Get Mystery Box with random crypto!

“ተስፋ አለኝ” ፑቲን የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን ጋር ያለው ድርድር እንደሚቀጥ | AHADU TELEVISION

“ተስፋ አለኝ” ፑቲን

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን ጋር ያለው ድርድር እንደሚቀጥል ለመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸኃፊ ገለጹ፡፡

ውይይቶች በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ፑቲን አስገንዝበዋል ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በዝነኛው ነጩ ጠረጴዛቸው የመንግስታቱ ድርጅትን ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን በዩክሬን ጦርነት ዙሪያ አውርተዋቸዋል ፡፡

ከሚደረጉት ውይይቶች መልካም ውጤት ሊመጣ እንደሚችል ተስፋ አለኝ ያሉት የክሪሚሊኑ መሪ ቅድመ ሁኔታዎቻችን ሊሟሉ ግን ግድ ይላቸዋል ብለዋል ፡፡

በዕርግጥ ፑቲን የክሪሚያ እንዲሁም የሴቫስቶፖል ግዛቶች ጉዳይ ውሳኔ ካልተሰጠበት የደኅንነት ማረጋገጫውን ሊፈርሙ እንደማይችሉ አሳስበዋል ፡፡

ለስምንት ዓመታት ያህል ከዩክሬን ጋር ግጭት ውስጥ የገቡት የዶንባስ ሰዎች ጉዳይም ግምት ውስጥ የሚገባ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ አጽንኦት ሰጥተውበታል ፡፡

በብንያም ካሴ
አሐዱ ቴሌቪዥን
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24 #Ahadu_News_24 #News_24 #Ahadu #News