Get Mystery Box with random crypto!

Marriage Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ biblicalmarriage — Marriage Tube M
የቴሌግራም ቻናል አርማ biblicalmarriage — Marriage Tube
የሰርጥ አድራሻ: @biblicalmarriage
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.09K
የሰርጥ መግለጫ

ኢሳ 53:10
በቻናላችን
👉 🌷ጋብቻ ምንድነው?🌷
👉 ❤️ማንን ላግባ?❤️
👉 😳ፖርኖግራፊና መዘዙ😳
🚩 የፍቅር ታሪኮች
💝 የርቀት ፍቅር
አጋር ቻናል:- @Nazrawi_tube
ለአስተያየት
👉 @Biblicalmarriage_bot
0910337074
🔵ቅድስና ለእግዚአብሔር🔵

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-08-14 18:03:09
ከላይ የምትመለከቱት ፎቶ የተነሳው በ1994(እ.አ.አ) በሱዳን ሀገር ሲሆን ፎቶውን ያነሳው ኬቪን ካርተር የተባለ ደቡብ አፍሪካዊ የፎቶ ባለሙያና ጋዜጠኛ ነው። በፎቶው ላይ ያለችው ህፃን ሴት ስትሆን ቤተሰቦቿ ምግብ ለማምጣት ወደ UN ካምፕ ሲሄዱ በረሃብ ምክንያት መራመድ አቅቷት መሬት ላይ ስትንፏቀቅ ጥንብ አንሳ አሞራው ከኋላዋ መጥቶ ሞቷን ይጠባበቅ ነበር። ይህም ማለት እንደሞተች ሊበላት ማለት ነው። በዚህ ጊዜ ነበር ፎቶ አንሺው አሞራው በሮ እንዳይሄድበት ጥሩ ፎቶ ለማንሳት የሚመቸውን ቦታ በመያዝ ፎቶ ያነሳት።

ይህ ፎቶ በኒውዮርክ ታምስ ላይ መነጋገሪያ እስኪሆንና የአለምን ህዝብ ያሳዘነና መነጋገሪያ ርዕስ የፈጠረ ነበር። ለጋዜጠኛው በተደጋጋሚ ይቀርብለት የነበረው ጥያቄ "ልጅቷ መጨረሻዋ ምን ሆነ ዳነች ወይ ወይስ ሞታ አሞራው በላት ወይ?" የሚል ነበር።

ጋዜጠኛው የዚህችን ህፃን መጨረሻ እንዳላየ ማስረዳት ችሏል።

በስተመጨረሻ ግን ኬቪን ካርተር ከሙያዬ ይልቅ ለዚህች ልጅ ብደርስላት መልካም ነበር ይህች ልጅ በእጄ የሞተች ያክል ይሰማኛል" በሚል ጭንቀት ስለተሰቃየ #እራሱን_ሊያጠፋ ችሏል።


ከምንም በላይ ሰብአዊነት ይቀድማል!

አብርሃም ነኝ
2.9K views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 09:05:02
በትዳር ውስጥ በባልና በሚስት መካከል ችግር ሊፈጥር የሚችለው የትኛው ነው?
Anonymous Quiz
5%
ሀ. የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት
3%
ለ. የንግግር ክህሎት ማነስ
2%
ሐ. የግብረስጋ ግንኙነት
4%
መ. ከትዳር አጋር ይልቅ ለሌላ ሰው ቅድሚያ መስጠት
86%
ሠ. ሁሉም
677 voters2.7K views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 09:02:22
በትዳር ውስጥ የባል ሃላፊነት የሆነው የትኛው ነው??
Anonymous Quiz
2%
ሀ. ሚስቱን መንከባከብ
6%
ለ. ሚስቱን መውደድ
1%
ሐ. ለቤቱ የሚያስፈልገውን ማሟላት
91%
መ. ሁሉም
632 voters2.6K views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 06:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 12:35:49 የልብስና የአለባበስ ነገር
================

#ልብስ ለሌላው ሰው መታየት የሌለባቸው የሰውነት ክፍሎቻችንን ለመሸፈን እንዲሁም በልብሱ ዲዛይን ምክንያት የሚገኘውን ውበት ለመላበስ የሚለበስ ነው። ሌሎችም ብዙ ጥቅሞች ሊኖሩት እንደሚችሉ እሙን ነው። ሰዎች እንደየ አቅማቸው ያምርብኛል የሚሉትን ልብስ ገዝተው ወይም አሰርተው ይለብሳሉ! ሴቶችም ወንዶችም።

#አለባበስ ጋ ስንመጣ ብዙ ጊዜ አለባበሳቸው የሚመለከታቸውን ሰው ወደሌላ ነገር(ምኞት) ይመራል በሚል እህቶች ላይ ቅሬታ ሲቀርብ ይስተዋላል! አንዳንድ እህቶችም "እህቴ እንዲህ ባትለብሺ ጥሩ ነው"የሚል ምክር ሲሰጣቸው ከመቀበል ይልቅ " ስለእከሌ ምን አገባኝ ደግሞስ ማን እየኝ አለው!" የሚል ከመፅሃፍ ቅዱስ እይታ ውጭ የሆነ መልስ ሲመልሱ ይስተዋላል።

#እህቴ የፈለግሽውን ልብ መልበስሽ መብትሽ ነው ነገር ግን ያ የለበስሽው ልብስ የሚያይሽን ሰው በውስጡ ስጋዊ ምኞት የሚፈጥርበት ከሆነ አንቺም ይህም ወንድም በጥፋት ውስጥ ትሆናላችሁ። ስለዚህ ነው የምትለብሺው ልብስ ውበትሽን ከመጠበቅና ሰውነትሽን ከመሸፈን አልፎ በተመልካች ልብ ውስጥ ኃጢአት እንዲወለድ የሚያደርግ ምኞት እንዲፀነስ እንዳያደርግ ነው አለባበስሽን ማስተካከል ያለብሽ

አንዳንድ እህቶች ጡታቸውን፣እምብርታቸውን፣ታፋቸውን፣ዳሌያቸውን የሚያሳይ ልብስ ይለብሳሉ። ብዙ ወንዶችንም ይስባሉ! እህቴ እርግጠኛ መሆን ያለብሽ ነገር ጡትሽን አይቶ የመጣ ወንድ አንቺን ፈልጎ ሳይሆን ጡትሽን ነው። #አንቺ_ደግሞ_ጡትሽ_አይደለሽም
አንዳንድ የሰውነታችን ክፍሎች በልብስ እንዲሸፈኑ የተደረጉት በቀላሉ እንዳይገኙና የፈለጋቸው አካል ዋጋ መክፈል እንዳለበት ለማሳወቅም ጭምር ነው። ገላለጥሽው ማለት ግን ዋጋውንና ዋጋሽን አሳጣሽው ማለት ነው።

#ወንድሞች

የአለባበስ ጉዳይ ብዙ ጊዜ እህቶች የሚወቀሱበት ነገር ቢሆንም አንዳንድ ወንድሞችም ስሜት ቀስቃሽና ፍኞት ፈጣሪ ልብስ ሲለብሱ ይስተዋላሉ!
ለምሳሌ:-
ከእህቶች ጋር ሲሆን የደረት ቁልፍ በመክፈት ደረትን ማሳየት(ጡትን ከፍቶ እንደማሳየት ይቆጠራል)
የብልትን ቅርፅ የሚያሳይ ሱሪ መልበስ ሴት ልጅ በጣም ስስ ታይት እንዳደረገች ያክል ነው።

በነገራችን ላይ እህቶችም ወንድሞችም አንድን ልብስ ስትለብሱ ያምርብኛል፣ሌሎች ወደኔ እንዲሳቡ ያደርጋል በሚል እይታ ስለሆነ ማማሩ የሚደገፍ ቢሆንም ልብሳችሁን አይቶ የመጣው ሰው በስሱ ወይም በግላጭ የሆነ ውድ ነገር ስላሳያችሁት እንጂ እናንተነታችሁን ፈልጎ ላይሆን ይችላል! ስለዚህ ውድ የሆነ ማንነታችሁን በተገላለጠ ልብስ አታሳንሱት!

ምርጥ አለባበስ ማለት ለራስ ውበት እያሰቡ ለሌላውም እያሰቡ ሲሆን ነው።
ክርስትና ለጌታም ለሰዎችም መኖር ነው! ክርስትና እንደፈለኩኝ ብሆን ሌላ ሰው ምን አገባው የሚባልበት አይደለም!

ክርስቲያን ነሽ/ህ አዎ ከሆነ መልሱ በአለባበስሽ/ህ ጌታን አክብር/ር ለሰዎች ፈተና አትሁኚ/ን።

ክርስቲያናዊ አለባበስ ምን አይነት ነው
3.8K views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 21:50:52
#URGENT

የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን "መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጋብቻ" የሚለው የፌስቡክ ገፃችን በመጠለፉ ምክንያት ከቁጥጥራችን ውጭ በመሆኑ እስክናስተካክል ድረስ በዚህ ገፅ የሚለጠፍ ማንኛውም ነገር እኛን እንደማይወክል ለማሳወቅ እንወዳለን!

እውቀቱ ያላችሁ ደግሞ እንዴት መመለስ እንደምንችል ብትረዱን ደስ ይለናል!

እናመሰግናለን
3.9K views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 11:33:49 #መንፈስ_የሆነው_ቃል!

… ከአፌ የሚወጣ ቃሌ … የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም (ኢሳ 55፡10-11)።

የእግዚአብሔር ቃል እጅግ ብዙ ሥራን ይሠራል፡፡ የጌታ መንፈስ በነቢዩ ኢሳይያስ ከእኔ የሚወጣው ቃል፣ መንፈስ የሆነው ቃል፣ ወይም የጊዜው ቃል፣ የምሻውን ያደርጋል፣ የላክሁትን ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም (ኢሳይያስ 55፡10-11) ብሎ ተናግሯል፡፡

እውነት ነው መንፈስ የሆነው ቃል ከእግዚአብሔር አፍ ይውጣ እንጂ በከንቱ አይወድቅም፡፡ የዕብራውያን ጸሐፊ የእግዚአብሔርን ቃል ሲገልጸው የሚሠራ እና ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅ የተሳለ እና ወደ ጠለቀው ማንነታችን ዘልቆ ልባችንን እንደሚመረምር እና በእርሱ ፊት ሁሉ ነገር የተገለጠ እና የተራቆተ (ዕብራውያን 4፡12-16) እንደ ሆነ ይናገራል፡፡

አዎ ትክክል! የእግዚአብሔር ቃል የሚሠራ ነው፣ ነፍስን ይመልሳል፣ ሰላምንና ደስታን ይሰጣል፣ ከብዙ ጥፋት ያወጣል ያድናልም፣ መንገድንም ያቀናል፡፡ በግሌ የቃሉን ኃይል በሕይወቴ አይቼዋለሁ፡፡ መንፈስ የሆነው ቃል ከብዙ ጉድ ሊያወጣን እንደሚችል በድፍረት መናገር እችላለሁ፡፡ በተግባር ደረጃ ይህ የሕይወት ቃል ወደ ውስጤ በመግባቱ ከመጠጥ፣ ከጫት፣ ከሲጋራ ሱስ እና ብልሹ ከሆነ ማኅበራዊ ሕይወት መንጭቆ አውጥቶኛል፡፡

እጅግ በጣም ይገርማል፡፡ እላዬ የነበረው የሱስ ቀንበር ቀላል አልነበረም፡፡ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ ይህ ኃይል ያለው ቃል ነፃ አድርጐኝ፣ ተለቅቄ ያለ ምንም ባርነት እየኖርኩ እገኛለሁ፡፡ ወደ እሱ ከመጣሁ በኋላም ተነግሮ የማያልቅ ሥራን በሕይወቴ እየሠራ ይገኛል፡፡

ይህ የሚሠራ ቃል የጠላትን ተግዳሮት እንድናሸንፍ ያደርገናል፤ መጽሐፉ እንዲህ ይላልና፡-“ኃያል ሆይ፣ ፍላጻዎችህ የተሳሉ ናቸው፤ እነርሱም በንጉሥ ጠላቶች ልብ ውስጥ ይገባሉ፤ አሕዛብም በበታችህ ይወድቃሉ።” (መዝሙር 45፡5) ይህ ምንባብ የሚናገረው እንደ ተሳለ ፍላጻ፣ በመንፈስ የሚነገር ቃል የሚያመጣውን ውጤት ነው፡፡

አዎ! በሕይወታችን መንፈስ የሆነው ቃል ማንኛውንም ተግዳሮት ጥሶ የመግባትና ነገሮችን የመለወጥ ችሎታ አለው፡፡

ነገር ግን እዚህ ጋ ሊታሰብ የሚገባው ጉዳይ፣ ወደ ውስጣችን በተለያየ መንገድ የሚገባው ቃል እንዴት ይሳላል የሚለው ነው፡፡ በጆሮአችን የምንሰማቸውና በዓይናችን የምናነባቸው የእግዚአብሔር መዛግብቶች፣ ወደ ልባችን የሚያልፉት በአእምሮአችን በኩል ነው፡፡

ለቃሉ ያልተከፋፈለ ልብን በመስጠት ስናጠናውና ስናሰላስለው፣ ብሎም በተግባር ደረጃ ስንለማመደው፣ በልባችን ጽላት ላይ በማይረሳ መልኩ ይጻፋል፤ ከሕይወታችን ጋር በሚገባ ይዋሃዳልም፡፡

ታዲያ ቃሉ በውስጣችን በእምነት ሲዋሃድ ተሳለ ማለት ይቻላል፡፡ ይህ የተሳለ ቃል ነው አሸናፊና ባለ ድል የሚያደርገን! ስለዚህ ለቃሉ ያልተከፋፈለ ልብን እንስጥ !
4.4K views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 22:08:27 ​​​​​​​​​​​​​​​​​─​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─━━─━━ ⊱✿⊰ ━━━━━━──


➲ ፍቅር ዕውር ነው



አንድ ሰው ቆንጆ ልጃገረድ አገባ፡፡እሱም በጣም ይወዳት ነበር፡፡አንድ ቀን የቆዳ በሽታ ያዛት፡፡ቀስ እያለች ውበቷን ማጣት ጀመረች፡፡በቀን በአንደኛው ባልዋ ለጉብኝት ራቅ ወደላ ስፍራ ሄደ፡፡በሚመለስበት ጊዜ አደጋ አጋጠመውና እና ዓይኑን አጣ፡፡ሆኖም የጋብቻ ህይወታቸው እንደተለመደው ቀጠለ፡፡ግን ቀናት እያለፉ ውበቷን ደረጃ በደረጃ አጣች፡፡

ዓይነ ስውር ባል ይህንን አያውቅም እናም በትዳራቸው ሕይወት ውስጥ ምንም ልዩነት አልነበረም፡፡እሷም እሱን መውደዷን ቀጠለች እሱም በጣም ይወዳት ነበር፡፡አንድ ቀን በድንገት ሞተች፡፡ ድንገት መሞቷ ታላቅ ሀዘን አምጥቶለታል፡፡ሀዘን ሲበረታበት ከዚያች ከተማ ለመልቀቅ ፈለገ፡፡በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች
አሁን እንዴት ብቻውን መሄድ ይችላል? በእነዚህ ሁሉ ቀናት ሚስቱ ነበር የምትረዳው፡፡ ብለው ይወያዩ ነበር፡፡ሰውየውም

አይነስውር አይደለሁም ብሎ መለሰ፡፡ይህን ያህል ጊዜ የማላይ መስዬ ነበር የቆየሁት፣ምክንያቱም የቆዳ በሽታ እንዳለባት አውቅ ስለነበር የሷን ስሜት እንዳይጎዳ ብዬ ነው፡፡ውበቷ ሲጠፋ መጨነቅ ስለጀመረች ምንም እነዳልሆነ እንዲሰማት ነበር፡፡ስለዚህ እንደማላይ ነገርኳት፡፡እሷ ለኔ በጣም ጥሩ ሚስት ነበረች፡፡እሷን ደስተኛ ማድረግ ብቻ ነበር የምፈልገው ፡፡

አንዳንድ ጊዜ አውቀን አየተን ልናልፋቸው የሚገቡ ጉዳዬች ስናልፋቸው ፣ በዙሪያችን ካሉ ሰዎችን ጋር ያለን መልካም ግንኙነት እንዲጠነክር ይረዳል፡፡
ናትናኤል ቤኪ ነኝ። ሀሳብ አስተያየት ካለዎት በዚህ ሊንክ ያስቀምጡልን። @CbekinaT

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ @Biblicalmarriage
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን


➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
633 viewsNatinael Beki, 19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 02:35:18
14.2K ተከታይ ያለውን የቲክቶክ ገፄን Follow በማድረግ ዘወትር ማክሰኞና ሐሙስ በሚኖረኝ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም አብረውኝ እንዲሆኑ እጋብዛለሁ!

ቀጣይ የሚኖረኝ ዝግጅት #ፖርኖግራፊና_ጉዳቱ የሚል ነው!

ሊንኩን ተጭነው ቤተሰብ ይሁኑ!

tiktok.com/@abrish_tilahun


Biblicalmarriage
1.8K views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 23:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 21:50:10
2.9K views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 16:36:38
የፍቅር ጓደኛ አሎት?
Anonymous Poll
35%
ሀ. አዎ
65%
ለ. የለኝም
642 voters2.3K views ༒☬አብርሃም ጥላሁን☬ ༒ , 13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ