳርሽን በጌታ ፊት ይዘሽ መቅረብ

ትዳር መንፈሳዊ ተቋም እንደመሆኑ መጠን ብዙ ፈተና ይገጥመዋል። እነዚህ ፈተናዎች ደግሞ ትዳሩ እንዲፈርስ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ። ስለዚህ በትዳርሽ ጉዳይ የተቋመ ባለቤት ከሆነው እግዚአብሔር ጋር መነጋገርና ትዳርሽን ለጌታ አሳልፎ መስጠት ተገቢ ነው። በተጨማሪም የትዳር አጋርሽ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ እያለፈ ሊሆን ስለሚችል ማለትም ልቡን ከአንቺ እንዲያርቅ በተለያየ ሁኔታ ጠላት የጥፋት መንገድ ውስጥ ሊያስገባው ስለሚችል ለባልሽ በጌታ ፊት ልትሆኚ ይገባል።

@Biblicalmarriage

2. በትዳር ውስጥ የሚስት ሃላፊነት የሆነውን ሃላፊነትሽን መወጣት

እህቴ የአንቺ ሃላፊነት ምንድነው?? በነገርሽ ላይ ትዳርሽ ጣፋጭ እንዲሆንና ከስጋት ለመታደግ ከአንቺ በኩል የሚጠበቅብሽን ሃላፊነት መወጣት መፅሃፍ ቅዱሳዊ ነው። ባልሽን ማክበር፣ ከስራ ሲመለስ በፈገግታ መቀበል፣ ችግሩን መጋራት፣ ስሜቱን መረዳት፣ ...ወዘተ

@Biblicalmarriage

3. . ከትዳር አጋርሽ ውጭ የፍቅር ቃላትን አለመጠቀም

ባልሽ በፍቅር ቃላት ፍቅሩን እንዲገልፅልሽ ትፈልጊያለሽ። ያንን ማድረግ አልቻለም። ስለዚህ አንቺ ሌሎች እነዛ ከባልሽ ፈልገሽ ያላገኘሻቸውን የፍቅር ቃላት በመጠቀም ስላወሩሽ ልብሽ ተወስዶብሻል። ይሄ ደግሞ አደገኛ ነው። ምናልባት ያ ከባልሽ ውጭ የፍቅር ቃል ተጠቅሞ የሚያወራሽ ሰው ቢያገባሽ እሱስ እንዳሁኑ ባልሽ ዝም የሚል ከሆነ? አየሽ ያንን ጉዞሽን አቁመሽ ከባልሽ ጋር በግልፅ ተወያይታችሁ ባልሽ ቃላቱን እንዲጠቀም ማድረግ ይሻላል እንጂ ከሌላ ወንድ ጋር ግንኙነት መጀመር ፍፃሜው ውድቀት ነው።

ሥለዚህ፦

ከባልሽ ጋር በግልፅ ተወያዩ
ታገሺው
አንቺ ለባልሽ የሚገባውን አድርጊለትባልሽም ለአንቺ የሚገባሽን ያድርግልሽ። ያን ጊዜ ሁለታችሁም ውጭ ውጭውን አታዩም።



“ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፥ እንደዚሁም ደግሞ ሚስቲቱ ለባልዋ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 7፥3


@Biblicalmarriage
5.4K views12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ