2022-04-26 11:08:28
“ኒውክሌር አይናቅም ፤ጦርነት ጦርነት ነው”ሩሲያ
ሩሲያ የኒውክሌር ጦርነት ቀውስ ቀላል ግምት ሊሰጠው እንደማይገባ ዓለም ትወቅልኝ አለች፡፡
ሞስኮ ዓለም የሚመጣውን ቀውስ በቀላሉ ልትመለከተው አይገባም ባይ ናት ፡፡
ምዕራባውያን እንዲህ ዓይነቱን የጦርነት ነጋሪት ጉሰማ ሊቀንሱት እንደሚገባም በዘገባው ላይ ተመላክቷል ፡፡
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ስርጌ ላቭሮቭ የኒውክሌር ጦርነት አደጋው የከፋ እና ቀውሱ ሊታይ የሚችል ነው ብለውታል ፡፡
ሊፈጠር የሚችለውን ቀውስ በቀላሉ አናየውም ይላሉ ሚንስትሩ፡፡
የየናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር እና መከላከያ ሚንስትሮች በኪዬቭ ጉብኝት ካደረጉ በኋላ አገራቸው ለዩክሬን ወታደራዊ ድጋፍ ማድረጓን እንደምትገፋበት ማረጋገጣቸው የፑቲንን ኃይሎች አበሳጭቷል፡፡
በዋሽግተን የሞስኮ አምባሳደር ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ዩክሬን የምታደርገውን የመሳሪያ ማስገባት ሂደት ማቆም እንዳለባት አሳስበዋል ፡፡
ክሪሚሊኖች ምዕራባውያን ለዩክሬን ድጋፍ ማድረጋቸው ጦርነቱን ያባብሰዋል እንጂ አያለዝበውም ባዮች ናቸው ፡፡
የሩሲያው የውጭ ገዳይ ሚንስትር ስርጌ ላቭሮቭ እንደሚሉት የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት በእጅ አዙር ጦርነት ከሩሲያ ጋር እየተዋጋ ነው ፤በእጅ አዙርም ዩክሬንን እያስታጠቀ ነው ፡፡
ላቭሮቭ ጦርነት ጦርነት ነው ሌላ ትርጓሜ የለውም የሚል ዓይነት ሃሳባቸውን ለማጋራትም ሞክረዋል፡፡
ቢቢሲ እና ዘ ሮይተርስ እንደዘገቡት
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
752 views08:08