Get Mystery Box with random crypto!

Marriage Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ biblicalmarriage — Marriage Tube M
የቴሌግራም ቻናል አርማ biblicalmarriage — Marriage Tube
የሰርጥ አድራሻ: @biblicalmarriage
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.09K
የሰርጥ መግለጫ

ኢሳ 53:10
በቻናላችን
👉 🌷ጋብቻ ምንድነው?🌷
👉 ❤️ማንን ላግባ?❤️
👉 😳ፖርኖግራፊና መዘዙ😳
🚩 የፍቅር ታሪኮች
💝 የርቀት ፍቅር
አጋር ቻናል:- @Nazrawi_tube
ለአስተያየት
👉 @Biblicalmarriage_bot
0910337074
🔵ቅድስና ለእግዚአብሔር🔵

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-01-03 12:26:38
አንድም ፍጹም ጻድቅ በማይገኝበትና የስነ ሥርዓት ደረጃን በደንብ ባላየች በዚች ዓለም ውስጥ ስንመላለስ፣ ዋጋ የተከፈለበት የእግዚአብሔር ጸጋ አኗኗራችንን ካልዳኑት ሰዎች በተለየ እንድናደርግ ያደርገናል፡፡ የእግዚአብሔርን ጸጋ ተቀብሎ የጽድቅን ሕይወት ከመምራት የሚሸሽ የልቡን ክፋትና ደንዳናነት፣ ከእወቀት መጉደሉንም ያሳያል፡፡ በእኛ ዘመን መዳን ማለት የጽድቅን መንገድ መከተል ነው፡፡ የጽድቅን መንገድ የምንከተለው ደግሞ ለመዳን ሳይሆን፣ የእግዚአብሔር የማዳን ጸጋ በእኛ ውስጥ የሚያመጣው ፍሬ በመሆኑ ነው፡፡
መልካም ቀን ይሁንላችሁ
@Biblicalmarriage
585 viewsNatinael Beki, 09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 13:55:32 ለዚህ ሰው ያላችሁን ምክር በ @Biblicalmarriage_bot በኩል ላኩልን
608 views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 13:50:29 ሰላም እንደምን ኣለክ? ጥያቄዩ እኔ አሁን እድሜዩ 26 ነው ከዛሬ 10 አመት በፊት አንድ መጥፎ ልምድ ተጠናውቶኝ እስካሁን ድረስ ልተወው አልቻልኩም። መጀመሪያ የወሲብ ፊልም መየት ከዛም እራስን በራስ ማርካት ። እንደዚህም እያደረኩ ቸርች እሄድ ነበር አንዳንድ አገልግሎትም አገለግል ነበር ከዛሬ 7" ዓመት በፊት ግን የህሊና ወቀሳውን ስላልቻልኩት ቸርችም መሄድ አቆምኩ ። ከዛም በሃላ ይበልጡኑ ተዘፈቁበት ።አልፎ አልፎ በቃ ከዚህ ነገር መውጣት አለብኝ በቃኝ ብዬ ባቆምም 15 ቀን ወይም ወር ድረስ ብቆይ ነው ተመልሼ እገባበታለሁ ።ከአቅሜ በላይ ሆኖብኛል እና እባክህ የምትመክረኝ ወይም የምታሳየኝ መንገድ ካለ አግዘኝ እላለሁ ።አመሰግናለሁ
627 views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 09:59:53
እኛ የዚህ ምድር ፍጡራን ብንሆንም ከዚህም የላቀ ማንነት ያለን ፍጡራን ነን፡፡ ይህን እውነታ ዘወትር ማስታወስ ያስፈልጋል! እንደዚያም ሆኖ ግን ጊዜ ከመፈጠሩ በፊት ስላለው ነገር ምንም የምናውቀው የለንም፡፡ እግዚአብሔር ግን ከጊዜም በፊት ነበር፡፡ ራሱንም “እኔ ነኝ” እያለ ገልጾአል፡፡ የነበረው፣ ያለውና ወደፊትም የሚኖረው እርሱ ነው፡፡ አጽናፈ ዓለሙ ወደ ህልውና ከመምጣቱ በፊትም፣ ለእኛ ህልውና መሠረት በመሆን እርሱ ነበር፡፡ እግዚአብሔር “እኔ ነኝ” ይላል፡፡ ቀድሞም የነበረ፣ በኋላም የእኛ አጽናፈ ዓለም ከመፈጠሩ በፊትም እርሱ እግዚአብሔር በሥፍራው ነበር፡፡ የእርሱን ዘለዓለማዊ ሐሳብ በቃላት መግለጽ የሚቻል አይደለም፡፡ ለዚህም ነው እያንዳንዱ አዲስ ጅማሬ፣ ቀንም ቢሆን ሳምንትም፣ ዓመት ወይም ምዕተ ዓመት ጅማሬው በእግዚአብሔር የሆነው፡፡ እርሱ ብቻውን ፍጹም የሆነ ፈጣሪና የእኛም ጅማሬ ነው፡፡ @Biblicalmarriage
Happy New Year
102 viewsNatinael Beki, 06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 11:47:27 መልሱን መላክ የምትችሉት
በ @Biblicalmarriage_bot ብቻ ነው
670 views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 11:45:22 ድጋሚ መመለስ አይቻልም!
673 views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 11:41:59 #የሚያሸልም_ጥያቄ

ቀድመው ለመለሱ 5 ሰዎች የ130 ደቂቃ የስልክ የድምፅ  Package !

ጥይቄ
1. የ2018 የአለም ዋንጫ ያሸነፈች ሃገር ማናት?

2. ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የሚለው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል መለውን(የመፅሃፉን ስም ምህራፍና ቁጥር) ይጥቀሱ

ከላይ ያሉትን ሁለት ጥያቄዎች በመመለስ የ130 ደቂቃ አሸናፊ ይሁኑ!

መልስዎትን
በ @Biblicalmarriage_bot ወይም በ @Abrishel በኩል ያድርሱን


@Biblicalmarriage
689 views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 11:35:14 #የሽልማት_ፕሮግራም


ሰላም ለእናንተ ይሁን የቻናላችን ተከታታዮች ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኋላ በዚህ ቻናላችን የተመለስን መሆኑን ስናበስር በደስታ ነው። በዚህ ቻናል በከል በሚተላለፉ መልዕክቶች ብዙ ሰዎች እንደተጠቀማችሁ በአስተያየት መስጫ ቦታችን (@Biblicalmarriage_bot) በኩል በላካችሁልን አስተያየት ተረድተናል።

ዛሬም እንደቀድሞ አስተማሪ ሃሳቦችን በዚሁ ቻናልልችን እናነሳለን።

አስተያየት ለመስጠትና ጥያቄ ለመጠየቅ

@Biblicalmarriage_bot
573 views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 07:47:44
እያንዳንዱ ሰው የገነባው ምድራዊ መንግሥት ፈራሽ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ያቋቋመው መዋቅርም በስባሽና ወዳቂ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሰጠን መንግሥቱ ግን የማትዝግ፣ የማትጠፋ ወይም የማትወስ መንግሥት ለእኛ አቆይቶልናል፡፡ ይህቺ መንግሥቱ የማትበሰብስና የማትጠፋ ዘራፊ ሌቦች ሰብረው ገብተው የማይሰርቁባት ናት፡፡
@Natinaelbeki
@Bibilicalmarriage
Have a wonderful time
754 viewsNatinael Beki, edited  04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-17 21:22:03 ፀጋና ሰላም በያላችሁበት ለያንዳንዳችሁ ይብዛ። ውድ የቻነላችን ተከታታዮች፣ ዛሬም እንደተለመደው ለንባብ ይሆነን ዘንድ ከህይወት ከተማርኩት ላይ ትንሿን እነሆ ብያለሁ።

ፍቅር የምትቀበለው ብቻ ሳይሆን የምትሰጠውም ጭምር ነው!

በናትናኤል ቤኪ

ፍቅር ማለት የራስን ፍላጎት መጠበቅና መውደድ ሳይሆን ለሌላው መኖር ነው::

ሰው ኣፈቀርኩ ብሎ የሚያምነው እራሱ ብቻ የሚፈለገውን ነገር ማግኘት ሲችል ብቻ ነው::

ሰዎች ለፍቅር የሚያስቀምጡት መስፈርት ብዙ ነው ውበት ደም ግባት ቁመት ሃብትና ዝና እውቀት ወዘተ................ነገር ግን

እውነተኛ ፍቅር ማለት በሌላ ሰው ውስጥ ያለን ፍላጎትና ሃሳብ ማንነትን ጭምር በሙሉ ልብ መቀበል መቻል ነው:: ኣብዛኛውን ወንዶችና ሴቶች ኣፈቀርን ሲሉ ይሰማሉ ኣፈቀርን ካሉት ነገር ውስጥ ግን ኣንዱም እውነት ላይሆን ይችላል:: ለምሳሌ ኣንድ ወንድ እረጅም ጸጉርና ቁመና ያላት ሴት የፍቅር ምርጫው ልትሆን ትችል ይሆናል:: ሴቷም እንዲሁ እንደዚህ ኣይነት የፍቅር መስፈርት ያላቸው ሰዎች የሚያፈቅሩት ፍላጎታቸውን እንጂ ወደድን የሚሉትን ሰው ኣይደለም:: በ1ጴጥ1:24 ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል ይላል እንደዚህ ኣይነት ሰዎች የወደዱት ውበት በእድሜና በህመም ይሁን በኣደጋ ቢለወጥና የወደዱት ነገር ቢጠፋ የነሱም ፍቅር ኣብሮ ይጠፋል:: ሰው በእድሜ በህመም በኣደጋ ውበቱን ሊያጣ ይችላል::ውበት ለሰው የሚያስደስት ነገር እንኳን ቢሆን የሰው ትክክለኛ ፍላጎትና ምርጫ በሰው ስብእና ላይ ያተኮረ መሆነ ኣለበት የሚል እምነት ኣለኝ::የእግዚኣብሄር ቃል በምሳ31፥30 ውበት ሐሰት ነው ደም ግባትም ከንቱ ነው እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች።ይላል በዚህ ቃል ላይ ከውበትና ከደም ግባት በላይ ትኩረት የተሰጠው እግዚኣብሄርን መፍራቷ ብቻ ነው::

የዚህ ቃል እውነት ሴቶችን ብቻ ሳይሆን ወንዶችንም የሚያጋራ ትልቅ ምክር ነው:: ጳውሎስ ስለ ባሎች ለኤፌሶን በጻፈው መልእክቱ ላይ ባሎች ሆይ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ ኣለ እንጂ ውበታቸውን ውደዱ ኣላለም :: እውነተኛ ፍቅር ከውበት ያለፈና ውበት ቢኖርም ባይኖርም ኣብሮ የሚኖር ልባዊ ቁርኝት ነው::የምትፈልገውን ለማግኘት ሳይሆን ሰው ካንተ የሚፈልገውንም ለመስጠት በሰውነቱና በማንነቱ ለመቀበልና ለመውደድ ውደድ::ፍቅር የምትቀበለው ብቻ ሳይሆን የምትሰጠውም ጭምር ነው!

ፍቅር ማለት የራስን ፍላጎት መጠበቅና መውደድ ሳይሆን ለሌላው መኖር ነው::

ሰው ኣፈቀርኩ ብሎ የሚያምነው እራሱ ብቻ የሚፈለገውን ነገር ማግኘት ሲችል ብቻ ነው::

ሰዎች ለፍቅር የሚያስቀምጡት መስፈርት ብዙ ነው ውበት ደም ግባት ቁመት ሃብትና ዝና እውቀት ወዘተ................ነገር ግን

እውነተኛ ፍቅር ማለት በሌላ ሰው ውስጥ ያለን ፍላጎትና ሃሳብ ማንነትን ጭምር በሙሉ ልብ መቀበል መቻል ነው:: ኣብዛኛውን ወንዶችና ሴቶች ኣፈቀርን ሲሉ ይሰማሉ ኣፈቀርን ካሉት ነገር ውስጥ ግን ኣንዱም እውነት ላይሆን ይችላል:: ለምሳሌ ኣንድ ወንድ እረጅም ጸጉርና ቁመና ያላት ሴት የፍቅር ምርጫው ልትሆን ትችል ይሆናል:: ሴቷም እንዲሁ እንደዚህ ኣይነት የፍቅር መስፈርት ያላቸው ሰዎች የሚያፈቅሩት ፍላጎታቸውን እንጂ ወደድን የሚሉትን ሰው ኣይደለም:: በ1ጴጥ1:24 ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል ይላል እንደዚህ ኣይነት ሰዎች የወደዱት ውበት በእድሜና በህመም ይሁን በኣደጋ ቢለወጥና የወደዱት ነገር ቢጠፋ የነሱም ፍቅር ኣብሮ ይጠፋል:: ሰው በእድሜ በህመም በኣደጋ ውበቱን ሊያጣ ይችላል::ውበት ለሰው የሚያስደስት ነገር እንኳን ቢሆን የሰው ትክክለኛ ፍላጎትና ምርጫ በሰው ስብእና ላይ ያተኮረ መሆነ ኣለበት የሚል እምነት ኣለኝ::የእግዚኣብሄር ቃል በምሳ31፥30 ውበት ሐሰት ነው ደም ግባትም ከንቱ ነው እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች።ይላል በዚህ ቃል ላይ ከውበትና ከደም ግባት በላይ ትኩረት የተሰጠው እግዚኣብሄርን መፍራቷ ብቻ ነው::

የዚህ ቃል እውነት ሴቶችን ብቻ ሳይሆን ወንዶችንም የሚያጋራ ትልቅ ምክር ነው:: ጳውሎስ ስለ ባሎች ለኤፌሶን በጻፈው መልእክቱ ላይ ባሎች ሆይ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ ኣለ እንጂ ውበታቸውን ውደዱ ኣላለም :: እውነተኛ ፍቅር ከውበት ያለፈና ውበት ቢኖርም ባይኖርም ኣብሮ የሚኖር ልባዊ ቁርኝት ነው::የምትፈልገውን ለማግኘት ሳይሆን ሰው ካንተ የሚፈልገውንም ለመስጠት በሰውነቱና በማንነቱ ለመቀበልና ለመውደድ ውደድ::
ሳብ አስተያይት ካለዎት በዚህ ልንክ አማካኝነት ልያገኙን ይችላሉ።
@Natinaelbeki
@Bilblicalmarriage
376 viewsNatinael Beki, 18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ