Get Mystery Box with random crypto!

በተለያዩ አጥቢያዎች፣ የወጣቶች ህብረትና የተማሪ ህብረቶች(ኮሌጅና ዩኒቨርስቲዎች) ባገለገልንባቸው | Marriage Tube

በተለያዩ አጥቢያዎች፣ የወጣቶች ህብረትና የተማሪ ህብረቶች(ኮሌጅና ዩኒቨርስቲዎች) ባገለገልንባቸው ጊዜያት ካስተዋልናቸው ነገሮች ውስጥ የተበላሸ የተቃራኒ ፃታ ግንኙነት፣ ቅድስና የጎደለው እጮኝነት፣ ችላ የተባለ ወጣትነት፣ በትዳር ውስጥ ያሉ ከባድና ውስብስብ ጉዳዮች፣ የፖርኖግራፊ ችግር...ወዘተ አስተውለናል።

በዚህ ሁሉ ግን ቤተ ክርስቲያን ምን ያክል ዝም እንዳለችና ብዙዎች ደጋፊና መካሪ እንዲሁም አቅጣጫ ጠቋሚ ያጡ ወጣቶች መብዛታቸው ብሎም በጭንቅ ውስጥ ያለ ጋብቻ እንዳለ ግልፅ ነው።

ወጣቶች የንፅህና ጉድለት ተገኝቶባቸው ከአጥቢያና ከህብረት ከማገድ በፊት እንዲሁም ባለትዳሮች ትዳራቸው በፍቺ ከመቋጨቱ በፊት ቤተ ክርስቲያን ትኩረት ሰጥታ ስልጠዎችንና የፀሌት ጊዜዎችን ልታዘጋጅ ይገባል!

ልንረዳችሁ የምትፈልጉ ወገኖች ስልካችን ክፍት ነው።

ተባረኩ!


@Biblicalmarriage