Get Mystery Box with random crypto!

የዩክሬኗ ዋና ከተማ መመታትና የጉቴሬዝ ራሳቸውን መውቀስ የዩክሬኗ ዋና ከተማ ኪዬቭ በሩሲያ ሚሳዔ | AHADU TELEVISION

የዩክሬኗ ዋና ከተማ መመታትና የጉቴሬዝ ራሳቸውን መውቀስ

የዩክሬኗ ዋና ከተማ ኪዬቭ በሩሲያ ሚሳዔሎች መመታቷን የዩክሬን መንግስት አስታወቀ ፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዩክሬንን እየጎበኙ ባሉበት ሰዓት ነው ጥቃቱ የተፈጸመው ፡፡

ሩሲያ ሁለት ሚሳዔሎችን ወደ ኪዬቭ ማስወንጨፏን የዩክሬን ባለስልጣናት አረጋግጠዋል ፡፡

ባለስልጣናቱ እንደሚሉት አንደኛው ሚሰዔል ባለ ሀያ አምስት ፎቅ ህንጻን የመታ ሲሆን ቢያንስ አስር ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል ፡፡

የሐሙሱ ጥቃት የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀኃፊ ጉቴሬዝ ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚየር ዜሌንስኪ ጋር የነበራቸውን ውይይት እንዳጠናቀቁ መፈጸሙ ቀውሱን አሳሳቢ አደርጎታል ፡፡
ኪዬቭ አሁንም ለሩሲያ ሚሳዔሎች የተጋለጠች እና ሰለባ የሆነች ከተማ መሆኗም አጽንኦት ተሰጥቶበታል ፡፡

ጉቴሬዝ የሚመሩት ድርጅት በዩክሬን ጦርነት ላይ መፍትሔ መስጠት አለመቻሉንም ተችተዋል ፡፡

ዋና ፀኃፊው የፀጥታው ምክር ቤት በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለመከላከል ወይንም እንዲቆም ለማድረግ የፈየደው ነገር የለም ባይ ናቸው ፡፡

ባለ አስራ አምስት ዓባላቱ የጸጥታው ምክር ቤት ለዓለምን ሰላም ማስፈን ቀዳሚ ስራው ቢሆንም ይህን ግን ማሳከላት አልቻለም ብለዋል ጉቴሬዝ ፡፡
ጉቴሬዝ ራሳቸውን እና የሚመሩትን ድርጅት መውቀሳቸው በዩክሬን ከፍተኛ ውድመት መከሰቱን የሚያሳይ ነው ተብሏል ፡፡

ዋሽንግተን ፖስት እና ቢቢሲ እንዳስነበቡት ፡፡

በብንያም ካሴ
አሐዱ ቴሌቪዥን
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ahadutelevision