Get Mystery Box with random crypto!

በሚሳዔል ማዕበል የምትጠበቀው የኪሞቹ አገር ሰሜን ኮሪያ በአራት ወራት ውስጥ አስራ አራተኛውን | AHADU TELEVISION

በሚሳዔል ማዕበል የምትጠበቀው የኪሞቹ አገር

ሰሜን ኮሪያ በአራት ወራት ውስጥ አስራ አራተኛውን የባሊስቲክ ሚሳዔል አስወነጨፈች ፡፡

ፒዮንግያንግ ራሴን ለማስከበር የኒውክሌር መርሃ ግብሬን አጠናክሬ እቀጥላለሁ ባለች ማግስት ባሊስቲክ ሚሳዔል ማስወንጨፏን ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ እወቁልን ብለዋል ፡፡

ኪም ጆንግ ኡንም በጦር መሳሪያ አቅም ጡንቻችን ማፈርጠም ከዋሽንግተንም ሆነ ከሌሎች ኃይሎች የሚቀጣብንን ወታደራዊ ጥቃት ለመቀልበስ ቁልፉ ወታደራዊ ዲፕሎማሲያችን ነው ብለው ያምናሉ፡፡

አዲሱ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት በዓለ-ሲመታቸውን ሊፈጽሙ እንደሆነ እየተነገረ ባለበት ወቅት ነው ኪሞቹ ባሊስቲክ ሚሰዔል ያስወነጨፉት ፡፡

ሰሜን ኮሪያ የመጨረሻ ሙከራዋን ያደረገችው በፈረንጆቹ ሚያዚያ 16 እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም ፡፡

መጋቢት ላይም ግዙፍ ነው ያለቸውን አህጉር አቋራጭ ሁዋሶንግ -17 የተሰኘ ባሊስቲክ ሚሳዔል ማስወንጨፏም ይታወሳል ፡፡

ሚሳዔሉ 4 መቶ 70 ኪ.ሜተትሮችን የሚያቋርጥ እና በ7መቶ 80 ኪ ሎ ሜትር ከፍታ የሚምዘገዘግ ነው ፡፡

የሰሜን ኮሪያ ተደጋጋሚ የሚሳዔል ሙከራ ለዩናይትድ ስቴትስ ፣ለጃፓን እንዲሁም ለጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያ ስጋት ከሆነ ሰነባብቷል ፡፡

ፒዮንግያንግ ዩናይትድ ስቴትስ ድረስ ዘልቆ ውድመት የሚያስከትል ረቂቅ የጦር መሳሪያ እንዳላት መታወቁ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ተደርጋ እንድትሳል አድርጓታል ፡፡
ኒውዮርክ ታይምስ እና ዎል ስትሪት ጆርናል እንዳስነበቡት
በብንያም ካሴ
አሐዱ ቴሌቪዥን
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ahadutelevision