Get Mystery Box with random crypto!

🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ🌿

የቴሌግራም ቻናል አርማ adis_zena — 🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ🌿
የቴሌግራም ቻናል አርማ adis_zena — 🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ🌿
የሰርጥ አድራሻ: @adis_zena
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.96K
የሰርጥ መግለጫ

አዲስ ዜና ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support us
ለማስታወቂያ ስራ @adis_probot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-04-09 15:28:58 #MoE

የዲጂታል ትምህርት ስትራቴጂ እየተነደፈ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ስትራቴጂው በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት በመላ ሀገሪቱ ለመስጠት እንደሚያስችል በሚኒስቴሩ የአይሲቲና ዲጂታል ትምህርት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዘላለም አሰፋ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ዓለም አቀፉ ኩባንያ 'ህዋዌ ቴክኖሎጂ' በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የአይሲቲ አካዳሚ መክፈት መጀመሩ ብዙ የአይሲቲ ባለሙያዎችን ለማፍራት እንደሚያስችል ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ዘርፉ በቴክኖሎጂ የታገዘ መሆኑ ተማሪዎች ዓለም አቀፋዊ ዕውቀትን እንዲያገኙ የሚያስችል እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ምስል፦ የሁዋዌ አይሲቲ አካዳሚ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሲከፈት
@Adis_Zena
@Adis_Zena
10.6K viewsedited  12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 07:06:56
መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ለሚመረቁ የ4ኛ ዓመት ተማሪዎች ሞዴል የመውጫ ፈተና በኦንላይን ሰጥቷል።

በዩኒቨርሲቲው የተዘጋጀና ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ ሶፍትዌር፤ ሞዴል ፈተናውን ለመስጠት ጥቅም ላይ ውሏል።

ፈተናው ተማሪዎች ቴክኖሎጂውን እንዲለማመዱ፣ ቅድመ ዝግጅታቸውን እንዲፈትሹ እና ክፍተቶችን ለመለየት የሚያስችል መሆኑን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ካሳ ሻውል (ዶ/ር) ገልጸዋል።

በዚህ ዓመት መጨረሻ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና፤ 250 ሺህ የሚጠጉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች ፈተናውን በኦንላይን እንደሚወስዱ መንግስት መግለጹ ይታወሳል፡፡
@Adis_Zena
@Adis_Zena
10.5K viewsedited  04:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 10:22:40
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሞዴል ፈተና ለ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በቀጣይ ሳምንት ይሰጣል።

ሞዴል ፈተናው ከመጋቢት 27 እስከ 29/2015 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡

ሞዴል ፈተናው ስታንዳርዱን ጠብቆ በቢሮው መዘጋጀቱን የቢሮው የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክተር ዲናኦል ጫላ ገልጸዋል።

ፈተናው ተማሪዎች ራሳቸውን ለዋናው ፈተና ዝግጁ ማድረግ እንዲችሉ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።
@Adis_Zena
@Adis_Zena
11.5K viewsedited  07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 19:04:42 #AddisAbaba

" ከ75 ሺ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎችን የሚኒስትሪ ፈተና ለማስፈተን ዝግጅት እየተደረገ ነው " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ

ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠውን የ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ተማሪዎችን ለማስፈተን የዝግጅት ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋቃ።

የቢሮው የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሠጡት ቃል ፦

- በአዲስ አበባ ከተማ በግል እና በመንግሥት ትምህርት ቤቶች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙ ከ75 ሺህ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስፈተን ዝግጅት እየተደረገ ነው።

- ከቢሮ እስከ ትምህርት ቤቶች ድረስ ተማሪዎቹን ለፈተና የማዘጋጀት ሥራ እየተሠራ ይገኛል።

- ተማሪዎች የሚኒስትሪ ፈተና ከመፈተናቸው አስቀድሞ የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ ሞዴል ፈተናዎችን በማዘጋጀት በወሩ እንዲወስዱ ተደርጓል። ለፈተናው የተለያዩ አጋዥ መጽሐፍትንም አንብበው እንዲዘጋጁ እና እንዲፈተኑ እየተደረገ ነው።

- በአማርኛ ቋንቋ የሚፈተኑ አራት እንዲሁም በአፋን ኦሮሞ የሚፈተኑ አምስት የትምህርት ዓይነት ፈተናዎች የሚወስዱ ይሆናል። በዚህ መሠረትም ፦
የሒሳብ፣
የአካባቢ ሳይንስ፣
አማርኛ፣
አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶች ይሰጣሉ።

- ምዝገባው የሚካሄደው በኦንላይን ሲሆን የተመዘገቡ ተማሪዎች የተመዘገቡበትን የስም እና ዕድሜ ስህተት እንዳይኖር ማረጋገጥ እና ማስተካከል ይችላሉ።

- በየክላስተሩ ላሉ ትምህርት ቤቶች ወጥ በሆነ መልኩ ስልጠና በመስጠት ትምህርት ቤቶች ራሳቸው ፈተናዎችን እንዲያወጡ እና እንዲፈተኑ ይደርጋል።

- በአዲሱ ሥርዓት ትምህርት በየምዕራፉ ማጠናቀቂያ ላይ ለተማሪዎች ፈተና ይሰጣል። ለዚህም አንደኛ ምዕራፍ የሚባለው ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል ያለው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ሲሆን ሁለተኛ ምዕራፍ የሚባለው ከሰባት እስከ ስምንተኛ ክፍል ነው።

- የመጀመሪያ ምዕራፍ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚያጠናቅቁት ስድስተኛ ክፍል ላይ ስለሆነ የሚኒስትሪ ፈተናው ተማሪዎች ከታች ጀምረው ራሳቸውን እያነጹ እንዲመጡ የሚያደርግ ነው። የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ አንጻር ከፍተኛ ጥቅም አለው።

- የመማሪያ መጽሐፍት በሚፈለገው ልክ ሀገር ውስጥ አለመገኘት እና በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ከውጭ የሚመጡ መጽሐፍት የመዘግየት ሁኔታ አለ።

- የሚኒስትሪ ፈተና የሚሰጥበት ቀናት የሚወሰነው በአገር አቀፍ ደረጃ ቢሆንም እንደ ቢሮ #ከሰኔ አጋማሽ በኋላ ለመስጠት ዝግጁ ነን።
@Adis_Zena
@Adis_Zena
12.4K viewsedited  16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 07:39:37 #MoE

250 ሺህ ለሚጠጉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በመጪው ሐምሌ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተጠናቀቅ እንደሚገኝ በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ሰይድ መሐመድ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስቴሩ የመውጫ ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት ከመንግሥት እና ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የመውጫ ፈተናውን ወስደው ማለፍ ያልቻሉ ተማሪዎች ደጋግመው መፈተን የሚችሉበት ዕድል መኖሩን ኃላፊው አመልክተዋል።

ፈተናውን በተደጋጋሚ ወስዶ ማለፍ ያልቻለ ተማሪ ከዲግሪ በታች ባሉ ደረጃዎች ምዘና እንዲወስድ የሚያደርግ የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ በትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን በመዘጋጀት ላይ ይገኛል ብለዋል።

ይሁን እንጂ ተፈታኙ ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዝግጁ ነኝ ብሎ ባሰበ ጊዜ ፈተናውን መውሰድና ማለፍ ከቻለ የዲግሪ ማረጋገጫ ማግኘት እንደሚችል ገልጸዋል።

የመውጫ ፈተናው በኦንላይን እንደሚሰጥ ያመለከቱት ኃላፊው፤ ተማሪዎች ዋናውን ፈተና ከመፈተናቸው በፊት ሞዴል ፈተናዎች እንደሚወስዱ ጠቅሰዋል፡፡ 
@Adis_Zena
@Adis_Zena
10.9K viewsedited  04:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 11:01:59 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የጠራው ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ አለመኖሩን አሳውቋል።

በዚህ ዓመት ሊሰጥ በታሰበው የመውጫ ፈተና ዙሪያ በስሙ የተሰራጨው መረጃ ህብረቱን የማይወክል መሆኑንም ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል።

በዚህ ዓመት እንዲሰጥ በተወሰነው የመውጫ ፈተና ላይ ተማሪዎች በሚያነሷቸው ስጋቶችና ቅሬታዎች ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይቶች መደረጋቸውን ወደፊትም እንደሚደረጉ ህብረቱ ገልጿል።

በውይይቶቹ የተነሱ ሀሳቦች ገሚሶቹ ምላሽ ያገኙ ሲሆን በቀጣይ የሚስተካከሉ መረጃዎችን የሚያሳወቅ መሆኑንም ህብረቱ ጠቁሟል።

ፈተናው የተማሪዎችን ብቃት የሚመዝንና የትምህርት ጥራት ሊያስጠብቅ በሚችልበት ሁኔታ ላይ አሁንም በጋራ እየሠራ መሆኑን ህብረቱ አስታውሷል።

ተማሪዎች በፈተናው እና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ሀሳብ በግቢያቸው ለሚገኙ የተማሪዎች ህብረት እያቀረቡ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አማካይነት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመወያየት ምላሽ የሚሰጥበት መሆኑንም ገልጿል።

በቅርቡ የተሰራጨው መረጃ ህብረቱን የማይወክልና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የገለጸው ህብረቱ፤ በህብረቱ የተጠራ ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ አለመኖሩን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል።

ተመራቂ ተማሪዎች በተቋሞቻቸውና በተማሪዎች ህብረት አማካይነት የሚሰጡ የድጋፍ ትምህርቶችን በመከታተል ለመውጫ ፈተናው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ህብረቱ ጥሪ አድርጓል።

ሐሰተኛና የተዛባ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ህብረቱ አሳስቧል።
@Adis_Zena
@Adis_Zena
10.1K viewsedited  08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 13:28:24
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ከ1 ሺህ 400 በላይ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER
8.9K viewsedited  10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 08:14:52
#GambellaUniversity

በ2015 ዓ.ም በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ ሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች መግቢያ ጊዜ መጋቢት 08 እና 09/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➧ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፡፡

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
11.7K views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 17:53:43 በ2015 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ መደበኛ እና የአቅም ማሻሻያ ሪሚዲያል የመግቢያ ቀን ያሳወቁ ዩኒቨርሲቲዎች

¤ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ - መጋቢት 11 እና 12

¤ ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ መጋቢት 16 እና 17

¤ አምቦ ዩኒቨረሲቲ መጋቢት 7 እና 8

¤  መቅደላ አምባ ዩኒቨረሲቲ መጋቢት 7 እና 8

¤ ቡሌ ሆራ ዩኒቨረሲቲ መጋቢት 4 እና 5

¤ ጂንካ ዩኒቨረሲቲ መጋቢት 4 እና 5

¤ መዳ ወላቡ ዩኒቨረሲቲ መጋቢት 7 እና 8

¤ ወለጋ ዩኒቨረሲቲ መጋቢት 7 እና 8

¤ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨረሲቲ መጋቢት 4 እና 5

¤ ኢንጂባራ ዩኒቨረሲቲ መጋቢት 4 እና 5

¤ ደባርቅ ዩኒቨረሲቲ መጋቢት 5 እና 6

¤ አሶሳ ዩኒቨረሲቲ መጋቢት 11 እና 12

¤ ወሎ ዩኒቨረሲቲ መጋቢት 4 እና 5

¤ ቦረና ዩኒቨረሲቲ መጋቢት 11 እና 12

¤ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨረሲቲ መጋቢት 8 እና 9

Share  @Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
10.5K views14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-12 11:46:28
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ለአቅም ማሻሻያ Remedial ፕሮግራም የተመደቡ ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው የሪሚዲያል ተማሪዎችን በነገው ዕለትም መቀበሉን ይቀጥላል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
10.0K views08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ