Get Mystery Box with random crypto!

Bemnet Library

የቴሌግራም ቻናል አርማ bemnet_library — Bemnet Library B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bemnet_library — Bemnet Library
የሰርጥ አድራሻ: @bemnet_library
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 46.29K
የሰርጥ መግለጫ

ሁሉም ዓይነት መፅሀፍ ለእርስዎ ቀርቧል
#ማጋራት መተሳሰብ ነው
! ከ 2014 ጀምሮ! እንደ እርስዎ ላሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ቁጥር 1 ምርጫዎች ነበርን
💬 @Bemni_Alex

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-09-03 11:43:29
አዘጋጅ Sheger Fm
3.8K viewsBemni, edited  08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 20:11:24 @Bemnet_Library

በጀርመን ወታደሮች ባህሪና ድርጊት እጅጉን ይበሳጭ የነበረው አይንስታይን በጣልያን ኑሮውን ሲመሰርት የጀርመን ዜግነቱን ሰርዞ የስዊስ ዜግነት እንዲሰጠው ጠየቀ፤ጥያቄውም ተቀባይነት አገኘ። ይህንኑ አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ፦ <<ሰው በሕግ ፊት የእኩልነት መብቱና ነፃነቱ የማይጠበቅበትና የወደደውን ማስተማር የማይችልበት ሀገር ዜጋ ለመሆን ስለማልፈልግ ብቻ ይህን ወስኛለሁ>> በማለት ተናግሯል።

የአቶሚክ ኢነርጂን ቀመር በማግኘት የታላቅ እውቀት ባለቤትነቱን ካረጋገጠ በኃላ በዲሴምበር 11/1945 የኖቤል ሽልማት ተቀብሎ ንግግር እንዲያደርግ ተጋበዘ።ንግግሩ አጭር ነበር፦ <<ጦርነቱን አሸንፈናል፤ሰላምን ግን አላሸነፍንም(we won the war,but not the peace)>>።የአቶሚክ ኢነርጂ ቀመር በመጠቀም የአውቶሚክ ቦምብ ከተሰራ በኃላ "የኒውዮርክ ታይምስ" ጋዜጣ አዘጋጅ ወደ አይንስታይን መኖሪያ በማቅናት በእሱ ግኝት ስለተሰራው አውዳሚ መሳሪያ የተሰማውን ጠየቀው፦ <<እኔ የማውቀው አንድም የአውቶሚክ ቦምብ አለመስራቴን ነው፤ሰዎች መስራታቸውን ግን ስምቻለሁ>> አለው።ይህን ማለቱ የእሱ ግኝት አላማ ለሰው ልጅ ልማት እንጂ ጥፋት እንዳልነበር፤ነገር ግን ሰዎች ግኝቱን በመጠቀም የጥፋት መሳሪያ መስራታቸውን ለመግለጽ ነው።

ለጋዜጠኛው በማከልም እንዲህ አለው፦ <<ልብ በል!እኔ አውቶሚክ ኢነርጂን ቀድሜ ባላገኘው ኖሮ ጀርመኖች ማግኘታቸው አይቀርም ነበር።በዚህም ግኝታቸው የሰው ዘር ቁንጮ እኛ ነን ለሚሉት እንደማረጋገጫ ይጠቀሙታል።ምናልባት የእኔ ስህተት ፕሬዚዳንት ሩዝቬልት የአውቶሚክ ቦንብ እንዲሰራ ሲጠይቀኝ መፈረሜ ነበር፤እሱም ቢሆን ይቅርታ አይነፈገኝም።የጊዜ ጉዳይ እንጂ ጀርመኖች እሱንም መስራታቸው አይቀርም ነበር>> ብሏል።ጋዜጠኛው በማስተካከል አንድ ጥያቄ አቀረበለት፦<<ታዲያ አቶሚክ ቦንብን የሰሩት እንዴት መቆጣጠር ያቅታቸዋል?>> አይንስታይን ለጥያቄው ሲመልስ <<ይህ የሚያሳየው ከፊዚክስ ይልቅ ፓለቲካ ከባድ መሆኑን ነው>> አለው።

ስለአለም ሰላም ተጠይቆም በሰጠው መልስ፦<<ሶስተኛው የአለም ጦርነት በምን እንደሚካሄድ ባላውቅም አራተኛው ግን በድንጋይና በዱላ እንደሚሆን አውቃለሁ>> በማለት የሰው ልጅ ስልጣኔ መጥፊያ የመቃረቡን ስጋት ገልፆ<<ለዚህች አለም ሰላም ማምጣት ከተፈለገ ግን የጋንዲን ሃሰብ ብቻ ስራ ላይ ማዋል በቂ ነው>> ብሏል


ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
1.4K viewsBemnet, edited  17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 23:14:21
መውሰድ ከምትችለው በላይ ምን ማከል እንደምትችል አስብ!

እ.ኤ.አ. በ1993 በሱዳን በተከሰተው ረሃብ ወቅት አንዲት ሱዳናዊት ህፃን ልጅ በጠኔ ተይዛ ከሞት ጋር ግብግብ ላይ እያለች ስትወድቅ(ስትሞት) ሊበላት የሚጠብቃት አሞራ አጠገቧ ቆሞ የሚያሳይ ፎቶ አለም ላይ ተሰራጨ።ፎቶግራፉን ያነሳው ደቡብ አፍሪካዊው ጋዜጠኛ ኬቨን ካርተር ሲሆን በዚህ ፎቶ የተነሳ የምርጥ ፎቶ የፑሊትዘር ሽልማትን ተቀናጀ።

ይሁን እንጂ ኬቨን ያገኘውን ስኬት ያጣጣመው ለውስን ጊዜያት ብቻ ነበር፡፡
ከዚያ አሳዛኝ ፎቶግራፍ በኋላ አብዛኛው ተመልካች የአድናቆት ቃላትን ሲያጎርፉለት አንዱ የፎቶግራፉ ተመልካች ግን በአድናቆት ብቻ ሊያልፈው አልፈለገም "እውነት ለመናገር ግሩም ፎቶግራፍ ነው ያነሳህው ነገር ግን ያ አሞራ መውደቋን በጉጉት ሲጠባበቃት ለነበራት ህፃን ምን አደረግክላት?" ሲል ጠየቀው::

"በረራ ስለነበረብኝ ህፃኗን መርዳት ሆነ ፍፃሜዋን ማወቅ አልቻልኩም" ሲል መለሰ፡፡በመልሱ የተበሳጨው ተመልካች ታድያ በግዜው ልጂቱ በሁለት ጥንብአሳ ተከባ ነበረች በለኛ? አንዱ ጥንባሳ ሊበላት እየጠበቀ ሌላኛው ካሜራ ይዞ | እየቀረፀ..." ሲል አፌዘበት።

ካሜራማኑ ከዚያች ምልልስ በኋላ ህሊናው ሰላም አጣ ለዛች ህፃን ምን አደረግክ? ለሚለው ጥያቄ መልስ አጣ፤ በስተመጨረሻ በጭንቀት ብዛት እራሱን አጠፋ..በምናደርገው ማንኛውም ነገር፣ ከሁኔታው የምናገኘውን ነገር ከማስቀደም የሰው ልጅ እንዲቀድም መፍቀድ አለብን።ጋዜጠኛው ፎቶግራፍ ከማንሳት በዘለለ ትንሿን ልጅ አንስቶ ወደ የተባበሩት መንግስታት የምግብ ማእከል ቢወስዳት ኖሮ ዛሬ በህይወት ሊኖር እና የበለጠ ሊከበር ይችል ነበር።

Teklehayimaot Abebe

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library u
2.6K viewsBemnet, 20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 00:06:26
" አንድ ቀን እንዲህ ብለሽ ትጠይቂኛለሽ .... ከኔ ሕይወት እና ካንተ ሕይወት ይበልጥ አስፈላጊው የቱ ነው ? ስትይ .... እኔ ደግሞ የኔ ሕይወት ! እልሻለሁ አንቺም ደንግጠሽ ከኔ ታፈገፍጊያለሽ ምክንያቱም የኔ |ሕይወት አንቺ መሆንሽን አታውቂምና።"


#ካህሊል_ጂብራን


ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
3.2K viewsBemnet, edited  21:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 22:42:26
ወደ ሰማይ አንጋጥጬ ስመለከት ይህ ሁሉ ጭካኔ፣እንደሚያበቃ፣ ዳግም ሰላም ና መረጋጋት እንደሚመጣ ተሰማኝ። ሁሉም ነገር ወደተሻለ ነገር እንደሚቀየርም ተረዳሁ።

#አና_ፍራንክ


ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
3.0K viewsBemnet, edited  19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 22:33:26
አንድ ሰዉ በዙሪያዉ ያሉት ሰዎች እነርሱ እንደሚፈልጉት ካልሆነ ይበሳጩበታል ያዝኑበታል አብዘሀኞቻችን ሌሎች ምን መሆን እንዳለባቸዉ አሳምረን እናዉቃለን የራሳችንን ግን አናዉቅም

#አልኬሚስቱ

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
2.9K viewsBemnet, edited  19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 20:22:11 @Bemnet_Library

ደብዳቤው

በአንድ ጦርነት ላይ ከከሞተ ወጣት የደረት ኪስ ውስጥ የተገኘው ደብዳቤ እንዲህ ይነበባል

«የኔ ወዳጅ «እንደገና እኩለ ሌሊት መጣ። እናም ከሚፈሰው ዕንባዬ በስተቀር መፅናኛ የለኝም። ከአሰቃቂዎቹ የጦርነት መዳፎች መካከል ሾልከህ ወደ እኔ ስለመመለስህ ያለኝ ተስፋ እንዳይሟጠጥ አድርጎ የሚያፅናናኝም ምንም ነገር የለም፡፡ በሄድክ ጊዜ የተናገርካቸውን ቃላት ልረሳቸው አልችልም፡፡ እያንዳንዱ ሰው በአንድ ወቅት የሚመልሳቸው የዕንባ ብድሮች አሉት» ነበር ያልከው?

«ወዳጄ ሆይ! ምን እንደምል አላውቅም፡፡ ሆኖም በመለያየት የተጎዳችው፣ ግን ደግሞ ለስቃይ ደስታን እንዲሁም ለሀዘን ተድላን በሚሰጥ ፍቅር የተፅናናችው ነፍሴ ራሷን በብራና ውስጥ ተድላን አንቆረቆረችው፡፡ ፍቅር ልባችንን ሲያጣምረው እና ሁለቱ ልቦቻችን በሀያሉ እግዚኣብሄር እስትንፋስ የሚዋሃዱበትን ቀን ስንናፍቅ ጦርነት በአስፈሪ ጩኸቷ ተጣራች። አንተም መሪዎቹ በጣሉብህ ግዴታ ተገፋፍተህ ተከተልካት"

«ሴቶችን ጋለሞቶች፣ ህፃናትን ደግሞ የሙት ልጆች አድርጎ ፍቅረኞችን የነጣጠላው ይህ ግዴታ ምንድን ነው? ጦርነቶችን ቀስቅሶ ግዛቶችን በከንቱ ያጠፋው ይህ የሀገር ፍቅር ምንድን ነው? ደግሞስ ከአንዷ ህይወት ጋር ሲነፃፀር የበለጠ ተራ ሊሆን የሚችለው ምንድን ነው? በአታላይ ፖለቲከኞች ዘንድ ከምንም የማይቆጠሩትን ምስኪን መንደርተኞችን ለጨቋኞቻቸው ሃያልነት ሲሉ እንዲሞቱ የሚጋብዛቸው ግዴታ ምንድን ነው? ግዴታ በህዝቦች መካከል ያለውን ሰላም ካጠፋ እንዲሁም የሀገር ፍቅር የሰውን ህይወት መረጋጋት ከበጠበጠ የሀገር ፍቅር ምንድነው??

«ተወው ወዳጄ ሆይ! ተወው! ዝም ብዬ ነው። ለቃላቶቼ ትኩረት አትስጥ! ጀግናና ለሀገርህ የምትታመን ሁን፡፡ ... በፍቅር ታውራ በስንብት እና ብቸኝነት ውስጥ የጠፋችውን ልጃገረድ ወሬም አትስማ፡፡በዚህኛው ህይውት ፍቅር ለእኔ ሲል በህይወት ካልመለሰህ እንግዲያውስ በእርግጠኝነት ፍቅር በመጪው ህይወት ያገናኘናል።ለዘለአለም ያንተው»

#ካህሊል_ጂብራን


ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
3.2K viewsBemni, edited  17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 09:07:39
ርዕስ=The Art of publik speakig
ደራሲ=Dale carnegie
ርዕስ=የንግግር ጥበብ
ተርጓሚ= ዮሐንስ አዳም

ንግግር ለመጀመር እንዳትጣደፉ፡ ጥድፊያ መሸበርንና ሁኔታዎችን መቆጣጠር አለመቻልን ያሳያል፡፡

ንግግራችሁ ውስጥ ስህተት ስታገኙ ይቅርታ አትጠይቁ። ይቅርታ መጠየቅ አያስፈልግም። ይቅርታ የምትጠይቁ ከሆነ ግን ይቅርታው አያግዛችሁም። ሰለዚህም ንግግራችሁን ቀጥሉ፡፡

በእርጋታ ከልብ ተነፍሱ፤ ንግግራችሁን ልክ እንደ ትልቅ ጓደኛችሁ እያወራችሁ እንደሆናችሁ በተረጋጋ መንፈስ አስቡ። ከዛ ንግግራችሁን እንደፈራችሁት መጥፎ ሆኖ አታገኙትም፡፡ ይህ ልክ ውኃ ውስጥ ጠልቆ እንደመግባት ዓይነት ነገር ነው። ውኃው ውስጥ ጠልቃችሁ ከገባችሁ በኋላ ወኃው ይረጋጋል፡፡ ሰለ እውነቱ ከሆነም ለጥቂት ጊዜ ንግግሮችን ካደረጋችሁ በኋላ የውኃ ጠለቃውን በደስታ የምትጠብቁ ይሆናል፡፡ከታዳሚው ፊት ቆማችሁ ታዳሚው ሐሳቦቻችሁ ደስታን የሚያጭሩላችሁ መሆኑን ያስብ ዘንድ ታደርጋላችሁ፡፡

Eneho books


ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
3.5K viewsBemni, edited  06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 00:20:06 ውዶቼ በእምነት እንዲህ ይላል፦

ወደፊት መጽሐፍ ብቻ አይደለም የምንልክላችሁ ደራሲውን ጭምር ነው። ስለዚህ አብራችሁን ዝለቁ!ለዛሬ 5 የመጽሐፍ ጥያቄዎችን መልሰናል። በቀጣይ የሁላችሁንም ጥያቄ ለመመለስ ጥረት እናደርጋለን።ታዲያ "ማጋራት መተሳሰብ ነው" የሚለው መርሃችን እንዳይረሳ!ካነበባችሁ በኃላ ለወዳጆቻችው አጋሯቸው።በተረፈ ምርጥዬ የሆነ አዳር ተመኘሁላችሁ


ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
3.4K viewsBemni, 21:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 23:59:54 #5

ናትናኤል "ሸበጥ" የተሰኘውን የብርሃን ዳኜ መጽሐፍ ጠይቋል ይህው ናቲ #መልካም_ንባብ

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
3.1K viewsBemni, 20:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ