Get Mystery Box with random crypto!

Bemnet Library

የቴሌግራም ቻናል አርማ bemnet_library — Bemnet Library B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bemnet_library — Bemnet Library
የሰርጥ አድራሻ: @bemnet_library
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 46.29K
የሰርጥ መግለጫ

ሁሉም ዓይነት መፅሀፍ ለእርስዎ ቀርቧል
#ማጋራት መተሳሰብ ነው
! ከ 2014 ጀምሮ! እንደ እርስዎ ላሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ቁጥር 1 ምርጫዎች ነበርን
💬 @Bemni_Alex

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-10 16:46:46 መፅሐፍ አንብቦ ያልተለወጠ ሠው ካላነበበው ሠው ምንም የሚለየውና የሚሻለው ነገር የለም

ወዳጄ ሆይ…. መፅሐፍት የሚያስተምሩህ በሠውነትህ ላይ ሌላ ሠዋዊ ተፈጥሮ እንድትጨምር ሳይሆን ትክክለኛ፣ ዓላማ ያለው፣ ዕውቀት ያለው፣ ምግባርና ንግግሩ አንድ የሆነና መልካም ማንነት ያለው ሠው መሆን እንዴት እንደምትችል ነው፡፡፡

መፅሐፍት ዓላማና ራዕይ እንዲኖርህ የዕውቀት ስንቅ ያዘጋጁልሃል፡፡ ለራስህና ለዓለም በጎ ታሪክ ጥለህ ማለፍ እንድትችል ብርታትና ጥንካሬ፣ መልካም አመለካከትና ቅንነት እንዲኖርህ ያግዙሃል፡፡ ይሄ የሚሆነው ግን ጎበዝ ተማሪ ከሆንክ ብቻ ነው፡፡ ጎበዝ ተማሪ መሆን ብቻውን ዋጋ የለውም፡፡ የተማረውን በተግባር መሞከር የሚችል ብልህ የተግባር ሠው መሆንም ይጠበቅብሃል፡፡

መፅሐፍ አንብቦ ያልተለወጠ ሠው ካላነበበው ሠው ምንም የሚለየውና የሚሻለው ነገር የለም፡፡ እንደው ለወሬ ፍጆታ ብቻ ካልሆነ በስተቀር! መፅሐፍት ዓለምን እንደቴሌቪዥን ያሳዩሃል፡፡ ዓለም ውስጥ ገብተህ በዕውቀት እንድትንቦራጨቅና የጥበብ ባህሩ ላይ መዋኘት እንደትችል አማካሪህ ሆነው ያገለግሉሃል፡፡ ነገር ግን እንደአንተ አይተውኑልህም፡፡ ተዋኙ ወይ ተዋንያኑ አንተው ራስህ ነህ፡፡ ተውኔቱ ደግሞ ሕይወትህ ነው፡፡ መቼቱ ኑሮህ ነው፡፡ መድረኩ ዓለምህ ነው፡፡

ያነበብከውን በአዕምሮህ አመላልሠህ፣ ሃሳብ ጨምረህና ተንትነህ መሬት አውርደህ በተግባር አስመስክረህ የምትኖርበት አንተ ነህ፡፡ ካንተ ሌላ ላንተ ማንም አይመጣም፡፡ መፅሐፍት መነሳሳት፣ እውቀትና ክህሎት እንዲኖርህ ከጀርባ ሆነው ይገፉሃል፡፡ መንገዱን የምትጀምረው ግን አንተው ራስህ ነው፡፡ ያላንተ ያንተን መንገድ የሚሄድ ማንም የለም፡፡

በዙሪያህ ያሉ ሠዎች ልክ እንደመፃሕፍቱ ለዓላማህ እንድትቆም ይመክሩህ፣ ይዘክሩህ፣ ያነሳሱህ ይሆናል እንጂ መንገድህን አይራመዱልህም፡፡ ሠው’ነትህ ላይ በጎ ምግባርና መልካም ዕውቀት እንድትጨምር መፅሐፍት ይረዱሃል እንጂ ራሳቸው ወደውስጥህ አይገቡም፡፡ ጨማሪውም ሆነ አስገቢው አንተው ራስህ ነህ፡፡ በምንነትህ ላይ ማንነትህን እንድትገነባ የመጽሐፍት ገፆቹ እንደመስታወት ሆነው ዓለሙን ያሳዩሃል፡፡

አንባቢ ሁሉ ባነበበው አይታነፅም፡፡ ብልህ አንባቢም መሆን ይጠበቅብሃል፡፡ ትንሽ አንብበህ ብዙ ማሠላሠል ግድ ይልሃል፡፡ ያነበብካቸውን ቁምነገሮች ከራስህ ሃሳብ ጋር እያስተሳሰርክና እያዋሃድክ የራስህ አዲስ ሃሳብ እንዲኖርህ መፅሐፍት መንገዱን ይጠርጉልሃል፡፡ የሁሉም ነገር ቁልፍ ያለው አንተው እጅ ላይ ነው፡፡ ቁልፉ ደግሞ አስተሳሰብህ ነው፡፡ የቁልፉ ጋን ምግባርና ተግባርህ ነው፡፡ ያነበብከውን በተግባር ካላረጋገጥክ መረጃ እንጂ ዕውቀት አልያዝክም ማለት ነው፡፡ ዕውቀት ማለት በማንበብ የሠበሰብከውን መረጃን በመጠቀም ለበጎ ዓላማ በተግባር በስራ ላይ ማዋል ነው፡፡ ዕውቀት በተግባር የሚገለፅ እንጂ በወሬ ላይ ብቻ የተንጠላጠለ አይደለም፡፡ ተማሪ የሚማረው ሊሠራበት ነውና ያነበብከውን አመዛዝነህ፣ ከራስህ ሃሳብ ጋር አዛምደህ፣ ከዘመኑ አዋጅተህ፣ የራስህን ሃሳብ ፈጥረህና አሳድገህ በገቢር ታውለው ዘንድ በርታ፡፡

መፅሐፍት ጌጥ ሳይሆን የነፍሳችን ምግብ ነው፡፡ ምግቡን አላምጦና አጣጥሞ መዋጥ ግድ ይላል፡፡ መዋጫ ውሃው አመለካከት ነው፡፡ አመለካከትህ መልካም ካልሆነ ጣፋጩ እሬት ይሆንብሃል፡፡

ወዳጄ መፅሐፍት ውስጥ የምታገኛቸውን ቁምነገሮች እንደ ማስቲካ አላምጠህ ከመትፋት ይልቅ አጣጥመህ ዋጣቸው፡፡ ማጣጣም ማለት ከራስ ሃሳብ ጋር ማስታረቅ ነው፡፡ ማጣጣም ማለት በሌሎች ሃሳብ ምሣሌነት የራስን ሃሳብ ማግኘት ነው፡፡ የሌሎችን ሃሳብ እንዳለ መገልበጥ ሳይሆን የራስን ሃሳብ በሌሎች መስታወትነት መስራት ነው፡፡ አበቃሁ!

ቸር ጊዜ!

እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
3.2K viewsBEMNET, edited  13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 09:28:38
ቃል መታመኛ ነው።ፍቅረኛሞች ሲጋቡ ቃል ይገባባሉ።ታምኜሽ እኖራለሁ፤ታምኜህ እኖራለሁ ተባብለው አንዳቸው ለአንዳቸው ሊኖሩ የኑራቸውን ጅማሬ በቃል ያስራሉ።

በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ ያሉ ሰዎች ተምረው ሲመረቁ ቃል ይገባሉ።በተማሩት መሰረት ህዝባቸውን በታማኝነት ለማገልገል።ሰዎች ብር፤ ዕቃ ሲዋሱ ለመመለስ ቃል ይገባሉ። ጓደኛዬ ወይም ታማኜ ብለው ሚስጥር የሚያካፍሉት ሰው ሚስጥር ለመጠበቅ ቃል ይገባሉ።እነኝህ ሁሉ ቃላቸውን ቢያፈርሱ የሚደርስባቸው ትዝብት ነው።

ወታደር ሀገሩን ለመጠበቅ ሰንደቅ አላማ ይዞ ቃል ይገባል። "ቃሉን ከበላ....እንደሚባለው የሃገሬ ብሂል ቃል ሲገቡት ሳይሆን ሲተገብሩት ከባድ ነው።ወታደር ቃሉን ሲያጥፍ ራሱን ይጎዳል፤ ሀገርን አደጋ ላይ ይጥላል።ሕዝብን ያስቀይማል፤ ይጎዳል።

ጋሻዬ ጤናው
'የተካደው ሰሜን ዕዝ' ደራሲ

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
3.5K viewsBEMNET, edited  06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 22:43:13 አንዳንድ ወንዶች አሉ ማፈቀራቸውን ሳይናገሩ እስከ ሞት ድረስ የሚዘልቁ፤ግን እኔ ዛሬ እነግርሻለሁ፤እንደማፈቅርሽና ለአመታቶች ያክል በፍቅርሽ ወላፈን ስቃጠል እንደነበር።

ምናልባት ለአንቺ የሚገቡ ፍቅሬን የሚገልፁ ጥዑመ ቃላቶች ላይኖሩኝ ይችላሉ።ግን አንድ ነገር ብቻ በልቤ ውስጥ ሲመላለስ በምናቤ ሲንጎራደድ ይሰማኛል። በ7 ፊደላት የተጠረዘ፣ በቀያይ ቀለሞች የተለበጠ፣ አንድበቴን ሰቅዞ የያዘ፤በልቤ ውስጥ የሚንጓለል አንድ ቃል ብቻ አለ።

እሱም "አፈቅርሻለሁ" መሆኑን ስነግርሽ ደስታዬ ከውስጤ ተንደርድሮ ፊቴን በፈገግታ ይሞላዋል።ፈገግታዬም አንድበቴን እስርስር አድርጎ መላው አካሌን በጤነኝነት መንፈስ ያንቦቀብቀዋል።እንደው ውዴ የኔ ዱንቡሽቡሽ የትኞቹ ቃላቶች ይሁኑ የሚገቡሽ...ይህው እሱን ስፈልግ ትላንት በትዝታው አታለለኝ..ነገ ደግሞ በገባው ቃል አስተኛኝ...አይኖቼን ስገልጥ ዛሬ አለቀ

@Bemni_Alex


ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
4.4K viewsBEMNET, 19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 12:53:59 ሳቅ ሲበዛ የሐዘንን ያህል እንምባ ያስፈስሳል፤መቀመጥ ሲበዛ የመስራትን ያህል ያደክማል፤ደግነት ሲበዛም እንዲሁ የክፋትን ያህል ይጎዳል እንጂ አይጠቅምም።
ሁሉን ነገር በመጠን ከያዙት ግን እንኳንስ መልካሙ ክፋውም ይጠቅማል ።

#ከበደ_ሚካኤል

ማጋራት መተሳሰብ ነው!!
@Bemnet_library
4.8K viewsBEAMLAK , edited  09:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 07:28:50 በጠዋት ተነስ! እንቅልፍን በቀላሉ ማሸነፍ

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
1.1K viewsBEMNET, 04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 07:28:41
አዘጋጅ inspire Ethiopia
1.1K viewsBEMNET, edited  04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 20:07:47 ውዶቼ ኢትዮጵያ 54 ሚሊየን ላሞች አሏት፤ሱዳን ደግሞ 42 ሚሊየን!ነገር ግን በዓለም ላይ ካሉ ድሆች አገሮች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው።

ሆላንድ 11 ሚሊዮን ላሞች አሏት!
ግን ለዓለም ወተት እና የወተት ተዋጽኦዎችን በማቅረብ ከአለም አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች

እኔ እንደሚመስለኝ ችግሩ ያለው ላሞቹ ላይ አይደለም። ኢኮኖሚውን የሚመሩ ላሞች ላይ እንጂ

@Bemnet_Library
2.3K viewsBEMNET, edited  17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 12:01:33 መውቀስ ማቆም አለብህ

ምንም አይነት ጥፋት ሌላ ሰው ላይ ብታገኝና ምንም ያህል ብትወቅሰው ወቀሳው አንተን አይቀይርም"
ዋይን ድየር

ስኬት ላለማግኝትህ የሆነን ሰው ወይም የሆነን ነገር መወቀስህን እስከቀጠልክ ድረስ ስኬታማ አትሆንም። አሸናፊ መሆን ከፈለግህ ለእውነቱ እውቅና
መስጠት አለብህ:።

እርምጃውን የጀመርከው፤ ሀሳቡን ያሰብከው፤ ስሜቱን የፈጠርከው፤ አሁን ያለህበት ቦታ እንድትሆን የመረጥከው አንተ ነህ።

የማይስማማህን ምግብ የበላህው አንተ ነህ!
አይሆንም ያላልከው አንተ ነህ!
ስራውን የተቀበልከው አንተ ነህ!
ስራው ላይ የቆየህው አንተ ነህ!
ልታምናቸው የመረጥከው አንተ ነህ!
ስሜትህን ችላ ያልከው አንተ ነህ!
ህልምህን የተወከው አንተ ነህ!
ብቻህን ለመስራት የወሰንከው አንተ ነህ!

በአጭሩ ሀሳቡን አሰብክ፤ ስሜቱን ፈጠርክ፤ ምርጫ አደረግክ! ቃላቶቹን ተናገርክ፣ ለዚያ ነው አሁን ያለህበት ላይ ያለኸው።

ከህይወት መመሪያ መጽሐፍ......

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library
1.0K viewsBEMNET, 09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 11:17:30
አዘጋጅ @Bemnet_Library
1.2K viewsBEMNET, 08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 11:05:55
አዘጋጅ @Bemnet_Library
1.2K viewsBEMNET, 08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ