Get Mystery Box with random crypto!

AHADU TELEVISION

የቴሌግራም ቻናል አርማ ahadutelevision — AHADU TELEVISION A
የቴሌግራም ቻናል አርማ ahadutelevision — AHADU TELEVISION
የሰርጥ አድራሻ: @ahadutelevision
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.31K
የሰርጥ መግለጫ

Your source for top local and international news and analysis.
"Voice of Ethiopian"
የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-12 20:21:14

2.4K views17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 11:43:20
በሚሳዔል ማዕበል የምትጠበቀው የኪሞቹ አገር

ሰሜን ኮሪያ በአራት ወራት ውስጥ አስራ አራተኛውን የባሊስቲክ ሚሳዔል አስወነጨፈች ፡፡

ፒዮንግያንግ ራሴን ለማስከበር የኒውክሌር መርሃ ግብሬን አጠናክሬ እቀጥላለሁ ባለች ማግስት ባሊስቲክ ሚሳዔል ማስወንጨፏን ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ እወቁልን ብለዋል ፡፡

ኪም ጆንግ ኡንም በጦር መሳሪያ አቅም ጡንቻችን ማፈርጠም ከዋሽንግተንም ሆነ ከሌሎች ኃይሎች የሚቀጣብንን ወታደራዊ ጥቃት ለመቀልበስ ቁልፉ ወታደራዊ ዲፕሎማሲያችን ነው ብለው ያምናሉ፡፡

አዲሱ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት በዓለ-ሲመታቸውን ሊፈጽሙ እንደሆነ እየተነገረ ባለበት ወቅት ነው ኪሞቹ ባሊስቲክ ሚሰዔል ያስወነጨፉት ፡፡

ሰሜን ኮሪያ የመጨረሻ ሙከራዋን ያደረገችው በፈረንጆቹ ሚያዚያ 16 እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም ፡፡

መጋቢት ላይም ግዙፍ ነው ያለቸውን አህጉር አቋራጭ ሁዋሶንግ -17 የተሰኘ ባሊስቲክ ሚሳዔል ማስወንጨፏም ይታወሳል ፡፡

ሚሳዔሉ 4 መቶ 70 ኪ.ሜተትሮችን የሚያቋርጥ እና በ7መቶ 80 ኪ ሎ ሜትር ከፍታ የሚምዘገዘግ ነው ፡፡

የሰሜን ኮሪያ ተደጋጋሚ የሚሳዔል ሙከራ ለዩናይትድ ስቴትስ ፣ለጃፓን እንዲሁም ለጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያ ስጋት ከሆነ ሰነባብቷል ፡፡

ፒዮንግያንግ ዩናይትድ ስቴትስ ድረስ ዘልቆ ውድመት የሚያስከትል ረቂቅ የጦር መሳሪያ እንዳላት መታወቁ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ተደርጋ እንድትሳል አድርጓታል ፡፡
ኒውዮርክ ታይምስ እና ዎል ስትሪት ጆርናል እንዳስነበቡት
በብንያም ካሴ
አሐዱ ቴሌቪዥን
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ahadutelevision
2.8K views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 12:17:44
የሩሲያ ጥቃት በጥቁር ባህሯ ከተማ
ሩሲያ በዩክሬን የወደብ ከተማ ላይ የሮኬት ጥቃት ማድረሷ ትችት እያሰነዘረባት ነው ፡፡
ሰኞ ጠዋት ላይ በደቡባዊ ዩክሬን ኦደሳ ከተማ የተፈጸመው ጥቃት ውደመት ማስከተሉን የዓለም መገናኛ ብዙኃን እያስነበቡ ይገኛሉ ፡፡
የመኖሪያ ህንጻ መውደሙን እና የአስራ አምስት ዓመት ታዳጊ ህይወቱን ማጣቱን ልታውቁት ይገባል ሲል የከተማዋ አስተዳደር አስገንዝቧል፡፡
ፕሬዚዳንት ዜሌንስኪም ይሄንው አረጋግጠዋል፡፡
የሩሲያ ጥቃት በዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ላይም ጉዳት አድርሷል ፤የዩክሬን ባለስልጣናትም ጥቃቱን አውግዘዋል ፡፡
ኦደሳ የዩክሬን ግዙፍ እና እጅግ አትራፊ የባህር ወደብ ናት ይሏታል፡፡
ዋሽንግተን ፖስት እና ቢቢሲ እነደዘገቡት ከተማዋ በስልታዊነትም ሆነ በምሳሌነት ሁነኛ ዒላማ ተደርጋ ትወሰዳለች ፡፡
በብንያም ካሴ
አሐዱ ቴሌቪዥን
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24 #Ahadu_News_24 #News_24 #Ahadu #News
2.0K views09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 11:38:29
የዩክሬኗ ዋና ከተማ መመታትና የጉቴሬዝ ራሳቸውን መውቀስ

የዩክሬኗ ዋና ከተማ ኪዬቭ በሩሲያ ሚሳዔሎች መመታቷን የዩክሬን መንግስት አስታወቀ ፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዩክሬንን እየጎበኙ ባሉበት ሰዓት ነው ጥቃቱ የተፈጸመው ፡፡

ሩሲያ ሁለት ሚሳዔሎችን ወደ ኪዬቭ ማስወንጨፏን የዩክሬን ባለስልጣናት አረጋግጠዋል ፡፡

ባለስልጣናቱ እንደሚሉት አንደኛው ሚሰዔል ባለ ሀያ አምስት ፎቅ ህንጻን የመታ ሲሆን ቢያንስ አስር ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል ፡፡

የሐሙሱ ጥቃት የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀኃፊ ጉቴሬዝ ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚየር ዜሌንስኪ ጋር የነበራቸውን ውይይት እንዳጠናቀቁ መፈጸሙ ቀውሱን አሳሳቢ አደርጎታል ፡፡
ኪዬቭ አሁንም ለሩሲያ ሚሳዔሎች የተጋለጠች እና ሰለባ የሆነች ከተማ መሆኗም አጽንኦት ተሰጥቶበታል ፡፡

ጉቴሬዝ የሚመሩት ድርጅት በዩክሬን ጦርነት ላይ መፍትሔ መስጠት አለመቻሉንም ተችተዋል ፡፡

ዋና ፀኃፊው የፀጥታው ምክር ቤት በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለመከላከል ወይንም እንዲቆም ለማድረግ የፈየደው ነገር የለም ባይ ናቸው ፡፡

ባለ አስራ አምስት ዓባላቱ የጸጥታው ምክር ቤት ለዓለምን ሰላም ማስፈን ቀዳሚ ስራው ቢሆንም ይህን ግን ማሳከላት አልቻለም ብለዋል ጉቴሬዝ ፡፡
ጉቴሬዝ ራሳቸውን እና የሚመሩትን ድርጅት መውቀሳቸው በዩክሬን ከፍተኛ ውድመት መከሰቱን የሚያሳይ ነው ተብሏል ፡፡

ዋሽንግተን ፖስት እና ቢቢሲ እንዳስነበቡት ፡፡

በብንያም ካሴ
አሐዱ ቴሌቪዥን
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ahadutelevision
1.6K views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 23:10:17 የኢራን መንግስት እስራኤልን ሊመታ እየተዘጋጀ ነው


1.2K views20:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 22:31:44 የሰሜን ኮሪያ ኒውክሌር ጉዳይ


1.2K views19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 20:10:06 ውድ ቤተሰቦቻችን የዕለተ-እሮብ አሐዱ 24 ዜና ሥርጭታችን ተጀምሯል


1.0K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 12:47:08
“ተስፋ አለኝ” ፑቲን

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን ጋር ያለው ድርድር እንደሚቀጥል ለመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸኃፊ ገለጹ፡፡

ውይይቶች በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ፑቲን አስገንዝበዋል ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በዝነኛው ነጩ ጠረጴዛቸው የመንግስታቱ ድርጅትን ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን በዩክሬን ጦርነት ዙሪያ አውርተዋቸዋል ፡፡

ከሚደረጉት ውይይቶች መልካም ውጤት ሊመጣ እንደሚችል ተስፋ አለኝ ያሉት የክሪሚሊኑ መሪ ቅድመ ሁኔታዎቻችን ሊሟሉ ግን ግድ ይላቸዋል ብለዋል ፡፡

በዕርግጥ ፑቲን የክሪሚያ እንዲሁም የሴቫስቶፖል ግዛቶች ጉዳይ ውሳኔ ካልተሰጠበት የደኅንነት ማረጋገጫውን ሊፈርሙ እንደማይችሉ አሳስበዋል ፡፡

ለስምንት ዓመታት ያህል ከዩክሬን ጋር ግጭት ውስጥ የገቡት የዶንባስ ሰዎች ጉዳይም ግምት ውስጥ የሚገባ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ አጽንኦት ሰጥተውበታል ፡፡

በብንያም ካሴ
አሐዱ ቴሌቪዥን
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24 #Ahadu_News_24 #News_24 #Ahadu #News
957 views09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 20:30:41

799 views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 18:46:12 https://www.tiktok.com/@ahadutv.official/video/7090800333269814574?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7080048124424652294
781 views15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ