Get Mystery Box with random crypto!

🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ🌿

የቴሌግራም ቻናል አርማ adis_zena — 🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ🌿
የቴሌግራም ቻናል አርማ adis_zena — 🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ🌿
የሰርጥ አድራሻ: @adis_zena
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.96K
የሰርጥ መግለጫ

አዲስ ዜና ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support us
ለማስታወቂያ ስራ @adis_probot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-21 12:03:09
ትላንት በአሰቃቂ የመኪና አደጋ ህይወታቸው ያለፈ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ቁጥር 20 ደርሷል።

መምህራኑን ዩኒቨርሲቲው ከሚገኝበት ሮቤ ከተማ ወደ ዶዶላ እያጓጓዘ የነበረው ተሸከርካሪ መንገድ ስቶ ገደል በመግባቱ በተከሰተው አደጋ እስካሁን የ20 መምህራን ህይወት ማለፉን ዩኒቨርሲቲው አረጋግጧል።

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አዳባ፣ ዶዶላ እና ሮቤ ሆስፒታሎች ተወስደው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አህመድ ከሊል (ዶ/ር) ለኦቢኤን ተናግረዋል፡፡

በመኪና አደጋው ህይወታቸው ላለፈ መምህራን ዛሬ ጠዋት የአስክሬን ሽኝት በዩኒቨርሲቲው እና የአካባቢው ማህበረሰብ ተደርጓል።
@Adis_Zena
@Adis_Zena
1.5K views09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 12:02:57
የ @Adis_zena ቤተሰቦች በአሉን ምክንያት በማድረግ አገልግሎታችሁን በታላቅ ቅናሽ ማስተዋወቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። @adis_probot
1.5K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 21:04:48
በ2015 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከሐምሌ 03 እስከ 13 /2015 ዓ.ም ይከናወናል፡፡

በዚህም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግል እና በመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ዕጩ ምሩቃን እንዲሁም ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቃል፡፡

አገር አቀፍ የመውጫ ፈተናው በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ ከሐምሌ 03 እስከ 13 /2015 ዓ.ም ተሰጥቶ እንዲጠናቀቅ ሚኒስቴሩ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በኦንላይን የሚሰጠውን ፈተና በአገር አቀፍ ደረጃ ከ240 ሺህ በላይ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች እንደሚወስዱ ይጠበቃል፡፡
@Adis_zena
@Adis_zena
3.6K views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 09:53:57
የዴሞክራሲ ኃይሎች ወደ አንድ የመምጫ ጊዜ አሁን ነው!!

ፋሽዝም አቆጥቁጦ የአገር አንድነትና የሕዝብ አንድነት አደጋ እንዲሆን በተቃውሞ ጎራ የምንገኝ የዴሞክራሲ ኃይሎች ራሳችን ተወቃሾች ነን። ለአገዛዙ የጭቆና የድጋፍ ባላ ሆነን በመቆየታችን ዴሞክራሲን አኮስምነናል፤ ከእለት ወደ እለት የጭቆና ኃይሉ ወደለየለት ፋሽስታዊ ደረጃ እንዲያድግ በታሪክ ፊት ድንክ የሚያደርገንን ስህተት ሰርተናል። በዚህም አገርና ሕዝብ በድለናል።

ጥያቄው አሁንስ ከዚህ ስህተታችን ተምረናል ወይ ። የተቃውሞ ጎራው አሁንም ያሉ ውስን አቅሞችን በታትኖ በመንቀሳቀስ የጭቆና ተክል እንዲፋፋ በማዳበሪያነት ይቀጥላል ወይ? የዴሞክራሲ ኃይሎች አሁን ካልተሰባሰብን መቼ ልንሰባሰብ ነው?

ህዝቡ በተለይ የተቃዋሚ ሀይሎች ወደ አንድ መጥተው የአገርን አንድነትና የሕዝብን ደኅንነት እንዲያስጠብቁ በጎ ግፊት ማድረግ ይኖርበታል። በተለያዩ አሰላለፎች ያሉ መዋቅሮች፣ አመራሮችና አባላት በየድርጅቶቻቸው በኩል የዴሞክራሲ ኃይሎች ወደ አንድ መጥተው ለአገርና ሕዝብ በእንደዚህ ያለ ሁነኛ ጊዜ በጠንካራ ቁመና የሚገኝ አማራጭ መሆን እንደሚገባቸው ትግል ሊያደርጉ ይገባል።

ፋሽዝም ሲከስም የኢትዮጵያ ትንሳዔ ይጀምራል!

አቶ ክርሰቲያን ታደለ

@Adis_zena
@Adis_zena
1.9K viewsedited  06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 06:23:01
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት . . .

ትናንት ማክሰኞ የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በ "ኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት" ላይ ሊደረጉ የሚገቡ ናቸው ያላቸው ማሻሻያዎች ላይ ያደረገውን ጥናት ይፋ አድርጓል።

ጥናቱ ምን ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ?

ጥናቱ ሁሉም የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች ላይ ሳይሆን ብሔር ነክ በሆኑ ድንጋጌዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

አሁን ያለው ሕገ-መንግሥት ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ምንም ማሻሻያ ሳይደረግበት መቆየቱ ተገልጿል።

ኢንስቲትዩቱ ላለፉት ሁለት / 2 ዓመታት አከራካሪ በሆኑ የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች በተለይም ብሔር ነክ በሆኑ ድንጋጌዎች ላይ ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች የማሻሻያ ጥናት ማድረጉን አሳውዋል።

በጥናቱም ፦

በ2000 ዓ.ም ሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ከተዘረዘሩት 83 ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መካከል 41 የሚሆኑት በስልታዊ የዘፈቀደ ዘዴ (systematic random sampling) ተመርጠዋል ሲል አሳውቋል።

በዚህ መሠረት የሕገ-መንግሥቱ መግቢያ ላይ ያሉ የተወሰኑ ሐሳቦች ማለትም ፦

የብሔር ብሔረሰቦች ሉዓላዊነት አንቀፅ 8፣

የፌዴራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ፣

ብሔራዊ አርማ፣

#ብሔርን መሠረት ያደረገው አስተዳደራዊ ወሰን፣

#መገንጠልን የሚደነግገው አንቀፅ 39፣

የፖለቲካ ፓርቲን #በብሔር_ማደራጀት

#የአዲስ_አበባ_አስተዳደርን በተመለከተ መሻሻል እንዳለባቸው #ሕዝቡ_ፍላጎት እንዳለው ተመላክቷል ብሏል።
@Adis_Zena
@Adis_Zena
2.7K viewsedited  03:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 19:13:01
የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ የ6ኛ እና 8 ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የሚሰጥባቸውን ቀናት ይፋ አደርጓል።

የ8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 19 እና 20 እንዲሁም የ6ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 26 እና 27 እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ቢሮው ከተማ አቀፍ ፈተናዎቹን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመስጠት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የገለፀ ዲሆን ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹን የበለጠ ማዘጋጀት እንዲችሉ ከከተማና ክፍለ ከተሞች ጋር በጋራ በመሆን የሞዴል ፈተናዎችን እንዲሰጡ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በ2015 ዓ.ም 75,100 የ8ኛ እንዲሁም 75,078 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተናውን ይወስዳሉ።
@Adis_Zena
@Adis_Zena
5.1K viewsedited  16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 18:19:25 በመዲናዋ የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 22 እና 23/2015 ዓ.ም ይሰጣል:-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን) ሚያዚያ 19/2015 ዓም

በመዲናዋ የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 22 እና 23 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡

በ2015 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ በሆነው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ቢሮው ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡

ተፈታኝ ተማሪዎችን በስነ-ልቦና ከማዘጋጀት ባሻገር በትምህርት ቤቶች ቅዳሜና ከመደበኛ ትምህርት ውጭ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የተማሪዎችን ስነ-ልቦና ለማዘጋጀት የሚያግዝ የሞዴል ፈተና መሰጠቱን ጠቅሰው፤ በፈተናው አበረታች ውጤት ተገኝቷል ነው ያሉት፡፡

በቀጣይም ተጨማሪ የሞዴል ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ነው የተናገሩት፡፡

ይህን ተከትሎ ሰኔ 22 እና 23 ቀን 2015 ዓ.ም የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና እንደሚሰጥ ዶክተር ዘላለም የገለጹት።

የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ለመውሰድ 75ሺህ 102 ተማሪዎች የኦንላይን ምዝገባ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

በፈተና ወቅት ኩረጃ እንዳይኖር በቂ ዝግጅት መደረጉን  ገልጸው በመጀመሪያ ዙር የሞዴል ፈተና ወቅት ኩረጃ እንዳይኖር የሚያስቸሉ ተግባራት መከናወናቸውን አስረድተዋል።

በተመሳሳይ የስምንተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 19 እና 20 ቀን 2015 ዓ.ም በከተማ ደረጃ የሚሰጥ ሲሆን፤ 78ሺህ 78 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
@Adis_Zena
@Adis_Zena
8.5K viewsedited  15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 18:22:13
" የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና  ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡

ፈተናው ልክ እንደባለፈው አመት በሁለት ዙር የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ የፈተና ችግሮችን ዘርዝረው ለቀጣዩ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ2015 ዓ.ም ፈተናን ለማስፈፀም ልዩ ልዩ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑንና የተፈታኞች መረጃ በአግባቡ እየተደራጀ መሆኑን  አብራርተዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍና አመለካከቱን ለመቀየር፣ ብቁና አገር ተረካቢ ትዉልድ ለመፍጠር አሁን ያለው ባለድርሻ አካል ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ በአንክሮ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በ2016 ዓ.ም የሚካሄደው ፈተና እንደአካባቢው ሁኔታ ኦን ላይን እንደሚሆን ገልጸው የእለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡
@Adis_Zena
@Adis_Zena
9.8K viewsedited  15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 08:24:50
በትግራይ ክልል መደበኛ ትምህርት ሚያዝያ 23/2015 ዓ.ም ይጀመራል።

በትግራይ ክልል ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል መደበኛ ትምህርት ሚያዝያ 23/2015 ዓ.ም እንደሚጀመር የጊዜያዊ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የጊዜያዊ መንግስት በተቋቋመባቸው የክልሉ አካባቢዎች መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንደሚጀመር የቢሮው ኃላፊ ኪሮስ ጉኡሽ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

"በክልሉ ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ 2.4 ሚሊዮን ተማሪዎችን ወደ ትምህርታቸው ለመመለስ ምዝገባ እንደሚደረግ" ኃላፊው ገልጸዋል።
@Adis_Zena
@Adis_Zena
9.2K viewsedited  05:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 18:56:41
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገባችሁና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት የተሰጠውን ነፃ የትምህርት ዕድል (ስኮላርሺፕ) እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ ተማሪዎች በተከታዩ ሊንክ አማካይነት የማመልከቻ ፎርሙን መሙላት ትችላላችሁ፦

http://survey.ethernet.edu.et/index.php/518562?lang=en

የማመልከቻ ፎርሙን መሙላት የሚቻለው ከዛሬ ሚያዝያ 09 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት ቀናት ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

በማመልከቻ ፎርሙ ልትሞሏቸው የሚገቡ፦

➧ የ12ኛ ክፍል ውጤት ኮፒ፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኮፒ፣
➧ ግለ ታሪክ (CV) ኮፒ፣
➧ የልደት የምስክር ወረቀት ኮፒ እና
➧ ሌሎች በፎርሙ የተጠቀሱ መረጃዎች።

መረጃዎቹ ተጣርተው ለፈተና የሚቀረቡ ተማሪዎችን ዝርዝር በቀጣይ እንደሚያሳውቅ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
@Adis_Zena
@Adis_Zena
10.2K viewsedited  15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ