Get Mystery Box with random crypto!

Bemnet Library

የቴሌግራም ቻናል አርማ bemnet_library — Bemnet Library B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bemnet_library — Bemnet Library
የሰርጥ አድራሻ: @bemnet_library
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 46.29K
የሰርጥ መግለጫ

ሁሉም ዓይነት መፅሀፍ ለእርስዎ ቀርቧል
#ማጋራት መተሳሰብ ነው
! ከ 2014 ጀምሮ! እንደ እርስዎ ላሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ቁጥር 1 ምርጫዎች ነበርን
💬 @Bemni_Alex

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-09-07 07:20:05 ተአምረኛው ማለዳ:The Miracle Morning

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
1.8K viewsBEMNET, 04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 07:19:58
አዘጋጅ Hal Elrod
1.7K viewsBEMNET, edited  04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 19:30:52 ይህው መጽሐፉ አንብቡት.....

#አካላዊ_ብቃት_ለሁሉም

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
121 viewsBEMNET, 16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 19:00:01
ውዶቼ ብታምኑም ባታምኑም ስፖርት መስራት የጀመርኩት ይሄን መጽሐፍ ካነበብኩ በኃላ ነው።እንደውም አንድ ቀን የስፖርት መንፈሴ ተነሳስቶ ለወራት ያክል ጂሙንም፣ ፑሽአፑንም ፣ ቁጭ ብድጉንም፣ ሩጫውንም ሳይቀር ሳጧጡፈው ዋልኩኝ!

ከዛ በሚያስገርም ሁኔታ ጡንቻዬ እንደ ድፎ ዳቦ መፋፋት ጀመረ፤ሁሉም ጎሮቤቴ ተገረመ፤ጓደኞቼ ሳይቀሩ ይሄ ግን በእምኒ ነው እያሉ እስከመጠራጠር ደረሱ።ፋዙካና ማዘርም ግርም ብለው "ሚስጥሩ ግን ምንድን ነው?" ብለው ጠየቁኝ፤እኔም ዘና ብዬ " ሚስጥሩ "አካላዊ ብቃት ለሁሉም" የሚለው የፍቅሩ ወልደየስ ምርጥዬ መጽሐፍ ነው " አልኳቸው።አሁን ሁሉቱም የኔን ፈለግ ተከትለው ጡንቸኛና ጤኔኛ ሆነዋል ፈጣሪ ይመስገን

መጽሐፉን በpdf ያዘጋጀልን የምንግዜም የበእምነት ላይብረሪ ተከታይ የሆነው ፍፁም ሽዋንግዛው ነው።ፍፁምዬ በጣም እናመሰግናለን፤ይለመድብህ ብለናል! በተረፈ ከበእምነት ላይብረሪ ጋር ምርጥዬ ምሽት እንዲሆንላችሁ ተመኘሁ።i sure 100% ትወዱናላችው።

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
511 viewsBEMNET, edited  16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 16:01:02
አዘጋጅ inspire Ethiopia

እነዚህ ቲክቶክ ላይ ከ4 ሚሊዮን በላይ እይታዎች ያገኙ ምርጥ ምርጥ አነቃቂ ንግግሮች ስብስብ ናቸው!

#እኔን ከማነቃቃትም በላይ አአስተምሮኛል! እናንተም እንደምትማሩበትና እንደምትለወጡበት አልጠራጠርም።

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
1.3K viewsBEMNET, edited  13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 15:31:48
የቱ ነው ሰው ማለት

በውስጡ እያደባ በአፉ የሚጫወት
እኔን ግራ ገባኝ የቱ ነው ሰው ማለት?
ወይስ እያበላህ ዞር ብሉ የሚያማህ
ዛሬ የኔ ነው ስትል ነገ የሚከዳህ
ጓደኛ ስትለው የሚሆንህ ጠላት
እስቲ እንነጋገር የቱ ነው ሰው ማለት?

እኔ አንዳንድ ጊዜ ጓደኛዬ እልና
የሆዴን በሙሉ ዘክዝኬ እነግርና
መፍትሔ ስጠብቅ ለነገርኩት ሚስጥር
ሲወራ እሰማለሁ ጉዳዬ ከመንደር።
እኔም ጓደኛዬን ምነው እባክህ ብለው
ችግሬን አዳምጠህ መፍትሔ ሳትሰጠው
ምን በደልኩህና ለአገር ነዛኽው?
ብዬ ብጠይቀው ብሎ መለሰልኝ ለአንድ ሰው ብቻ ነው።

ሚስጥር ከሁለት ሰው ካለፈ ጨዋታው
ነገር መባከኑን እንደምን አጣኽው?
መፍትሔ ሳይሰጥህሚስጥር የሚያወጣው
የጓደኝነት እምነት መለኪያ ምንድነው?
ለጥያቄዬ መልስ ሃሣብ እፈልጋለሁ።
እናንተም ንገሩኝ ሰው ማለት የቱነው ሰው ያለሰው መኖር እንደማይችል አውቀህ ሰው ሆይ ለጓደኛህ ታማኝ ሁን እባክህ።

#ህልምና ስኬት ከሚለው የገጣሚ ሙሉመቤት ገብረዮሐንስ የግጥም መጽሐፍ ላይ የተወሰደ...


ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
1.4K viewsBEMNET, 12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 22:58:46 በህይወቴ ብላክ ቦርድ ላይ በቾክ የተፃፈ ነገር በዳስተር ሲጠፋ አይቼ አውቃለው።ነገር በልብ ውስጥ የተፃፈ ፍቅርና አፍቃሪውን እንደ ወላፈን የሚያብከነክን ትዝታ በምንና እንዴት ሊጠፋ እንደሚችል አላውቅም!

ውድ ሲኞሪታ በፍቅርሽ ማዕበል ውስጥ እንደምንም ብዬ ያለፍኩት የመጀመሪያው ወንድ እኔ እንደሆንኩ ነግረሽኝ ነበር።ለመጀመሪያ ጊዜ የፍቅርን ጣዕም የቀመስኩት በአንተ ነው ያልሽንም ጊዜ በፍፁም አረሳም።በሀይቁ ዳር ተቀምጠን ጀልባ ላይ ሆነው የሚፈነድቁትን ልጆች እያየን "እንደዚህ አይነት ልጆች ቢኖሩኝ ኖሮ ብዬ" በውስጤ ሳስብ "እኔም" ያልሽበትን ጊዜ እንዴት ልረሳ እችላለሁ።

ደግሞ ታመመስ ስትባይ ድንግጥግጥ ብለሽ በቢጃማ ቀሚስ ከድሬ እስከ ደዘ በወይኔ አለም ታክሲ የመጣሽበትን በእንባ ታጥበሽ ዝለሽ "በእምነት ደና ነው" ብለሽ የጠየቅሽው ዶ/ር አዳኝ ዘውዱን እየሰማው ነበር በመዳን ስሜት ውስጥ አንቺን እያሰብኩ!

ግን ምን ዋጋ አለው።መድሀኒቱን ልግዛ ብለሽ እንደወጣሽ አውቀሽ ይሁን ታመሽ ወይ ችግር አጋጥሞሽ ሳላውቅ በዛው ቀረሽ።እኔ እንደው በትዝታሽ ማዕበልና በሃሳቤ ጓዳ በጣም ስላሰብኩሽ የውስጤ እውነታ በእውኑ አለም ወጣ፤"ብዙ ሰዎች በእምነት ምን ሆነህ ነው" አሉኝ አንቺን እያሰብኩኝ ራሴን ጎድቼ በእውን አለም ያዩኝ..እኔም "ምንም" አልኩ የሚታየውን እውነት ከሰው እየደበኩ፤ብቻ ምንም አይደል ይሄ ሁሉ ያልፋል፤እንደምትመጪ ልቤ ይነግረኛል፤እውነቱን ነው ብዬ ስለተቀበልኩ ከህሊናዬ ጋር እየተፋለምኩ እወንዙ ዳር ሆኜ እስከ መስከረም 1 ልጠብቅሽ ወሰንኩ።አዲስ አመት አዲስ ተስፋ አይደል የሚባለው!"
እባክሽ ነይና በአዲስ ተወልጄ ተስፋዬን ላድሰው

@Bemni_Alex


ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
2.6K viewsBEMNET, edited  19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 18:32:06 ውጪያዊ ማንነት

መለኪያው ምን ይሆን የማንነት ትርጉም
ቁመት ነው ቁንጅና ወይስ ደግሞ ቀለም?
ወይስ የቀይ ዳማ ቅላትና ጥቁረት
በሥጋ መተለቅ ውፍረትና ግዝፈት?
ይሆን ቀጠን ብሉ ረዘም ያለ ቁመት
የዕድሜ መጨመር፣የፀጉር መሽበት
የቱ ይሆን መለኪያው የሰው ሰውነቱ
መልካም ሥራ ሠርቶ የሚያሰኘው አንቱ?
የሰው ልጅ ማንነት ከውስጥ ካልወጣ
ላይ ላዩን ቢያሣምር ሲገባ ሲወጣ!
ቢማር ቢመራመር ቢሞላ በጥበብ
እኔ የማምንበት የማሰፍረው ነጥብ፤
ስለ ውበት ሳይሆን ስለ ሰው ቁንጅና
በውጪ ሰውነት መልክና ቁመና፤ ፀባይ ቁምነገር ነው የሰው መመዘኛ
ማንነት መለኪያው ባለባበስ ሳይሆን የውጪውን አካል ግርዶሽ አርጉ መልክን
መልክን ግርዶሽ ኣርገው የውጭውን አካል
ንፁህ ቅን አሳቢ ራስን በማስመሰል ስንቱን አሰቃይቶ ስንቱን በማታለል ብዙ ጨካኝ አለ ኣጉል ጨዋ መሰል።
ደግሞ በሌላ አንፃር ውጪው ያላማረ
እንዲሁ ሲታዩ በውጭ አካላቸው
በጨካኝ ወንበዴ ስንፈርጃቸው
መልካም በጎ ሥራ ሆኖ ተግባራቸው
ውስጣቸው ያማረ ብዙ ሰዎች ናቸው፡፡
የውስጥ ነፀብራቅ ካልወጣ በይፋ
ውጭን በማሣመር ቢዘከር ቢለፋ
ራስን ማታለል ነው በሐሰት ልፍለፋ፡፡
በዝና ደንዝዞ ለማስመሰል ቢጥር
በጉራ ቢፎልል ምን ቁመናው ቢያምር ከውስጥ ከሌለ ዝንተ ዓለም አይሠምር፡፡

#ህልምና ስኬት ከሚለው የገጣሚ ሙሉመቤት ገብረዮሐንስ የግጥም መጽሐፍ ላይ የተወሰደ...


ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
3.1K viewsBEMNET, 15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 06:03:08 በጠዋት ተነስ! Wake Up at 5:00am

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
3.6K viewsBEMNET, edited  03:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 06:02:56
አዘጋጅ Sinework Taye
3.4K viewsBEMNET, edited  03:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ